Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 26:59 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

59 የቆሬ ወገን፥ የቀ​ዓት ወገን። ቀዓ​ትም እን​በ​ረ​ምን ወለደ። በግ​ብፅ ሀገር እነ​ዚ​ህን ሌዋ​ው​ያ​ንን የወ​ለ​ደ​ቻ​ቸው የሌዊ ልጅ የእ​ን​በ​ረም ሚስት ስም ዮካ​ብድ ነበረ። ለእ​ን​በ​ረ​ምም አሮ​ን​ንና ሙሴን እኅ​ታ​ቸ​ው​ንም ማር​ያ​ምን ወለ​ደ​ች​ለት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

59 የእንበረም ሚስቱ ዮካብድ ትባል ነበር፤ እርሷም በግብጽ አገር ከሌዋውያን የተወለደች የሌዊ ዘር ነበረች። ከእንበረምም አሮንን፣ ሙሴንና እኅታቸውን ማርያምን ወለደች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

59 የእንበረም ሚስት ስም ዮካብድ ነበረ። እርሷ በግብጽ ከሌዊ የተወለደች የሌዊ ልጅ ነበረች፤ ለእንበረምም አሮንንና ሙሴን እኅታቸውንም ማርያምን ወለደችለት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

59 ዓሞራም በግብጽ የተወለደችውን የሌዊን ሴት ልጅ ዮኬቤድን አግብቶ ነበር፤ እርስዋም አሮንና ሙሴ የተባሉትን ሁለት ወንዶች ልጆችንና ማርያም የተባለችውን አንዲት ሴት ልጅ ወለደችለት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

59 የእንበረም ሚስት ስም ዮካብድ ነበረ። እርስዋ በግብፅ ከሌዊ የተወለደች የሌዊ ልጅ ነበረች፤ ለእንበረምም አሮንንና ሙሴን እኅታቸውንም ማርያምን ወለደችለት።

参见章节 复制




ዘኍል 26:59
7 交叉引用  

የአ​ሮን እኅት ነቢ​ይቱ ማር​ያ​ምም ከበሮ በእ​ጅዋ ወሰ​ደች፤ ሴቶ​ችም ሁሉ በከ​በ​ሮና በዝ​ማሬ በኋ​ላዋ ወጡ።


እኅ​ቱም ምን እን​ደ​ሚ​ደ​ር​ስ​በት ታውቅ ዘንድ በሩቅ ቆማ ትጐ​በ​ኘው ነበር።


እን​በ​ረ​ምም የአ​ባ​ቱን ወን​ድም ልጅ ዮካ​ብ​ድን አገባ፤ አሮ​ን​ንና ሙሴን፥ እኅ​ታ​ቸ​ው​ንም ማር​ያ​ምን ወለ​ደ​ች​ለት፤ የእ​ን​በ​ረ​ምም የሕ​ይ​ወቱ ዘመን መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ነው።


የአ​ባ​ት​ህን እኅት ኀፍ​ረተ ሥጋ አት​ግ​ለጥ፤ የአ​ባ​ትህ ዘመድ ናትና።


ሙሴም ኢት​ዮ​ጵ​ያ​ዊ​ቱን ሴት አግ​ብ​ቶ​አ​ልና ባገ​ባት በኢ​ት​ዮ​ጵ​ያ​ዊቱ ሴት ምክ​ን​ያት ማር​ያ​ምና አሮን አሙት።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር ወደ ጺን ምድረ በዳ መጡ፤ ሕዝ​ቡም በቃ​ዴስ ተቀ​መጡ፤ ማር​ያ​ምም በዚያ ሞተች፤ ተቀ​በ​ረ​ችም።


跟着我们:

广告


广告