Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 24:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ዐማ​ሌ​ቅ​ንም አይቶ በም​ሳሌ ይና​ገር ጀመር፤ እን​ዲ​ህም አለ፦ “ዐማ​ሌቅ የአ​ሕ​ዝብ አለቃ ነበረ፤ ዘራ​ቸ​ውም ይጠ​ፋል።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ከዚያም በለዓም አማሌቅን አይቶ ንግሩን እንዲህ ሲል ጀመረ፤ “አማሌቅ ከሕዝቦች የመጀመሪያው ነበር፤ በመጨረሻ ግን ይደመሰሳል።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 በለዓምም አማሌቅን አይቶ ምሳሌውን ይመስል ጀመር፥ እንዲህም አለ፦ “የአሕዛብ መጀመሪያ የሆነ አማሌቅ ነበረ፤ ፍጻሜው ግን ወደ ጥፋት የሚያመራ ይሆናል።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ከዚህ በኋላ በለዓም ወደ ዐማሌቅ በመመልከት እንዲህ ሲል ይህን የትንቢት ቃል ተናገረ፦ “ዐማሌቅ ከሁሉ የሚበልጥ ኀያል ሕዝብ ነበረ፤ በመጨረሻ ግን እርሱ ራሱ ለዘለዓለም ይጠፋል።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 አማሌቅንም አይቶ ምሳሌውን ይመስል ጀመር፥ እንዲህም አለ፦ አማሌቅ የአሕዛብ አለቃ ነበረ፤ ፍጻሜው ግን ወደ ጥፋት ይመጣል።

参见章节 复制




ዘኍል 24:20
18 交叉引用  

ቴም​ና​ሕም ለዔ​ሳው ልጅ ለኤ​ል​ፋዝ ዕቅ​ብት ነበ​ረች፤ አማ​ሌ​ቅ​ንም ለኤ​ል​ፋዝ ወለ​ደ​ች​ለት፤ የዔ​ሳ​ውም ሚስት የሐ​ዳሶ ልጆች እነ​ዚህ ናቸው።


ያመ​ለ​ጡ​ት​ንም የአ​ማ​ሌ​ቃ​ው​ያ​ንን ቅሬታ መቱ፥ በዚ​ያም እስከ ዛሬ ድረስ ተቀ​ም​ጠ​ዋል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “የዐ​ማ​ሌ​ቅን ዝክር ከሰ​ማይ በታች ጨርሼ እደ​መ​ስ​ሳ​ለ​ሁና ይህን ለመ​ታ​ሰ​ቢያ በመ​ጽ​ሐፍ ጻፈው፤ በኢ​ያ​ሱም ጆሮ ተና​ገር” አለው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በተ​ሰ​ወ​ረች እጅ ዐማ​ሌ​ቅን እስከ ልጅ ልጅ ይዋ​ጋ​ልና።


ዐማ​ሌ​ቅም መጥቶ ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋራ በራ​ፊድ ተዋጋ።


ከያ​ዕ​ቆ​ብም ኀያል ሰው ይወ​ጣል፤ ከከ​ተ​ማ​ውም የቀ​ሩ​ትን ያጠ​ፋል።”


ከቄ​ጤ​ዎ​ንም እጅ የሚ​ወ​ጣው አሦ​ር​ንና ዕብ​ራ​ው​ያ​ንን ያስ​ጨ​ን​ቃል፤ እነ​ር​ሱም በአ​ን​ድ​ነት ይጠ​ፋሉ።”


ከዘሩ ሰው ይወ​ጣል፤ ብዙ ሕዝ​ብ​ንም ይገ​ዛል፥ መን​ግ​ሥ​ቱም ከአ​ጋግ ይልቅ ከፍ ከፍ ትላ​ለች፥ መን​ግ​ሥ​ቱም ትሰ​ፋ​ለች።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ዘር በዘሩ ጊዜ ምድ​ያ​ማ​ው​ያ​ንና አማ​ሌ​ቃ​ው​ያን ይዘ​ም​ቱ​ባ​ቸው ነበር፥ በም​ሥ​ራ​ቅም የሚ​ኖሩ ልጆች አብ​ረው ይዘ​ም​ቱ​ባ​ቸው ነበር፤


እር​ሱም ጀግና ነበረ፤ አማ​ሌ​ቃ​ው​ያ​ን​ንም መታ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ከዘ​ራ​ፊ​ዎቹ እጅ አዳነ።


የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እስ​ራ​ኤል ከግ​ብፅ በወጡ ጊዜ በመ​ን​ገድ እንደ ተዋጉ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ክፉ ያደ​ረ​ጉ​ትን አማ​ሌ​ቃ​ው​ያ​ንን ዛሬ እበ​ቀ​ላ​ለሁ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ዳዊ​ትና ሰዎቹ በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ወደ ሴቄ​ላቅ በገቡ ጊዜ፥ አማ​ሌ​ቃ​ው​ያን በአ​ዜብ በሰ​ቄ​ላ​ቅም ላይ ዘም​ተው ነበር፤ ሴቄ​ላ​ቅ​ንም መት​ተው በእ​ሳት አቃ​ጥ​ለ​ዋት ነበር፥


ዳዊ​ትም ሄዶ የአ​ጥ​ቢያ ኮከብ ከሚ​ወ​ጣ​በት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ዳግ​መ​ኛም በማ​ግ​ሥቱ መታ​ቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም በግ​መል ተቀ​ም​ጠው ከሸ​ሹት አራት መቶ ጐል​ማ​ሶች በቀር አን​ድም ያመ​ለጠ የለም።


跟着我们:

广告


广告