Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 22:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 እር​ሱም በአ​ህ​ያ​ዪቱ ላይ ተቀ​ምጦ ነበር፤ ሁለ​ቱም ብላ​ቴ​ና​ዎቹ ከእ​ርሱ ጋር ነበሩ። አህ​ያ​ዪ​ቱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መል​አክ በመ​ን​ገድ ላይ ቆሞ የተ​መ​ዘ​ዘም ሰይፍ በእጁ ይዞ አየች፤ ከመ​ን​ገ​ዱም ላይ ፈቀቅ ብላ ወደ ሜዳ ውስጥ ገባች፤ በለ​ዓ​ምም ወደ መን​ገድ ይመ​ል​ሳት ዘንድ አህ​ያ​ዪ​ቱን መታት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 አህያዪቱም የእግዚአብሔር መልአክ የተመዘዘ ሰይፍ ይዞ በመንገድ ላይ መቆሙን ባየች ጊዜ ከመንገድ ወጥታ ዕርሻ ውስጥ ገባች፤ በለዓምም ወደ መንገዱ እንድትመለስ መታት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 አህያይቱም የጌታን መልአክ በመንገድ ላይ ቆሞ የተመዘዘም ሰይፍ በእጁ ይዞ አየች፤ እርሷም ከመንገዱ ፈቀቅ ብላ ወደ እርሻው ውስጥ ገባች፤ በለዓምም ወደ መንገድ እንድትመለስ አህያይቱን መታት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 መልአኩ ሰይፉን መዞ በመንገዱ ላይ መቆሙን አህያይቱ በተመለከተች ጊዜ መንገዱን ለቃ ወደ እርሻ ገባች፤ በለዓምም አህያይቱን ወደ መንገዱ ለመመለስ ደበደባት፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 አህያይቱም የእግዚአብሔርን መልአክ በመንገድ ላይ ቆሞ የተመዘዘም ሰይፍ በእጁ ይዞ አየች፤ ከመንገዱም ፈቀቅ ብላ ወደ እርሻው ውስጥ ገባች፤ በለዓምም ወደ መንገድ ይመልሳት ዘንድ አህያይቱን መታት።

参见章节 复制




ዘኍል 22:23
11 交叉引用  

ኤል​ሳ​ዕም፥ “አቤቱ፥ ያይ ዘንድ ዐይ​ኖ​ቹን፥ እባ​ክህ፥ ግለጥ” ብሎ ጸለየ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የብ​ላ​ቴ​ና​ውን ዐይ​ኖች ገለጠ፤ እነ​ሆም፥ የእ​ሳት ፈረ​ሶ​ችና ሰረ​ገ​ሎች በኤ​ል​ሳዕ ዙሪያ ተራ​ራ​ውን ሞል​ተ​ውት አየ።


ዳዊ​ትም ዐይ​ኖ​ቹን አነሣ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ በም​ድ​ርና በሰ​ማይ መካ​ከል ቆሞ፥ የተ​መ​ዘ​ዘም ሰይፍ በእጁ ሆኖ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ተዘ​ር​ግቶ አየ። ዳዊ​ትና ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቹም ማቅ ለብ​ሰው በግ​ን​ባ​ራ​ቸው ተደፉ።


ሽመላ በሰ​ማይ ጊዜ​ዋን አው​ቃ​ለች፤ ዋኖ​ስና ጨረባ፥ ዋሊ​ያም የመ​ም​ጣ​ታ​ቸ​ውን ጊዜ ይጠ​ብ​ቃሉ፤ ሕዝቤ ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍርድ አላ​ወ​ቁም።


እር​ሱም ስለ ሄደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተቈጣ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ሊያ​ሰ​ና​ክ​ለው ተነሣ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ከወ​ይኑ ቦታ​ዎች መካ​ከል በወ​ዲ​ያና በወ​ዲህ ወገን ግንብ በነ​በ​ረ​በት ቆመ።


አብ​ረ​ውኝ የነ​በ​ሩ​ትም መብ​ረ​ቁን አይ​ተው ደነ​ገጡ፤ ነገር ግን ይና​ገ​ረኝ የነ​በ​ረ​ውን ቃል አል​ሰ​ሙም።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ኢያሱ በኢ​ያ​ሪኮ አጠ​ገብ ሳለ ዐይ​ኑን አን​ሥቶ ተመ​ለ​ከተ፤ እነ​ሆም፥ የተ​መ​ዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ ሰው በፊቱ ቆሞ አየ፤ ኢያ​ሱም ወደ እርሱ ቀርቦ፥ “ከእኛ ወገን ወይስ ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችን ወገን ነህ?” አለው።


ነገር ግን ስለ መተላለፉ ተዘለፈ፤ ቃል የሌለው አህያ በሰው ቃል ተናግሮ የነቢዩን እብድነት አገደ።


ወዮላቸው! በቃየል መንገድ ሄደዋልና፤ ስለ ደመወዝም ለበለዓም ስሕተት ራሳቸውን አሳልፈው ሰጥተዋል፤ በቆሬም መቃወም ጠፍተዋል።


跟着我们:

广告


广告