Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 21:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ከሖ​ርም ተራራ በኤ​ር​ትራ ባሕር መን​ገድ ተጓዙ፤ የኤ​ዶ​ም​ንም ምድር ዞሩ​አት፤ ሕዝ​ቡም በመ​ን​ገድ ተበ​ሳጩ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እስራኤላውያን በኤዶም ዞረው ለመሄድ ስላሰቡ ከሖር ተራራ ተነሥተው ወደ ቀይ ባሕር በሚወስደው መንገድ ተጓዙ፤ ይሁን እንጂ ሕዝቡ በመንገድ ሳለ ትዕግሥቱ ዐለቀ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ከሖርም ተራራ የኤዶምያስን ምድር በዙርያው አድርገው ለመሄድ በኤርትራ ባሕር መንገድ ተጓዙ፤ ሕዝቡም በመንገድ እየተጓዙ ሳሉ ጉልበታቸው ደከመ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 እስራኤላውያን በኤዶም ግዛት ዙሪያ ለመሄድ አስበው ከሖር ተራራ ተነሥተው ወደ ቀይ ባሕር በሚወስደው መንገድ ተጓዙ፤ ነገር ግን በመንገድ ሳሉ የሕዝቡ ትዕግሥት አለቀ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ከሖርም ተራራ ከኤዶምያስ ምድር ርቀው ሊዞሩ በኤርትራ ባሕር መንገድ ተጓዙ፤ የሕዝቡም ሰውነት ከመንገዱ የተነሣ ደከመ።

参见章节 复制




ዘኍል 21:4
14 交叉引用  

ደግ​ሞም፥ “በየ​ት​ኛው መን​ገድ እን​ሄ​ዳ​ለን?” አለ፤ እር​ሱም፥ “በኤ​ዶ​ም​ያስ ምድረ በዳ መን​ገድ” አለው።


ሙሴም ይህን ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ተና​ገረ፤ እነ​ርሱ ግን ከሰ​ው​ነ​ታ​ቸው መጨ​ነቅ፥ ከሥ​ራ​ቸ​ውም ክብ​ደት የተ​ነሣ ቃሉን አል​ሰ​ሙ​ትም።


ዐማ​ሌ​ቅና ከነ​ዓ​ና​ዊ​ውም በሸ​ለቆ ውስጥ ተቀ​ም​ጠ​ዋል፤ እና​ንተ ግን ነገ ተመ​ል​ሳ​ችሁ በኤ​ር​ትራ ባሕር መን​ገድ ወደ ምድረ በዳ ሂዱ።”


ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘዘ አደ​ረገ፤ በማ​ኅ​በ​ሩም ሁሉ ፊት እያዩ ወደ ሖር ተራራ አወ​ጣ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ​ሚ​ሰ​ጣ​ቸው ምድር እን​ዳ​ይ​ሻ​ገሩ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ልብ ለምን ታጣ​ም​ማ​ላ​ችሁ?


ወደ ወይን ዘለላ ሸለቆ መጡ፤ ምድ​ሪ​ቱ​ንም አዩ​አት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወደ ሰጣ​ቸው ምድር እን​ዳ​ይ​ገቡ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ልብ መለሱ።


እነ​ር​ሱም ከሖር ተራራ ተጕ​ዘው በሴ​ል​ሞና ሰፈሩ።


የደቀ መዛ​ሙ​ር​ት​ንም ልቡና አጽ​ናኑ፤ በሃ​ይ​ማ​ኖ​ትም እን​ዲ​ጸኑ፦“ በብዙ ድካ​ምና መከራ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት እን​ገባ ዘንድ ይገ​ባ​ናል” እያሉ መከ​ሩ​አ​ቸው።


እና​ንተ ግን ተመ​ል​ሳ​ችሁ በኤ​ር​ትራ ባሕር መን​ገድ ወደ ምድረ በዳ ሂዱ።


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዳ​ለኝ ተመ​ል​ሰን በኤ​ር​ትራ ባሕር መን​ገድ ወደ ምድረ በዳ ሄድን፤ የሴ​ይ​ር​ንም ተራራ ብዙ ቀን ዞርን።


እስ​ራ​ኤ​ልም በቃ​ዴስ ተቀ​መጠ። በም​ድረ በዳም በኩል አለፈ፤ የኤ​ዶ​ም​ያ​ስ​ንና የሞ​ዓ​ብ​ንም ምድር ዞሩ፤ ከሞ​ዓብ ምድ​ርም በም​ሥ​ራቅ በኩል መጡ፤ በአ​ር​ኖ​ንም ማዶ ሰፈሩ፤ አር​ኖ​ንም የሞ​ዓብ ድን​በር ነበ​ረና ወደ ሞዓብ ድን​በር አል​ገ​ቡም።


跟着我们:

广告


广告