ዘኍል 21:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)24 እስራኤልም በሰይፍ መታው፤ ምድሩንም ከአርኖን ጀምሮ እስከ አሞን ልጆች እስከ ያቦቅ ድረስ ወረሰ፤ የአሞንም ልጆች ዳርቻ ኢያዜር ነበረ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም24 እስራኤል ግን በሰይፍ መታው፤ ከአርኖን እስከ ያቦቅ ድረስ ያለውንም ምድሩን ወሰደበት፤ ይሁን እንጂ የአሞናውያን ወሰን የተመሸገ ስለ ነበር ከያቦቅ አላለፈም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)24 እስራኤልም በሰይፍ መታው፥ ምድሩንም ከአርኖን ጀምሮ እስከ ያቦቅ እስከ አሞን ልጆች ድረስ ወረሰ፤ የአሞንም ልጆች ዳርቻ የጸና ነበረ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም24 እስራኤላውያን ግን ድል ነሡአቸው፤ ከአርኖን ወንዝ አንሥቶ በስተሰሜን እስከ ዐሞናውያን ወሰን ማለትም እስከ ያቦቅ ወንዝ ድረስ የሚገኘውን ግዛት ያዙ፤ ይሁን እንጂ የዐሞናውያን ወሰን በብርቱ የተጠበቀ በመሆኑ ወደዚያ አልገቡም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)24 እስራኤልም በሰይፍ መታው፥ ምድሩንም ከአሮኖን ጀምሮ እስከ አሞን ልጆች እስከ ያቦቅ ድረስ ወረሰ፤ የአሞንም ልጆች ዳርቻ የጸና ነበረ። 参见章节 |