Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 19:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 “ሰውም ርኩስ ቢሆን ሁለ​መ​ና​ው​ንም ባያ​ነጻ፥ ያ ሰው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መቅ​ደስ አር​ክ​ሶ​አ​ልና ከማ​ኅ​በሩ መካ​ከል ተለ​ይቶ ይጠ​ፋል፤ በሚ​ያ​ነጻ ውኃ አል​ተ​ረ​ጨ​ምና ርኩስ ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ይሁን እንጂ አንድ የረከሰ ሰው ራሱን ሳያነጻ ከቀረ የእግዚአብሔርን መቅደስ አርክሷልና ከማኅበረ ሰቡ ተለይቶ ይጥፋ፤ የሚያነጻው ውሃ ያልተረጨበት ስለ ሆነ ርኩስ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 “ሰውም ርኩስ ቢሆን ሁለመናውንም ባያነጻ፥ ያ ሰው የጌታን መቅደስ አርክሶአልና ከጉባኤው መካከል ተለይቶ ይጠፋል፤ ከርኩሰት የሚያነጻውን ውኃ አልተረጨም፤ ርኩስ ነው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 “ያልነጻና ራሱንም ያላነጻ ሰው ለማንጻት የተመደበው ውሃ በላዩ ስላልፈሰሰ የረከሰ ሆኖ ይቈያል፤ እንደዚህ ያለው ሰው የእግዚአብሔርን ድንኳን ስለሚያረክስ ከማኅበሩ ይለይ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ሰውም ርኩስ ቢሆን ሁለመናውንም ባይጠራ፥ ያ ሰው የእግዚአብሔርን መቅደስ አርክሶአልና ከጉባኤው መካከል ተለይቶ ይጠፋል፤ በሚያነጻ ውኃ አልተረጨም፤ ርኩስ ነው።

参见章节 复制




ዘኍል 19:20
13 交叉引用  

በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀን የሥ​ጋ​ውን ቍል​ፈት ያል​ተ​ገ​ረዘ፥ ያች ነፍስ ከወ​ገ​ንዋ ተለ​ይታ ትጥፋ፤ ቃል ኪዳ​ኔን አፍ​ር​ሳ​ለ​ችና።”


እንደ እርሱ ያለ​ውን የሚ​ያ​ደ​ርግ ሰው፥ በሌ​ላም ሰው ላይ የሚ​ያ​ፈ​ስ​ሰው ከሕ​ዝቡ ተለ​ይቶ ይጥፋ።”


“እን​ዲ​ሁም በእ​ነ​ርሱ መካ​ከል ያለ​ች​ውን ድን​ኳ​ኔን ባረ​ከሱ ጊዜ፥ በር​ኩ​ስ​ነ​ታ​ቸው እን​ዳ​ይ​ሞቱ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከር​ኩ​ስ​ነ​ታ​ቸው አን​ጹ​አ​ቸው።


ልብ​ሱ​ንና ገላ​ውን ባያ​ጥብ ግን ኀጢ​አ​ቱን ይሸ​ከ​ማል።”


ከአ​ሮን ዘር ለምጽ ወይም ፈሳሽ ነገር ያለ​በት ሁሉ ንጹሕ እስ​ኪ​ሆን ድረስ ከተ​ቀ​ደ​ሰው አይ​ብላ። ከበ​ድ​ንም የተ​ነሣ ርኩስ የሆ​ነ​ውን፥ ወይም ዘሩ ከእ​ርሱ የሚ​ፈ​ስ​ስ​በ​ትን የሚ​ነካ፥


የሀ​ገር ልጅ ቢሆ​ንም ወይም መጻ​ተኛ ቢሆን፥ በእጁ ትዕ​ቢ​ትን የሚ​ያ​ደ​ርግ ሰው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሰድ​ቦ​አል፤ ያም ሰው ከሕ​ዝቡ መካ​ከል ተለ​ይቶ ይጠ​ፋል።


የሞ​ተ​ውን ሰው በድን የነካ ሁለ​መ​ና​ውን ባያ​ነጻ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ድን​ኳን ያረ​ክ​ሳል፤ ያ ሰው ከእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ተለ​ይቶ ይጠ​ፋል፤ በእ​ር​ሱም ላይ የሚ​ያ​ነጻ ውኃ አል​ተ​ረ​ጨ​ምና ርኩስ ይሆ​ናል፤ ርኵ​ሰቱ ገና በእ​ርሱ ላይ ነው።


ነገር ግን ንጹሕ የሆነ ሰው በመ​ን​ገ​ድም ላይ ያል​ሆነ ፋሲ​ካን ባያ​ደ​ርግ፥ ያ ሰው ከሕ​ዝቡ ዘንድ ተለ​ይቶ ይጠ​ፋል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቍር​ባን በጊ​ዜው አላ​ቀ​ረ​በ​ምና ያ ሰው ኀጢ​አ​ቱን ይሸ​ከ​ማል።


ያመነ የተጠመቀም ይድናል፤ ያላመነ ግን ይፈረድበታል።


ስለዚህ ወዳጆች ሆይ! ይህን እየጠበቃችሁ ያለ ነውርና ያለ ነቀፋ ሆናችሁ በሰላም በእርሱ እንድትገኙ ትጉ፤


ዐመፀኛው ወደ ፊት ያምፅ፤ ርኵሱም ወደ ፊት ይርከስ፤ ጻድቁም ወደ ፊት ጽድቅ ያድርግ፤ ቅዱሱም ወደፊት ይቀደስ፤” አለ።


跟着我们:

广告


广告