Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 17:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ነገ​ረው፥ “ማጕ​ረ​ም​ረ​ማ​ቸው ከእኔ ዘንድ እን​ዲ​ጠፋ፥ እነ​ር​ሱም እን​ዳ​ይ​ሞቱ ለማ​ይ​ሰሙ ልጆች ምል​ክት ሆና ትጠ​በቅ ዘንድ የአ​ሮ​ንን በትር በም​ስ​ክሩ ፊት አኑር።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 እግዚአብሔር ሙሴን፣ “የአሮን በትር ለዐመፀኞቹ ምልክት እንድትሆን መልሰህ በምስክሩ ፊት ለፊት አኑራት፤ እነርሱ እንዳይሞቱም በእኔ ላይ የሚያደርጉትን ማጕረምረም ይህ ይገታዋል” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “የአሮንን በትር ወደ ምስክሩ ፊት መልሰህ አኑር፤ እርሱም ለሚያምፁብኝ ልጆች ምልክት ሆኖ ይቀመጥ፤ እነርሱም እንዳይሞቱ በእኔ ላይ ማጉረምረማቸውን ታስቆምበታለህ።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “የአሮንን በትር በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት መልሰህ አኑረው፤ ዐመፀኞች የሆኑ እስራኤላውያን በእኔ ላይ ማጒረምረማቸውን ካልተዉ እንደሚሞቱ ማስጠንቀቂያ ሆኖ ይቀመጥ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 እግዚአብሔርም ሙሴን፦ የአሮንን በትር ወደ ምስክሩ ፊት መልስ፤ ማጕረምረማቸው ከእኔ ዘንድ እንዲጠፋ እነርሱም እንዳይሞቱ ለሚያምፁብኝ ልጆች ምልክት ሆና ትጠበቅ አለው።

参见章节 复制




ዘኍል 17:10
23 交叉引用  

ቍጣ​ቸው እንደ እባብ መርዝ ነው፥ ጆሮ​ዋም እንደ ደነ​ቈረ እባብ፥


ሙሴም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘው ነገር ይህ ነው፦ ከግ​ብፅ ምድር በአ​ወ​ጣ​ኋ​ችሁ ጊዜ በም​ድረ በዳ ያበ​ላ​ኋ​ች​ሁን እን​ጀራ ያዩ ዘንድ ከእ​ርሱ አንድ ጎሞር ሙሉ ለልጅ ልጆ​ቻ​ችሁ ይጠ​በቅ” አለ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው እን​ዲሁ ይጠ​በቅ ዘንድ አሮን በም​ስ​ክሩ ፊት አኖ​ረው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ብሎ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና፥ “ሰማይ ስማ፤ ምድ​ርም አድ​ምጪ፤ ልጆ​ችን ወለ​ድሁ፤ አሳ​ደ​ግ​ሁም፤ እነ​ር​ሱም ዐመ​ፁ​ብኝ።


እስ​ራ​ኤል ከጊ​ብዓ ዘመን ጀምሮ ኀጢ​አ​ትን ሠር​ቶ​አል፤ በዚ​ያም ጸን​ተ​ዋል፤ በጊ​ብዓ ላይ ጦር አይ​ደ​ር​ስ​ባ​ቸ​ው​ምን? መጥ​ቶም የዐ​መፅ ልጆ​ችን ገሠ​ጻ​ቸው፤


ሙሴና አሮ​ንም በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ጉባኤ ፊት በግ​ን​ባ​ራ​ቸው ወደቁ።


“ሁሉን በቅ​ጽ​በት አጠ​ፋ​ቸው ዘንድ ከዚህ ማኅ​በር መካ​ከል ፈቀቅ በሉ።”


የእ​ነ​ዚህ ኃጥ​ኣን ጥና​ዎ​ቻ​ቸው በሰ​ው​ነ​ታ​ቸው ጥፋት ተቀ​ድ​ሰ​ዋ​ልና፤ የተ​ጠ​ፈ​ጠፈ ሰሌዳ አድ​ር​ጋ​ቸው፤ ለመ​ሠ​ዊያ መለ​በ​ጫም ይሁኑ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አቅ​ር​በ​ዋ​ቸ​ዋ​ልና የተ​ቀ​ደሱ ናቸው፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ምል​ክት ይሆ​ናሉ።”


እንደ ቆሬና ከእ​ር​ሱም ጋር እንደ ተቃ​ወ​ሙት ሰዎች እን​ዳ​ይ​ሆን፥ ከአ​ሮን ልጆች ያል​ሆነ ሌላ ሰው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ዕጣን ያጥን ዘንድ እን​ዳ​ይ​ቀ​ርብ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሙሴ ቃል እንደ ተና​ገ​ረው፥ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መታ​ሰ​ቢያ አደ​ረ​ጋ​ቸው።


ሙሴና አሮ​ንም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው አደ​ረጉ፤ እን​ዲሁ አደ​ረጉ።


እኔ ለእ​ና​ንተ በም​ገ​ለ​ጥ​በት በዚያ በመ​ገ​ና​ኛው ድን​ኳን ውስጥ በም​ስ​ክሩ ፊት አኑ​ራ​ቸው።


ሙሴም በት​ሮ​ቹን ሁሉ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ወደ እስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ አወ​ጣ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም አዩ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም በት​ሩን ወሰደ።


ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ አዘ​ዘው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የነ​በ​ረ​ች​ውን በት​ሩን ወሰደ።


“የቀ​ዓ​ትን ወገ​ኖች ነገድ ከሌ​ዋ​ው​ያን መካ​ከል አታ​ጥ​ፉ​አ​ቸው፤


ከእ​ነ​ር​ሱም አን​ዳ​ን​ዶቹ እን​ዳ​ን​ጐ​ራ​ጐ​ሩ​በት፥ በመ​ቅ​ሠ​ፍ​ትም እን​ደ​ጠፉ አና​ን​ጐ​ራ​ጕር።


በከ​ንቱ ነገ​ርም የሚ​ያ​ስ​ታ​ችሁ አይ​ኑር፤ በእ​ርሱ ምክ​ን​ያት በከ​ሓ​ዲ​ዎች ልጆች ላይ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መዓት ይመ​ጣ​ልና።


ለእ​ና​ንተ ከታ​ወ​ቀ​በት ቀን ጀምሮ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐመ​ፀ​ኞች ነበ​ራ​ችሁ።


“አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በም​ድረ በዳ ምን ያህል እን​ዳ​ሳ​ዘ​ን​ኸው፥ ከግ​ብፅ ሀገር ከወ​ጣ​ህ​በት ቀን ጀምሮ ወደ​ዚህ ስፍራ እስከ መጣ​ችሁ ድረስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ እን​ዳ​መ​ፃ​ችሁ አስብ፤ አት​ር​ሳም።


በው​ስ​ጥ​ዋም የወ​ርቅ ማዕ​ጠ​ን​ትና ሁለ​ን​ተ​ና​ዋን በወ​ርቅ የለ​በ​ጡ​አት፥ የኪ​ዳን ታቦት፥ መና ያለ​ባት የወ​ርቅ መሶ​ብና የለ​መ​ለ​መ​ችው የአ​ሮን በትር፥ የኪ​ዳ​ኑም ጽላት ነበ​ሩ​ባት።


የካ​ህ​ኑም የዔሊ ልጆች ክፉ​ዎች ነበሩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አያ​ው​ቁም ነበር።


ከዳ​ዊ​ትም ጋር ከሄዱ ሰዎች ክፉ​ዎ​ቹና ዐመ​ፀ​ኞቹ ሁሉ፥ “እነ​ዚህ ከእኛ ጋር አል​መ​ጡ​ምና እየ​ራ​ሳ​ቸው ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንና ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ይዘው ይሂዱ እንጂ ካስ​ጣ​ል​ነው ምርኮ ምንም አን​ሰ​ጣ​ቸ​ውም” አሉ።


跟着我们:

广告


广告