Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 15:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ትው​ልዱ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ቢሆን፥ ወይም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው የሚ​ኖር መጻ​ተኛ ቢሆን፥ ሳያ​ውቅ ኀጢ​አ​ትን ለሚ​ሠራ ሁሉ ሕጉ አንድ ይሆ​ን​ለ​ታል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 ያገር ተወላጅ እስራኤላዊ ይሁን ወይም መጻተኛ ባለማወቅ ኀጢአት ከሠራ በማናቸውም ሰው ላይ ሕጉ እኩል ተፈጻሚነት ይኖረዋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ትውልዱ በእስራኤል ልጆች መካከል ቢሆን፥ ወይም በመካከላቸው የሚቀመጥ መጻተኛ ቢሆን፥ ባለማወቅ ኃጢአትን ለሚሠራ ሁሉ አንድ ዓይነት ሕግ ይኑራችሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 የአገር ተወላጅ እስራኤላዊም ሆነ ወይም በዚያ የሚኖር መጻተኛ ባለማወቅ ኃጢአት የሚሠራ ሁሉ የሚከተለው ሕግ ይኸው ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 ትውልዱ በእስራኤል ልጆች መካከል ቢሆን፥ ወይም በመካከላቸው የሚቀመጥ መጻተኛ ቢሆን፥ ሳያውቅ ኃጢአትን ለሚሠራ ሁሉ ሕጉ አንድ ይሆንለታል።

参见章节 复制




ዘኍል 15:29
12 交叉引用  

“ከሕ​ዝ​ብ​ህም ከእ​ስ​ራ​ኤል ወገን ያል​ሆነ እን​ግዳ ስለ ስምህ ከሩቅ ሀገር ቢመጣ፥


ለሀ​ገር ልጅ፥ በእ​ና​ንተ መካ​ከ​ልም ለሚ​ቀ​መጡ መጻ​ተ​ኞች አንድ ሥር​ዐት ይሆ​ናል።”


“ይህም የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሁ​ን​ላ​ችሁ።


የሞ​ተ​ውን ወይም አውሬ የሰ​በ​ረ​ውን የሚ​በላ ሰው ሁሉ፥ የሀ​ገር ልጅ ወይም እን​ግዳ ቢሆን፥ ልብ​ሱን ያጥ​ባል፤ በው​ኃም ይታ​ጠ​ባል፤ እስከ ማታም ርኩስ ይሆ​ናል፤ ከዚ​ያም በኋላ ንጹሕ ይሆ​ናል።


“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ ማና​ቸ​ውም ሰው ሳያ​ውቅ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ኀጢ​አት ቢሠራ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ አት​ሥሩ ካላ​ቸው ትእ​ዛ​ዛት አን​ዲ​ቱን ቢተ​ላ​ለፍ፥


ለእ​ና​ንተ፥ በእ​ና​ን​ተም መካ​ከል ለሚ​ኖሩ መጻ​ተ​ኞች አንድ ሥር​ዐት ይሆ​ናል፤ ለልጅ ልጃ​ች​ሁም የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሆ​ናል፤ እና​ንተ እንደ ሆና​ችሁ እን​ዲሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት መጻ​ተኛ ይሆ​ናል።


ካህ​ኑም ባለ​ማ​ወቅ ስለ በደ​ለው ያስ​ተ​ሰ​ር​ያል፤ ባለ​ማ​ወ​ቅም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ኀጢ​አት ስለ ሠራው ሰው ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል።


የሀ​ገር ልጅ ቢሆ​ንም ወይም መጻ​ተኛ ቢሆን፥ በእጁ ትዕ​ቢ​ትን የሚ​ያ​ደ​ርግ ሰው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሰድ​ቦ​አል፤ ያም ሰው ከሕ​ዝቡ መካ​ከል ተለ​ይቶ ይጠ​ፋል።


ወደ አገ​ራ​ችሁ መጻ​ተኛ ቢመጣ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፋሲካ እንደ ፋሲ​ካው ሕግ እንደ ትእ​ዛ​ዙም ያድ​ርግ፤ ለመ​ጻ​ተ​ኛና ለሀ​ገር ልጅ አንድ ሥር​ዐት ይሁ​ን​ላ​ችሁ።”


ያላ​ወቀ ግን ባይ​ሠ​ራም ቅጣቱ ጥቂት ነው፤ ብዙ ከሰ​ጡት ብዙ ይፈ​ል​ጉ​በ​ታ​ልና። ጥቂት ከሰ​ጡ​ትም ጥቂት ይፈ​ል​ጉ​በ​ታ​ልና።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ሕዝብ አስ​ቀ​ድሞ ይባ​ር​ኩ​አ​ቸው ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባሪያ ሙሴ እን​ዳ​ዘዘ፥ እስ​ራ​ኤል ሁሉ፥ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም፥ ጸሓ​ፊ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም፥ ፈራ​ጆ​ቻ​ቸ​ውም፥ የሀ​ገሩ ልጆ​ችም፥ መጻ​ተ​ኞ​ችም እኩ​ሌ​ቶቹ በገ​ሪ​ዛን ተራራ አጠ​ገብ፥ እኩ​ሌ​ቶ​ቹም በጌ​ባል ተራራ አጠ​ገብ ሆነው፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦተ ሕግ በተ​ሸ​ከ​ሙት በሌ​ዋ​ው​ያን ካህ​ናት ፊት ለፊት፥ በታ​ቦ​ቱም ፊት በግ​ራና በቀኝ ቆመው ነበር።


跟着我们:

广告


广告