Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 15:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ለእ​ና​ንተ፥ በእ​ና​ን​ተም መካ​ከል ለሚ​ኖሩ መጻ​ተ​ኞች አንድ ሥር​ዐት ይሆ​ናል፤ ለልጅ ልጃ​ች​ሁም የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሆ​ናል፤ እና​ንተ እንደ ሆና​ችሁ እን​ዲሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት መጻ​ተኛ ይሆ​ናል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ማኅበረ ሰቡ ለእናንተም ሆነ በመካከላችሁ ለሚኖር መጻተኛ አንድ ዐይነት ደንብ ይኖረዋል፤ ይህም በሚቀጥሉት ትውልዶች ሁሉ የማይሻር ሥርዐት ነው። እናንተም ሆናችሁ መጻተኞቹ በእግዚአብሔር ፊት እኩል ትታያላችሁ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ለእናንተና በእናንተ መካከል ለሚቀመጥ መጻተኛ ለጉባኤው ሁሉ አንድ ዓይነት ሥርዓት ይኑር፥ ለልጅ ልጃችሁም የዘለዓለም ሥርዓት ይሆናል፤ እናንተ እንደ ሆናችሁት መጻተኛውም በጌታ ፊት እንዲሁ ይሆናል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 እናንተም ሆናችሁ በመካከላችሁ የሚኖሩ መጻተኞች ለሚመጡት ዘመናት ሁሉ እነዚህን የሥርዓት መመሪያዎች በተመሳሳይ ሁኔታ መጠበቅ ይኖርባችኋል፤ እናንተም ሆናችሁ እነርሱ በእግዚአብሔር ፊት አንድ ናችሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ለእናንተ በጉባኤው ላላችሁ በእናንተም መካከል ለሚቀመጥ መጻተኛ አንድ ሥርዓት ይሆናል፥ ለልጅ ልጃችሁም የዘላለም ሥርዓት ይሆናል፤ እናንተ እንደ ሆናችሁ እንዲሁ በእግዚአብሔር ፊት መጻተኛ ይሆናል።

参见章节 复制




ዘኍል 15:15
17 交叉引用  

ይህም ቀን መታ​ሰ​ቢያ ይሁ​ና​ችሁ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዓል ታደ​ር​ጉ​ታ​ላ​ችሁ፤ ለልጅ ልጃ​ች​ሁም ሥር​ዐት ሆኖ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ታደ​ር​ጉ​ታ​ላ​ችሁ።


ለእ​ና​ንተ ለል​ጆ​ቻ​ች​ሁም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይሆ​ና​ችሁ ዘንድ ይህን ሕግ ጠብቁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ​ንና አሮ​ንን አላ​ቸው፥ “ይህ የፋ​ሲካ ሕግ ነው፤ ከእ​ርሱ ባዕድ ሰው አይ​ብላ።


ለሀ​ገር ልጅ፥ በእ​ና​ንተ መካ​ከ​ልም ለሚ​ቀ​መጡ መጻ​ተ​ኞች አንድ ሥር​ዐት ይሆ​ናል።”


እን​ዲ​ሁም ኀጢ​አት እን​ዳ​ይ​ሆ​ን​ባ​ቸው፥ እን​ዳ​ይ​ሞ​ቱም፥ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ሲገቡ፥ በመ​ቅ​ደ​ሱም ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ ወደ መሠ​ዊ​ያው ሲቀ​ርቡ በአ​ሮ​ንና በል​ጆቹ ላይ ይሆ​ናል፤ ለእ​ርሱ፥ ከእ​ር​ሱም በኋላ ለዘሩ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሆ​ናል።


እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና ለመ​ጻ​ተ​ኛና ለሀ​ገር ልጅ አንድ ዐይ​ነት ሕግ ይሁ​ን​ላ​ችሁ።”


የአ​ሮ​ንም ልጆች ካህ​ናቱ መለ​ከ​ቱን ይንፉ፤ ይህም ለልጅ ልጃ​ችሁ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሁ​ን​ላ​ችሁ።


መጻ​ተ​ኛም ከእ​ና​ንተ ጋር ቢቀ​መጥ፥ ወይም በት​ው​ል​ዳ​ችሁ መካ​ከል ማንም ሰው ቢኖር፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን ቍር​ባን በእ​ሳት ቢያ​ቀ​ርብ እና​ንተ የም​ታ​ደ​ር​ጉ​ትን እርሱ እን​ዲሁ ያደ​ር​ጋል።


ትው​ልዱ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ቢሆን፥ ወይም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው የሚ​ኖር መጻ​ተኛ ቢሆን፥ ሳያ​ውቅ ኀጢ​አ​ትን ለሚ​ሠራ ሁሉ ሕጉ አንድ ይሆ​ን​ለ​ታል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አሮ​ንን ተና​ገ​ረው፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “እነሆ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ለእኔ የለ​ዩ​ትን የመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውን ቍር​ባ​ኔን ሁሉ ትጠ​ብቁ ዘንድ ለአ​ንተ ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ፤ ለአ​ንተ እስ​ክ​ታ​ረጅ፥ ከአ​ን​ተም በኋላ ለል​ጆ​ችህ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕግ እን​ዲ​ሆን ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ።


ወደ አገ​ራ​ችሁ መጻ​ተኛ ቢመጣ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፋሲካ እንደ ፋሲ​ካው ሕግ እንደ ትእ​ዛ​ዙም ያድ​ርግ፤ ለመ​ጻ​ተ​ኛና ለሀ​ገር ልጅ አንድ ሥር​ዐት ይሁ​ን​ላ​ችሁ።”


በዚ​ህም አይ​ሁ​ዳዊ፥ ወይም አረ​ማዊ የለም፤ ገዢ፥ ወይም ተገዢ የለም፤ ወንድ፥ ወይም ሴት የለም፤ ሁላ​ችሁ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ አንድ ናች​ሁና።


በእ​ርሱ ዘንድ አይ​ሁ​ዳዊ፥ ግሪ​ካ​ዊም፥ የተ​ገ​ዘረ፥ ያል​ተ​ገ​ዘ​ረም፥ አረ​መ​ኔም፥ ባላ​ገ​ርም፥ ቤተ ሰብ​እና አሳ​ዳሪ ማለት የለም ነገር ግን ክር​ስ​ቶስ ለሁሉ በሁ​ሉም ዘንድ ነው።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ሕዝብ አስ​ቀ​ድሞ ይባ​ር​ኩ​አ​ቸው ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባሪያ ሙሴ እን​ዳ​ዘዘ፥ እስ​ራ​ኤል ሁሉ፥ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም፥ ጸሓ​ፊ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም፥ ፈራ​ጆ​ቻ​ቸ​ውም፥ የሀ​ገሩ ልጆ​ችም፥ መጻ​ተ​ኞ​ችም እኩ​ሌ​ቶቹ በገ​ሪ​ዛን ተራራ አጠ​ገብ፥ እኩ​ሌ​ቶ​ቹም በጌ​ባል ተራራ አጠ​ገብ ሆነው፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦተ ሕግ በተ​ሸ​ከ​ሙት በሌ​ዋ​ው​ያን ካህ​ናት ፊት ለፊት፥ በታ​ቦ​ቱም ፊት በግ​ራና በቀኝ ቆመው ነበር።


ከዚ​ያም ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ይህ ለእ​ስ​ራ​ኤል ሥር​ዐ​ትና ሕግ ሆነ።


跟着我们:

广告


广告