Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 14:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 ንጥ​ቂያ ይሆ​ናሉ ያላ​ች​ኋ​ቸ​ውን ልጆ​ቻ​ች​ሁን እነ​ር​ሱን አገ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም የና​ቃ​ች​ኋ​ትን ምድር ይወ​ር​ሷ​ታል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 ይማረካሉ ያላችኋቸውን ልጆቻችሁን ግን አገባቸዋለሁ፤ እናንተ የናቃችኋትን ምድር እነርሱ ይደሰቱባታል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ነገር ግን ምርኮኛ ይሆናሉ ያላችኋቸውን ልጆቻችሁን እነርሱን ወደ ምድሪቱ አስገባቸዋለሁ፥ እናንተም የናቃችኋትን ምድር ያውቋታል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 ልጆቻችን ምርኮኞች ሆነው ይቀራሉ ብላችሁ የተናገራችሁባቸውን እነርሱን እናንተ ወደናቃችኋት ምድር አገባቸዋለሁ፤ ርስታቸውም ትሆናለች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 ምርኮኛ ይሆናሉ ያላችኋቸውን ልጆቻችሁን እነርሱን አገባቸዋለሁ፥ እናንተም የናቃችኋትን ምድር ያውቃሉ።

参见章节 复制




ዘኍል 14:31
14 交叉引用  

ያዕ​ቆ​ብም ለዔ​ሳው እን​ጀ​ራና የም​ስር ንፍሮ ሰጠው፤ በላ፥ ጠጣ፥ ተነ​ሥ​ቶም ሄደ፤ ዔሳ​ውም ብኵ​ር​ና​ውን አቃ​ለ​ላት።


እነ​ር​ሱም ወረ​ሱ​አት፤ በከ​ነ​ዓን ምድር የሚ​ኖ​ሩ​ት​ንም ሰዎች በፊ​ታ​ቸው አጠ​ፋ​ሃ​ቸው፤ የሚ​ወ​ድ​ዱ​ት​ንም ነገር ያደ​ር​ጉ​ባ​ቸው ዘንድ እነ​ር​ሱ​ንና ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን፥ የም​ድ​ሩ​ንም አሕ​ዛብ በእ​ጃ​ቸው አሳ​ል​ፈህ ሰጠ​ሃ​ቸው።


እነ​ርሱ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ፥ በጥ​ል​ቅም ያለ​ች​ውን ድን​ቁን ዐወቁ።


“ምክሬን ሁሉ ናቃችሁ፥ ዘለፋዬንም አልተመለከታችሁም፥


ምክሬን ይመለከቱ ዘንድ አልፈቀዱምና፥ ዘለፋዬንም ሁሉ ንቀዋልና፤


“ለል​ጆ​ቻ​ቸ​ውም በም​ድረ በዳ እን​ዲህ አል​ኋ​ቸው፦ በአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ልማድ አት​ሂዱ፤ ሥር​ዐ​ታ​ቸ​ው​ንም አት​ጠ​ብቁ፤ በበ​ደ​ላ​ቸ​ውም አንድ አት​ሁኑ፤ አት​ር​ከ​ሱም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጦ​ር​ነት እን​ሞት ዘንድ ወደ​ዚች ምድር ለምን ያገ​ባ​ናል? ሴቶ​ቻ​ች​ንና ልጆ​ቻ​ችን ለን​ጥ​ቂያ ይሆ​ናሉ፤ አሁ​ንም ወደ ግብፅ መመ​ለስ አይ​ሻ​ለ​ን​ምን?” አሉ​አ​ቸው።


ከአ​ስ​ሮን የአ​ስ​ሮ​ና​ው​ያን ወገን፤ ከከ​ርሚ የከ​ር​ማ​ው​ያን ወገን።


ነገር ግን ሙሴና ካህኑ አሮን በሲና ምድረ በዳ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በቈ​ጠ​ሩ​አ​ቸው ጊዜ ከነ​በ​ሩት ከእ​ነ​ዚያ መካ​ከል አን​ድም ሰው አል​ነ​በ​ረም።


እነርሱ ግን ቸል ብለው አንዱ ወደ እርሻው፥ ሌላውም ወደ ንግዱ ሄደ፤


‘እነሆ፥ እና​ንተ የም​ታ​ቃ​ልሉ፥ እዩ፤ ተደ​ነ​ቁም፤ ያለ​ዚያ ግን ትጠ​ፋ​ላ​ችሁ፤ ማንም ቢነ​ግ​ራ​ችሁ የማ​ታ​ም​ኑ​ትን ሥራ እኔ በዘ​መ​ና​ችሁ እሠ​ራ​ለ​ሁና።’ ”


ደግሞ፦ ይማ​ረ​ካሉ ያላ​ች​ኋ​ቸው ልጆ​ቻ​ችሁ፥ ዛሬም መል​ካ​ሙን ከክፉ መለ​የት የማ​ይ​ችሉ ሕፃ​ኖ​ቻ​ችሁ እነ​ርሱ ወደ​ዚያ ይገ​ባሉ፤ ምድ​ሪ​ቱ​ንም ለእ​ነ​ርሱ እሰ​ጣ​ለሁ፤ ይወ​ር​ሱ​አ​ታ​ልም።


ልጆ​ቻ​ቸ​ውን በእ​ነ​ርሱ ፋንታ አስ​ነሣ፤ እነ​ዚ​ህ​ንም ኢያሱ ገረ​ዛ​ቸው፤ በመ​ን​ገድ ስለ​ተ​ወ​ለዱ አል​ተ​ገ​ረ​ዙም ነበ​ርና።


跟着我们:

广告


广告