ዘኍል 14:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)23 በእውነት ለአባቶቻቸው የማልሁላቸውን ምድር አያዩም፤ ከእኔ ጋር በዚህ ላሉ መልካምንና ክፉን ለይተው ለማያውቁ ልጆቻቸው፥ የሚያውቀው ለሌለ ለታናሹ ሁሉ ያችን ሀገር እሰጣታለሁ፤ ለጥፋት ያነሳሱኝ ሁሉ አያዩአትም። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም23 ለአባቶቻቸው እሰጣቸው ዘንድ በመሐላ ቃል የገባሁላቸውን ምድር አያዩዋትም። የናቀኝ ማንኛውም ሰው ፈጽሞ አያያትም፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)23 በእውነት ለአባቶቻቸው የማልሁላቸውን ምድር አያዩም፥ እነዚህም የናቁኝ ሰዎች ሁሉ አያይዋትም፤ 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም23 ስለዚህ ለቀድሞ አባቶቻቸው ልሰጣቸው ቃል ወደገባሁላቸው ምድር በፍጹም አይገቡም፤ እኔን ከናቁኝ ሰዎች መካከል አንድ እንኳ ወደዚያች ምድር ከቶ አይገባም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)23 ነገሬንም ስላልሰሙ፥ በእውነት ለአባቶቻቸው የማልሁላቸውን ምድር አያዩም፤ ከእነርሱም የናቀኝ ሰው ሁሉ አያያትም፤ 参见章节 |