Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 13:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ነገር ግን በም​ድ​ሪቱ የሚ​ኖሩ ሰዎች ኀያ​ላን ናቸው፤ ከተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም የተ​መ​ሸጉ፥ እጅ​ግም የጸኑ ታላ​ላቅ ናቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 በዚያ የሚኖሩት ሰዎች ግን ኀያላን ሲሆኑ፣ ከተሞቹም የተመሸጉና ትላልቅ ናቸው፤ እንዲያውም የዔናቅን ዝርያዎች በዚያ አይተናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ነገር ግን በምድሪቱ የሚኖሩ ሰዎች ኃያላን ናቸው፤ ከተሞቻቸውም የተመሸጉ እጅግም ሰፋፊዎች ናቸው፤ ደግሞም በዚያ የዔናቅን ልጆች አየን።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ነገር ግን በዚያች ምድር የሚኖሩ ሕዝብ እጅግ ብርቱዎች ናቸው፤ ከተሞቻቸውም ታላላቆችና የተመሸጉ ናቸው፤ ከዚህም ሁሉ በላይ እጅግ ግዙፋን የዐናቅ ዘሮች አይተናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ነገር ግን በምድሪቱ የሚኖሩ ሰዎች ኃያላን ናቸው። ከተሞቻቸውም የተመሸጉ እጅግም የጸኑ ናቸው፤ ደግሞም በዚያ የዔናቅን ልጆች አየን።

参见章节 复制




ዘኍል 13:28
12 交叉引用  

ከራ​ፋ​ይም ወገን የነ​በ​ረው ኤስቢ መጣ፤ የጦ​ሩም ሚዛን ክብ​ደት ሦስት መቶ ሰቅል ናስ ነበር። አዲስ የጦር መሣ​ሪ​ያም ታጥቆ ነበር፤ ዳዊ​ት​ንም ሊገ​ድ​ለው ፈለገ።


በዚ​ያም ግዙ​ፋን የሆ​ኑ​ትን አየን፤ እኛም በእ​ነ​ርሱ ፊት እንደ አን​በ​ጣ​ዎች ሆን፤ እን​ዲ​ሁም በፊ​ታ​ቸው ነበ​ርን፤” እያሉ የሰ​ለ​ሉ​አ​ትን ምድር ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አስ​ፈሪ አደ​ረ​ጓት።


ወዴት እን​ወ​ጣ​ለን? ሕዝቡ ታላ​ቅና ብዙ ነው፤ ከእ​ኛም ይጠ​ነ​ክ​ራሉ፤ ከተ​ሞ​ቹም ታላ​ላ​ቆች፥ የተ​መ​ሸ​ጉም፥ እስከ ሰማ​ይም የደ​ረሱ ናቸው፤ የረ​ዐ​ይ​ት​ንም ልጆች ደግሞ በዚያ አየ​ና​ቸው ብለው ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ልባ​ች​ንን አስ​ፈ​ሩት።’


እነ​ር​ሱም እንደ ዔና​ቃ​ው​ያን ታላ​ቅና ብዙ፥ ጽኑ​ዓ​ንም ሕዝብ ነበሩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከፊ​ታ​ቸው አጠ​ፋ​ቸው፤ እነ​ር​ሱ​ንም አሳ​ድ​ደው በስ​ፍ​ራ​ቸው ተቀ​መጡ።


እጅግ ብዙ ከሆ​ኑት ከፌ​ር​ዜ​ዎን ከተ​ሞች ሌላ፥ እነ​ዚህ ከተ​ሞች ሁሉ ቁመቱ ረዥም በሆነ ቅጥር በመ​ዝ​ጊ​ያና በመ​ወ​ር​ወ​ሪ​ያም የተ​መ​ሸጉ ነበሩ።


በጋዛ፥ በጌ​ትም፥ በአ​ዛ​ጦ​ንም ከቀ​ሩት በቀር በእ​ስ​ራ​ኤል መካ​ከል ከኤ​ና​ቃ​ው​ያን ማን​ንም አላ​ስ​ቀ​ረም።


አሁን እን​ግ​ዲህ በዚያ ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ረ​ውን ይህን ተራ​ራማ ሀገር ስጠኝ፤ አንተ በዚያ ቀን ዔና​ቃ​ው​ያን፥ ታላ​ላ​ቆ​ችና የተ​መ​ሸጉ ከተ​ሞ​ችም በዚያ እን​ዳሉ ሰም​ተህ ነበር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእኔ ጋር ቢሆን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተና​ገ​ረኝ አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ።”


የዮ​ፎኒ ልጅ ካሌ​ብም ሦስ​ቱን የዔ​ና​ቅን ልጆች ሱሲን፥ ተለ​ሚ​ንና አካ​ሚን ከዚያ አጠ​ፋ​ቸው።


ሙሴም እንደ ተና​ገረ ለካ​ሌብ ኬብ​ሮ​ንን ሰጡት፤ ከዚ​ያም ሠላሳ ከተ​ሞ​ችን ወረሰ፤ ከዚ​ያም ሦስ​ቱን የዔ​ናቅ ልጆች አስ​ወ​ገ​ዳ​ቸው።


跟着我们:

广告


广告