Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 11:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ከእ​ስ​ራ​ኤል ሽማ​ግ​ሌ​ዎች፥ ለሕ​ዝቡ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና ጸሐ​ፍት ይሆኑ ዘንድ የም​ታ​ው​ቃ​ቸ​ውን፥ ሰባ ሰዎች ሰብ​ስ​ብ​ልኝ፤ ወደ ምስ​ክ​ሩም ድን​ኳን አም​ጣ​ቸው፤ በዚ​ያም ከአ​ንተ ጋር አቁ​ማ​ቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “በሕዝቡ መካከል በመሪነትና በእልቅና ብቃት አላቸው የምትላቸውን ሰባ የእስራኤል ሽማግሌዎች አምጣልኝ፤ ካንተም ጋራ ይቆሙ ዘንድ ወደ መገናኛው ድንኳን እንዲመጡ አድርግ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “በሕዝቡ ላይ ሽማግሌዎችና አለቆች እንደ ሆኑ የምታውቃቸውን የእስራኤል ሽማግሌዎች የሆኑ ሰባ ሰዎች ሰብስብልኝ፤ እነርሱንም ወደ መገናኛው ድንኳን አምጣቸው፥ በዚያም ከአንተ ጋር በየቦታቸው ይቁሙ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ለሕዝብ አመራር በመስጠት የታወቁ ሰባ ሽማግሌዎችን ምረጥ፤ እነርሱንም ሰብስበህ ወደ መገናኛው ድንኳን አምጣቸውና በአጠገብህ ይቁሙ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ ከእስራኤል ሽማግሌዎች፥ በሕዝቡ ላይ ሽማግሌዎችና አለቆች ይሆኑ ዘንድ የምታውቃቸውን፥ ሰባ ሰዎች ሰብስብልኝ፥ ወደ መገናኛውም ድንኳን አምጣቸው፥ በዚያም ከአንተ ጋር አቁማቸው።

参见章节 复制




ዘኍል 11:16
14 交叉引用  

በግ​ብፅ ምድር የተ​ወ​ለ​ዱ​ለት የዮ​ሴ​ፍም ልጆች ሁለት ናቸው፤ ወደ ግብፅ የገ​ቡት የያ​ዕ​ቆብ ቤተ ሰዎች ሁሉ ሰባ ናቸው።


ሙሴም ከእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ችሎታ ያላ​ቸ​ውን ሰዎች መረጠ፤ በሕ​ዝ​ቡም ላይ የሺህ አለ​ቆች፥ የመቶ አለ​ቆች፥ የአ​ም​ሳም አለ​ቆች፥ የዐ​ሥ​ርም አለ​ቆች አድ​ርጎ ሾማ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “አንተ፥ አሮ​ንም፥ ናዳ​ብም፥ አብ​ዩ​ድም፥ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰባ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ውጡ፤ በሩ​ቁም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስገዱ፤


ሙሴም፥ አሮ​ንም፥ ናዳ​ብም፥ አብ​ዩ​ድም፥ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰባ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ወጡ፤


ሙሴና አሮ​ንም ሄዱ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሁሉ ሰበ​ሰቡ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አለኝ፥ “ሂድ፤ የሸ​ክላ ሠሪ የሠ​ራ​ውን ገምቦ ግዛ፤ ከሕ​ዝ​ቡም ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና ከካ​ህ​ናት ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ከአ​ንተ ጋር ውሰድ፤


በፊ​ታ​ቸ​ውም ከእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሰባ ሰዎ​ችና የሳ​ፋን ልጅ ያእ​ዛ​ንያ ቆመው ነበር፤ ሰውም ሁሉ እያ​ን​ዳ​ንዱ በእጁ ጥና​ውን ይዞ ነበር፥ የዕ​ጣ​ኑም ጢስ ሽታ ይወጣ ነበር።


ሙሴም ወጣ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃሎች ለሕ​ዝቡ ነገረ፤ ከሕ​ዝቡ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችም ሰባ​ውን ሰዎች ሰብ​ስቦ በድ​ን​ኳኑ ዙሪያ አቆ​ማ​ቸው።


ሙሴም ተነ​ሥቶ ወደ ዳታ​ንና ወደ አቤ​ሮን ሄደ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሁሉ ከእ​ርሱ ጋር ሄዱ።


ከዚ​ህም በኋላ ጌታ​ችን ሌሎች ሰባ ሰዎ​ችን መረጠ፤ ሁለት ሁለት አድ​ር​ጎም ሊሄ​ድ​በት ወደ አለው ከተ​ማና መን​ደር በፊቱ ላካ​ቸው።


እነ​ዚ​ያም ሰባው ደስ ብሎ​አ​ቸው ተመ​ለ​ሱና፥ “አቤቱ፥ አጋ​ን​ንት ስንኳ በስ​ምህ ተገ​ዙ​ልን” አሉት።


ከእ​ና​ን​ተም ጥበ​በ​ኞ​ችና ዐዋ​ቂ​ዎች፥ አስ​ተ​ዋ​ዮ​ችም የሆ​ኑ​ትን ሰዎች ወሰ​ድሁ፤ በእ​ና​ን​ተም ላይ አለ​ቆች፥ የሻ​ለ​ቆ​ችም፥ የመቶ አለ​ቆ​ችም፥ የአ​ምሳ አለ​ቆ​ችም፥ የዐ​ሥር አለ​ቆ​ችም፥ ለፈ​ራ​ጆ​ቻ​ች​ሁም ጻፎች አድ​ርጌ ሰየ​ም​ኋ​ቸው።


“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሚ​ሰ​ጥህ በሀ​ገ​ርህ ደጅ ሁሉ በየ​ነ​ገ​ዶ​ችህ ፈራ​ጆ​ች​ንና መባ​ውን የሚ​ጽ​ፉ​ትን ሹሙ፤ ለሕ​ዝ​ቡም ቅን ፍር​ድን ይፍ​ረዱ።


ይህን ቃል በጆ​ሮ​አ​ቸው እነ​ግር ዘንድ፥ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ር​ንም አስ​መ​ሰ​ክ​ር​ባ​ቸው ዘንድ የነ​ገ​ዶ​ቻ​ች​ሁን አለ​ቆች፥ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቻ​ች​ሁን ሁሉ፥ ሹሞ​ቻ​ች​ሁ​ንም፥ ጻፎ​ቻ​ች​ሁ​ንም ሰብ​ስ​ቡ​ልኝ፤


跟着我们:

广告


广告