Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 10:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ከሠ​ራ​ዊቱ ሁሉ በኋላ የዳን ልጆች ሰፈር በሥ​ር​ዐ​ታ​ቸው ከየ​ሠ​ራ​ዊ​ታ​ቸው ጋር ተጓዘ፤ በሠ​ራ​ዊ​ቱም ላይ የአ​ሚ​ሳዲ ልጅ አኪ​ያ​ዜር አለቃ ነበረ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 በመጨረሻም የዳን ሰፈር ሰራዊት ለሁሉም ክፍሎች የኋላ ደጀን በመሆን በዐርማቸው ሥር ተጓዙ፤ አለቃቸውም የአሚሳዳይ ልጅ አኪዔዘር ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ሰፈሮቹንም ሁሉ ከኋላ ሆኖ የሚጠብቀው የዳን ልጆች ሰፈር ዓላማ በየሠራዊታቸው ተጓዘ፤ በሠራዊቱም ላይ የአሚሳዳይ ልጅ አኪዔዘር አለቃ ነበረ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 በመጨረሻም በዳን ነገድ ቡድን ሰንደቅ ዓላማ ሥር የሚገኙትና ለሁሉም ክፍሎች ደጀን የሚሆኑት በዓሚሻዳይ ልጅ በአሒዔዜር መሪነት የቡድን ተራቸውን ጠብቀው ተጓዙ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ከሰፈሮቹ ሁሉ በኋላ የሆነ የዳን ልጆች ሰፈር ዓላማ በየሠራዊታቸው ተጓዘ፤ በሠራዊቱም ላይ የአሚሳዳይ ልጅ አኪዔዘር አለቃ ነበረ።

参见章节 复制




ዘኍል 10:25
12 交叉引用  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፊ​ታ​ችሁ ይሄ​ዳ​ልና፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ይሰ​በ​ስ​ባ​ች​ኋ​ልና በች​ኮላ አት​ወ​ጡም፤ በመ​ኮ​ብ​ለ​ልም አት​ሄ​ዱም።


ያን ጊዜ ብር​ሃ​ንህ እንደ ንጋት ይበ​ራል፤ ፈው​ስ​ህም ፈጥኖ ይወ​ጣል፤ ጽድ​ቅ​ህም በፊ​ትህ ይሄ​ዳል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ይጋ​ር​ድ​ሃል።


ከዳን የአ​ሚ​ሳዲ ልጅ አክ​ያ​ዚር፥


በብ​ን​ያ​ምም ልጆች ነገድ ሠራ​ዊት ላይ የጋ​ዲ​ዮን ልጅ አቢ​ዳን አለቃ ነበረ።


በአ​ሴ​ርም ልጆች ነገድ ሠራ​ዊት ላይ የኤ​ክ​ራን ልጅ ፋግ​ኤል አለቃ ነበረ።


በዐ​ሥ​ረ​ኛ​ውም ቀን የዳን ልጆች አለቃ የአ​ሚ​ሳዲ ልጅ አኪ​ያ​ዜር መባ​ውን አቀ​ረበ፤


ሰባ​ቱም ካህ​ናት ሰባ​ቱን ቀንደ መለ​ከት ይዘው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ፊት ይሄዱ ነበር፤ ቀንደ መለ​ከ​ቱ​ንም ይነፉ ነበር፤ ተዋ​ጊ​ዎ​ችም በፊ​ታ​ቸው ይሄዱ ነበር፤ የቀ​ሩ​ትም ሕዝብ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቃል ኪዳን ታቦት በኋላ ይሄዱ ነበር፤ ካህ​ና​ቱም ቀንደ መለ​ከ​ቱን ይነፉ ነበር።


ሰል​ፈ​ኞ​ችም ፊት ፊት ይሄዱ ነበር፤ ካህ​ና​ቱም ነጋ​ሪት ይመቱ ነበር፤ ከታ​ቦቱ በኋላ ይከ​ተሉ የነ​በ​ሩ​ትም ቀንደ መለ​ከ​ቱን እየ​ነፉ ይሄዱ ነበር።


跟着我们:

广告


广告