Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ነህምያ 9:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 ነገር ግን አንተ ኀያል፥ ቸርና መሓሪ አም​ላክ ነህና በም​ሕ​ረ​ትህ ብዛት ፈጽ​መህ አላ​ጠ​ፋ​ሃ​ቸ​ውም፤ አል​ተ​ው​ሃ​ቸ​ው​ምም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 አንተ ግን ቸርና መሓሪ አምላክ ነህና ከምሕረትህ ብዛት የተነሣ፣ ፈጽመህ አላጠፋሃቸውም፤ አልተውሃቸውምም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ነገር ግን አንተ ቸርና መሐሪ አምላክ ነህና በምሕረትህ ብዛት ፈጽመህ አላጠፋሃቸውም፥ አልተውካቸውምም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 እንደገናም ከምሕረትህ ታላቅነት የተነሣ አልተውካቸውም፤ አንተ ቸርና ይቅር ባይ አምላክም ስለ ሆንክ አልደመሰስካቸውም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 ነገር ግን አንተ ቸርና መሐሪ አምላክ ነህና በምሕረትህ ብዛት ፈጽመህ አላጠፋሃቸውም፥ አልተውሃቸውምም።

参见章节 复制




ነህምያ 9:31
15 交叉引用  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ራራ​ላ​ቸው፤ ማራ​ቸ​ውም፤ ከአ​ብ​ር​ሃ​ምና ከይ​ስ​ሐቅ፥ ከያ​ዕ​ቆ​ብም ጋር ስላ​ደ​ረ​ገው ቃል ኪዳን እነ​ር​ሱን ተመ​ለ​ከተ፤ ሊያ​ጠ​ፋ​ቸ​ውም አል​ወ​ደ​ደም፤ ፈጽ​ሞም ከፊቱ አል​ጣ​ላ​ቸ​ውም።


አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቸርና መሓሪ ነውና፥ ወደ እር​ሱም ብን​መ​ለስ ፊቱን ከእኛ አያ​ዞ​ር​ምና ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብት​መ​ለሱ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁና ልጆ​ቻ​ችሁ በማ​ረ​ኩ​አ​ቸው ፊት ምሕ​ረ​ትን ያገ​ኛሉ፤ ደግ​ሞም ወደ​ዚ​ህች ምድር ይመ​ል​ሳ​ቸ​ዋል።”


ለመ​ስ​ማ​ትም እንቢ አሉ፤ ያደ​ረ​ግ​ህ​ላ​ቸ​ው​ንም ተአ​ም​ራት አላ​ሰ​ቡም፤ አን​ገ​ታ​ቸ​ው​ንም አደ​ነ​ደኑ፤ ለባ​ር​ነ​ታ​ቸ​ውም ወደ ግብፅ ይመ​ለሱ ዘንድ አለ​ቃን ሾሙ፤ አንተ ግን መሓ​ሪና ይቅር ባይ አም​ላክ፥ ለቍ​ጣም የም​ት​ዘ​ገይ፥ ምሕ​ረ​ት​ንም የም​ታ​በዛ ነህ፤ አል​ተ​ው​ሃ​ቸ​ውም።


አንተ ግን ምሕ​ረ​ትህ ብዙ ነውና በም​ድረ በዳ አል​ተ​ው​ሃ​ቸ​ውም፤ በመ​ን​ገ​ድም ይመ​ራ​ቸው ዘንድ የደ​መና ዓም​ድን በቀን፥ የሚ​ሄ​ዱ​በ​ት​ንም መን​ገድ ያበ​ራ​ላ​ቸው ዘንድ የእ​ሳት ዓም​ድን በሌ​ሊት ከእ​ነ​ርሱ አላ​ራ​ቅ​ህም።


ስለ ስሜ ቍጣ​ዬን አሳ​ይ​ሃ​ለሁ፤ እን​ዳ​ላ​ጠ​ፋ​ህም ግር​ማ​ዬን አመ​ጣ​ብ​ሃ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ ይላል፦ ምድር ሁሉ ባድማ ትሆ​ና​ለች፤ ነገር ግን ፈጽሜ አላ​ጠ​ፋ​ትም።


“ወደ ቅጥ​ርዋ ወጥ​ታ​ችሁ አፍ​ርሱ፤ ነገር ግን ፈጽ​ማ​ችሁ አታ​ጥፉ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ናቸ​ውና መጠ​ጊ​ያ​ዎ​ች​ዋን አት​ርፉ።


ነገር ግን “በዚያ ዘመን ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ፈጽሜ አላ​ጠ​ፋ​ች​ሁም።”


ሔት። ያል​ጠ​ፋ​ነው ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምሕ​ረት የተ​ነሣ ነው፤ ርኅ​ራ​ኄው አያ​ል​ቅ​ምና።


አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሓሪ አም​ላክ ነውና አይ​ተ​ው​ህም፤ አያ​ጠ​ፋ​ህ​ምም፤ ለአ​ባ​ቶ​ች​ህም የማ​ለ​ላ​ቸ​ውን ቃል ኪዳ​ኑን አይ​ረ​ሳም።


跟着我们:

广告


广告