Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ነህምያ 8:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ዕዝ​ራም አላ​ቸው፥ “ወደ ተራራ ሂዱ፤ የዘ​ይ​ትና የበ​ረሃ ወይራ፥ የባ​ር​ሰ​ነ​ትም፥ የዘ​ን​ባ​ባም፥ የለ​መ​ለ​መ​ው​ንም ዛፍ ቅር​ን​ጫፍ አምጡ፤ እንደ ተጻ​ፈ​ውም ዳሶ​ችን ሥሩ።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ስለዚህ በየከተሞቻቸውና በኢየሩሳሌም ይህን ቃል እንዲያውጁና እንዲያሠራጩ እንዲህ በማለት አዘዟቸው፤ “ወደ ኰረብቶች ውጡ፤ ከዘይትና ከበረሓ ወይራ፣ ከባርሰነት፣ ከዘንባባና ከለምለም ዛፎች ቅርንጫፎችን አምጡ፤ በተጻፈው መሠረት ዳሶችን ሥሩ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 በከተሞቻቸው ሁሉና በኢየሩሳሌምም፦ “እንደተጻፈው ዳሶችን ለመስራት ወደ ተራራ ውጡ፥ የዘይትና የበረሀ ወይራ፥ የባርሰነት፥ የዘንባባና የለመለመውን ዛፍ ቅርንጫፍ አምጡ” ብለው ይናገሩና ያውጁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 የዳስን በዓል በተመለከተ ሕጉ በሚያዝዘው መሠረት ወደ ተራራማው አገር ሄደው የወይራ ዘይት ዛፍና የዱር ወይራ ቅርንጫፎችን የባርሰነትና የዘንባባ ቅርንጫፎችን ለማምጣት በየከተማውና በኢየሩሳሌም አካባቢ እንዲሄዱ አዘዙአቸው።

参见章节 复制




ነህምያ 8:15
9 交叉引用  

ርግ​ብም በማታ ጊዜ ወደ እርሱ ተመ​ለ​ሰች፤ በአ​ፍ​ዋም እነሆ፥ የለ​መ​ለመ የወ​ይራ ቅጠል ይዛ ነበር። ኖኅም ከም​ድር ላይ ውኃው እንደ ጐደለ ዐወቀ።


እነ​ዚህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዓ​ላት፥ በየ​ዘ​መ​ና​ቸው የም​ታ​ው​ጁ​አ​ቸው፥ የተ​ቀ​ደሱ ጉባ​ኤ​ያት ናቸው።


በመ​ጀ​መ​ሪ​ያዋ ቀን የመ​ል​ካም ዛፍ ፍሬ፥ የዘ​ን​ባ​ባ​ው​ንም ቅር​ን​ጫፍ፥ የለ​መ​ለ​መ​ው​ንም ዛፍ ቅር​ን​ጫፍ፥ የወ​ን​ዝም አኻያ ዛፍ ውሰዱ፤ በአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በየ​ዓ​መቱ ሰባት ቀን ደስ ይበ​ላ​ችሁ።


እነሆም፥ አንድ ሰው በመጋላ ፈረስ ተቀምጦ በሌሊት አየሁ፥ እርሱም በሸለቆው ውስጥ ባሉ በባርሰነት ዛፎች መካከል ቆሞ ነበር፣ በስተ ኋላውም መጋላና ሐመር አንባላይም ፈረሶች ነበሩ።


ወደ ኢየሩሳሌምም ቀርበው ወደ ደብረዘይት ወደ ቤተ ፋጌ ሲደርሱ፥ ያን ጊዜ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለት ላከ፤


የዘ​ን​ባባ ዛፍ ዝን​ጣፊ ይዘው “ሆሣ​ዕና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም የሚ​መጣ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ቡሩክ ነው” እያሉ ወጥ​ተው ተቀ​በ​ሉት።


በዓ​መት ሦስት ጊዜ በቂጣ በዓል፥ በሰ​ባቱ ሱባ​ዔም በዓል፥ በዳ​ስም በዓል ወንድ ልጅህ ሁሉ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ረ​ጠው ስፍራ ይታይ፤


ከዚህ በኋላ አየሁ፤ እነሆም አንድ እንኳ ሊቆጥራቸው የማይችል ከሕዝብና ከነገድ ከወገንም ከቋንቋም ሁሉ እጅግ ብዙ ሰዎች ነበሩ፤ ነጭ ልብስም ለብሰው የዘንባባንም ዝንጣፊዎች በእጆቻቸው ይዘው በዙፋኑና በበጉ ፊት ቆሙ፤


跟着我们:

广告


广告