Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ነህምያ 8:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ሕዝ​ቡም ሁሉ የተ​ነ​ገ​ራ​ቸ​ውን ቃል አስ​ተ​ው​ለ​ዋ​ልና ሊበ​ሉና ሊጠጡ፥ እድል ፈን​ታም ሊልኩ፥ ደስ​ታም ሊያ​ደ​ርጉ ሄዱ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ስለዚህ ሕዝቡ ሁሉ የተነገራቸውን ቃል ተረድተው ስለ ነበረ፣ ለመብላት፣ ለመጠጣት፣ ከምግባቸው ከፍለው ለመላክና ሐሤትም ለማድረግ ሄዱ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ሕዝቡም ሁሉ ሊበሉ፥ ሊጠጡ፥ ለሌላቸው ድርሻቸውን ሊልኩና ታላቅ ደስታ ሊያደርጉ ሄዱ፤ የተነገራቸውን ቃል ማስተዋል ችለው ነበርና።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 የተነበበላቸውን ቃል ትርጒም በሚገባ ተረድተው ስለ ነበር ሕዝቡ ሁሉ ወደየቤታቸው ሄደው በመብላትና በመጠጣት እጅግ ተደሰቱ፤ ያላቸውንም ምግብ ከሌሎቹ ጋር አብረው ተካፈሉ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ሕዝቡም ሁሉ የተነገረላቸውን ቃል አስተውለዋልና ሊበሉና ሊጠጡ እድል ፈንታም ሊሰድዱ ደስታም ሊያደርጉ ሄዱ።

参见章节 复制




ነህምያ 8:12
25 交叉引用  

በዚ​ያም ቀን በታ​ላቅ ደስታ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በሉ፥ ጠጡም። የዳ​ዊ​ት​ንም ልጅ ሰሎ​ሞ​ንን ሁለ​ተኛ ጊዜ አነ​ገ​ሡት፤ እር​ሱ​ንም ንጉሥ ይሆን ዘንድ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀቡት፤ ሳዶ​ቅም በካ​ህ​ናት ላይ ተሾመ።


እር​ሱም፥ “ሂዱ፤ የሰ​ባ​ው​ንም ብሉ፤ ጣፋ​ጩ​ንም ጠጡ፤ ለእ​ነ​ዚ​ያም ምንም ለሌ​ላ​ቸው እድል ፈን​ታ​ቸ​ውን ላኩ፤ ዛሬ ለጌ​ታ​ችን የተ​ቀ​ደሰ ቀን ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኀይ​ላ​ችን ነውና አት​ዘኑ” አላ​ቸው።


ሌዋ​ው​ያ​ንም “ቀኑ የተ​ቀ​ደሰ ነውና ዝም በሉ፤ አት​ዘ​ኑም” እያሉ ሕዝ​ቡን ሁሉ ጸጥ ያደ​ርጉ ነበር።


በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ቀን ከሕ​ዝቡ ሁሉ የአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች፥ ካህ​ና​ቱም፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑም የሕ​ጉን ቃል ይተ​ረ​ጕ​ም​ላ​ቸው ዘንድ ወደ ጸሓ​ፊው ወደ ዕዝራ ተሰ​በ​ሰቡ።


ከት​እ​ዛ​ዙም አላ​ለ​ፍ​ሁም፤ ቃሉን በልቤ ሰው​ሬ​አ​ለሁ።


ቃልህ ተገ​ኝ​ቶ​አል፤ እኔም በል​ች​ዋ​ለሁ፤ አቤቱ! የሠ​ራ​ዊት አም​ላክ ሆይ! ቃል​ህን የከዱ ሰዎ​ችን አጥ​ፋ​ቸው፤ ስምህ በእኔ ላይ ተጠ​ር​ት​ዋ​ልና፥ ቃልህ ሐሤ​ትና የልብ ደስታ ሆነኝ።


እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም እን​ዲህ አሉ፥ “በመ​ን​ገድ ሲነ​ግ​ረን፥ መጻ​ሕ​ፍ​ት​ንም ሲተ​ረ​ጕ​ም​ልን ልባ​ችን ይቃ​ጠ​ል​ብን አል​ነ​በ​ረ​ምን?”


በእኔ ማለት በሥ​ጋዬ መል​ካም ነገር እን​ደ​ማ​ይ​ኖር አው​ቃ​ለሁ፤ መል​ካም ሥራ ለመ​ሥ​ራት መሻ​ቱስ በእኔ ዘንድ አለ፤ በጎ ምግ​ባር መሥ​ራት ግን የለ​ኝም።


እነዚህም ሁለት ነቢያት በምድር የሚኖሩትን ስላሠቃዩ በምድር የሚኖሩት በእነርሱ ላይ ደስ ይላቸዋል፤ በደስታም ይኖራሉ፤ እርስ በርሳቸውም ስጦታ ይሰጣጣሉ።


跟着我们:

广告


广告