Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ነህምያ 8:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ሰባ​ተ​ኛ​ውም ወር በደ​ረሰ ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው ነበሩ። ሕዝ​ቡም ሁሉ በው​ኃው በር ፊት ወዳ​ለው አደ​ባ​ባይ እንደ አንድ ሰው ሆነው ተሰ​በ​ሰቡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለእ​ስ​ራ​ኤል ያዘ​ዘ​ውን የሙ​ሴን ሕግ መጽ​ሐፍ ያመጣ ዘንድ ጸሓ​ፊ​ውን ዕዝ​ራን ነገ​ሩት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ሕዝቡ ሁሉ ከውሃ በር ፊት ለፊት በሚገኘው አደባባይ ላይ እንደ አንድ ሰው ተሰበሰቡ፤ ከዚያም እግዚአብሔር ለእስራኤል ያዘዘውን የሙሴ ሕግ መጽሐፍ እንዲያመጣ ለጸሓፊው ለዕዝራ ነገሩት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ሕዝቡም ሁሉ በውኃው በር ፊት ወዳለው አደባባይ እንደ አንድ ሰው ሆነው ተሰበሰቡ፤ ጌታ ለእስራኤል ያዘዘውን የሙሴን ሕግ መጽሐፍ እንዲያመጣ ለጸሐፊው ለዕዝራ ነገሩት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 የእስራኤል ሕዝብ በሰባተኛው ወር በየከተሞቻቸው መስፈራቸውን አበቁ፤ በዚያም ወር በመጀመሪያው ቀን በኢየሩሳሌም የውሃ በር ተብሎ በሚጠራው አደባባይ በውስጥ በኩል ሕዝቡ ሁሉ በአንድነት ተሰበሰቡ፤ እነርሱም የሕግ ምሁሩን ዕዝራን እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት ለእስራኤል ሕዝብ የሰጠውን የኦሪትን ሕግ መጽሐፍ ያመጣላቸው ዘንድ ለመኑት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ሰባተኛውም ወር በደረሰ ጊዜ የእስራኤል ልጆች በከተሞቻቸው ነበሩ። ሕዝቡም ሁሉ በውኃው በር ፊት ወዳለው አደባባይ እንደ አንድ ሰው ሆነው ተሰበሰቡ፥ እግዚአብሔርም ለእስራኤል ያዘዘውን የሙሴን ሕግ መጽሐፍ ያመጣ ዘንድ ጸሐፊውን ዕዝራን ተናገሩት።

参见章节 复制




ነህምያ 8:1
25 交叉引用  

ንጉ​ሡም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ወጣ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር የይ​ሁዳ ሰዎች ሁሉ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የሚ​ኖሩ ሁሉ፥ ካህ​ና​ቱና ነቢ​ያ​ቱም፥ ሕዝ​ቡም ሁሉ ከታ​ና​ሾቹ ጀምሮ እስከ ታላ​ቆቹ ድረስ ወጡ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት የተ​ገ​ኘ​ውን የቃል ኪዳ​ኑን መጽ​ሐፍ ቃል ሁሉ በጆ​ሮ​አ​ቸው አነ​በበ።


ኬል​ቅ​ያ​ስም ጸሓ​ፊ​ውን ሳፋ​ንን፥ “የሕ​ጉን መጽ​ሐፍ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አግ​ኝ​ቼ​አ​ለሁ” ብሎ ነገ​ረው። ኬል​ቅ​ያ​ስም መጽ​ሐ​ፉን ለሳ​ፋን ሰጠው።


ንጉ​ሡም፥ የይ​ሁ​ዳም ሰዎች ሁሉ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የሚ​ኖ​ሩና ካህ​ናቱ፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑም፥ ሕዝ​ቡም ሁሉ ከታ​ናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ወጡ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት የተ​ገ​ኘ​ውን የቃል ኪዳ​ኑን መጽ​ሐፍ ቃል ሁሉ በጆ​ሮ​አ​ቸው አነ​በበ።


ከዚ​ህም ነገር በኋላ በፋ​ርስ ንጉሥ በአ​ር​ተ​ሰ​ስታ መን​ግ​ሥት ዕዝራ የሠ​ራያ ልጅ፥ የዓ​ዛ​ር​ያስ ልጅ፥ የኬ​ል​ቅ​ያስ ልጅ፥


ዕዝ​ራም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ ይፈ​ል​ግና ያደ​ርግ ዘንድ፥ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሥር​ዐ​ት​ንና ፍር​ድን ያስ​ተ​ምር ዘንድ ልቡን አዘ​ጋ​ጅቶ ነበር።


ንጉ​ሡም አር​ተ​ሰ​ስታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ቃልና ለእ​ስ​ራ​ኤል የሆ​ነ​ውን ሥር​ዐት ይጽፍ ለነ​በ​ረው ለጸ​ሓ​ፊው ለካ​ህኑ ለዕ​ዝራ የሰ​ጠው የደ​ብ​ዳ​ቤው ቃል ይህ ነው፦


ይህም ዕዝራ ከባ​ቢ​ሎን ወጣ፤ እር​ሱም የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሙሴ የሰ​ጠ​ውን ሕግ ዐዋቂ ነበረ፤ የአ​ም​ላ​ኩም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በእ​ርሱ ላይ ነበ​ረ​ችና ንጉሡ ያሻ​ውን ሁሉ ሰጠው።


እነ​ዚ​ህም በኢ​ዮ​ሴ​ዴቅ ልጅ በኢ​ያሱ ልጅ በዮ​አ​ቂም በአ​ለ​ቃ​ውም በነ​ህ​ምያ፥ በጸ​ሓ​ፊ​ውም በካ​ህኑ በዕ​ዝራ ዘመን ነበሩ።


በም​ን​ጭም በር አቅ​ን​ተው ሄዱ፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ደረጃ፥ በቅ​ጥ​ሩም መውጫ፥ ከዳ​ዊ​ትም ቤት በላይ እስከ ውኃው በር ድረስ በም​ሥ​ራቅ በኩል ሄዱ።


ናታ​ኒ​ምም በዖ​ፌል በው​ኃው በር አን​ጻር በም​ሥ​ራቅ በኩል ወጥቶ በቆ​መው ግንብ አጠ​ገብ እስ​ካ​ለው ስፍራ ድረስ ተቀ​መጡ።


ሕዝ​ቡም ወጥ​ተው አመጡ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም በቤቱ ሰገ​ነት ላይ፥ በአ​ደ​ባ​ባ​ዩም ላይ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት አደ​ባ​ባይ ላይ፥ በው​ኃ​ውም በር አደ​ባ​ባ​ይና በኤ​ፍ​ሬም በር አደ​ባ​ባይ ላይ ዳስ ሠሩ።


በው​ኃ​ውም በር ፊት ባለው አደ​ባ​ባይ ላይ ቆሞ፥ በወ​ን​ዶ​ችና በሴ​ቶች በሚ​ያ​ስ​ተ​ው​ሉ​ትም ፊት፥ ከማ​ለዳ ጀምሮ እስከ ቀትር ድረስ አነ​በ​በው፤ የሕ​ዝ​ቡም ሁሉ ጆሮ የሕ​ጉን መጽ​ሐፍ ለመ​ስ​ማት ያደ​ምጥ ነበር።


ነገሩ እን​ዲህ አይ​ደ​ለም ይሉ ዘንድ፥ ለእ​ር​ሱም ግብር እን​ዳ​ይ​ሰጡ ሕግን ለር​ዳታ ሰጥ​ቶ​አ​ልና።


ሙሴም ያዘ​ዛ​ቸ​ውን ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ አመጡ፤ ማኅ​በ​ሩም ሁሉ ቀር​በው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቆሙ።


ለእስራኤል ሁሉ ሥርዓትንና ፍርድን አድርጌ በኮሬብ ያዘዝሁትን የባሪያዬን የሙሴን ሕግ አስቡ።


እርሱም “ስለዚህ የመንግሥተ ሰማያት ደቀ መዝሙር የሆነ ጻፊ ሁሉ ከመዝገቡ አዲሱንና አሮጌውን የሚያወጣ ባለቤትን ይመስላል፤” አላቸው።


“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! መንግሥተ ሰማያትን በሰው ፊት ስለምትዘጉ ወዮላችሁ፤ እናንተ አትገቡም፤ የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።


“ጻፎችና ፈሪሳውያን በሙሴ ወንበር ተቀምጠዋል።


ስለዚህ፥ እነሆ፥ ነቢያትንና ጥበበኞችን ጻፎችንም ወደ እናንተ እልካለሁ፤ ከእነርሱም ትገድላላችሁ ትሰቅሉማላችሁ፥ ከእነርሱም በምኵራባችሁ ትገርፋላችሁ ከከተማም ወደ ከተማ ታሳድዳላችሁ፤


እስ​ራ​ኤል ሁሉ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይታይ ዘንድ እርሱ በመ​ረ​ጠው ቦታ በአ​ን​ድ​ነት በሚ​ሄ​ድ​በት ጊዜ፥ ይህን ሕግ በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ፊት በጆ​ሮው አን​ብ​በው።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ ወጡ፤ ማኅ​በ​ሩም ከዳን እስከ ቤር​ሳ​ቤህ ድረስ፥ ከገ​ለ​ዓ​ድም ሰዎች ጋር፥ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ መሴፋ እንደ አንድ ሰው ሆነው ተሰ​በ​ሰቡ።


ሕዝ​ቡም ሁሉ እንደ አንድ ሰው ተነ​ሥ​ተው እን​ዲህ አሉ፥ “ከእኛ ዘንድ ማንም ወደ ሀገሩ አይ​ሄ​ድም፤ ወደ ቤቱም አይ​መ​ለ​ስም።


跟着我们:

广告


广告