Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ነህምያ 7:65 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

65 ሐቴ​ር​ሰ​ታም፥ “በኡ​ሪ​ምና በቱ​ሚም የሚ​ፈ​ርድ ካህን እስ​ኪ​ነሣ ድረስ ከተ​ቀ​ደ​ሰው ነገር አት​በ​ሉም” አላ​ቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

65 ስለዚህ አገረ ገዥውም ኡሪምና ቱሚም የሚይዝ ካህን እስኪነሣ ድረስ እጅግ ከተቀደሰው ምግብ እንዳይበሉ አዘዛቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

65 ገዢውም፦ በኡሪምና በቱሚም የሚፈርድ ካህን እስኪነሣ ደረስ ከተቀደሰው ነገር እንዳይበሉ ነገራቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

65 ስለዚህም የይሁዳ ገዥ በኡሪምና በቱሚም የሚያገለግል ካህን እስከሚነሣበት ጊዜ ድረስ ለእግዚአብሔር መባ ሆኖ ከሚቀርበው ቊርባን መመገብ የማይችሉ መሆናቸውን ነገራቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

65 ሐቴርሰታም፦ በኡሪምና በቱሚም የሚፈርድ ካህን እስኪነሣ ደረስ ከተቀደሰው ነገር አትበሉም አላቸው።

参见章节 复制




ነህምያ 7:65
16 交叉引用  

ሐቲ​ር​ሰ​ስ​ታም፥ “በኡ​ሪ​ምና በቱ​ሚም የሚ​ፈ​ርድ ካህን እስ​ኪ​ነሣ ድረስ ከቅ​ዱሰ ቅዱ​ሳኑ አት​በ​ሉም” አላ​ቸው።


ያተ​ሙ​ትም እነ​ዚህ ናቸው፤ የሐ​ካ​ልያ ልጅ ሐቴ​ር​ሰታ ነህ​ምያ፥ ሴዴ​ቅ​ያስ፤


እነ​ዚህ በት​ው​ልድ መጽ​ሐፍ ትው​ል​ዳ​ቸ​ውን ፈለጉ፤ ነገር ግን አል​ተ​ገ​ኘም፤ ከክ​ህ​ነ​ትም ተከ​ለ​ከሉ።


ጉባ​ኤ​ውም ሁሉ አርባ ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ስድሳ ነበሩ፤


ከአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆ​ችም ስለ ሥራው ስጦታ ሰጡ። ሐቴ​ር​ሰ​ታም አንድ ሺህ የወ​ርቅ ዳሪክ፥ አም​ሳም ድስ​ቶች፥ አም​ስት መቶ ሠላ​ሳም የካ​ህ​ናት ልብስ በቤተ መዛ​ግ​ብት ውስጥ ሰጠ።


ሕቴ​ር​ሰታ ነህ​ም​ያም፥ ጸሓ​ፊ​ውም ካህኑ ዕዝራ፥ ሕዝ​ቡ​ንም የሚ​ያ​ስ​ተ​ምሩ ሌዋ​ው​ያን ሕዝ​ቡን ሁሉ፥ “ዛሬ ለአ​ም​ላ​ካ​ችን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደሰ ቀን ነው፤ አት​ዘኑ፤ አታ​ል​ቅ​ሱም” አሉ​አ​ቸው፤ ሕዝቡ ሁሉ የሕ​ጉን ቃል በሰሙ ጊዜ ያለ​ቅሱ ነበ​ርና።


በፍ​ርዱ ልብሰ እን​ግ​ድ​ዓም ውስጥ ኡሪ​ም​ንና ቱሚ​ምን ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ወደ ቤተ መቅ​ደስ በገባ ጊዜ በአ​ሮን ልብ ላይ ይሆ​ናሉ፤ አሮ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ሁል​ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ፍርድ በልቡ ላይ ይሸ​ከ​ማል።


ከመ​ሥ​ዋ​ዕ​ቱም የተ​ረ​ፈው ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆቹ ይሆ​ናል፤ ይህም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት የተ​ረፈ ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነው።


ከመ​ሥ​ዋ​ዕ​ቱም የተ​ረ​ፈው ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆቹ ይሆ​ናል፤ ይህም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት የተ​ረፈ ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነው።


በእ​ርሾ ቦክቶ አይ​ጋ​ገ​ርም። ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት የሰ​ጠ​ኋ​ቸው ዕድል ፈንታ ይህ ነው፤ እር​ሱም እንደ ኀጢ​አ​ትና እንደ በደል መሥ​ዋ​ዕት ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነው።


ልብሰ እን​ግ​ድ​ዓ​ው​ንም በእ​ርሱ ላይ አደ​ረገ፤ በል​ብሰ እን​ግ​ድ​ዓ​ውም ላይ የም​ል​ክ​ትና የእ​ው​ነት መገ​ለ​ጫ​ዎ​ችን አኖ​ረ​በት።


በካ​ህ​ኑም በአ​ል​ዓ​ዛር ፊት ይቁም፤ እር​ሱም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ፍርድ ይጠ​ይ​ቅ​ለት፤ እርሱ ከእ​ር​ሱም ጋር የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማኅ​በር ሁሉ በቃሉ ይውጡ፤ በቃ​ሉም ይግቡ።”


ስለ ሌዊም እን​ዲህ አለ፥ ለሌዊ ቃሉን፥ በመ​ከ​ራም ለፈ​ተ​ኑት፥ በክ​ር​ክር ውኃም ለሰ​ደ​ቡት፥ ለእ​ው​ነ​ተ​ኛው ሰው ጽድ​ቁን መልስ።


跟着我们:

广告


广告