Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ነህምያ 6:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 አም​ላኬ ሆይ፥ ስለ​ዚህ ሥራ​ቸው ጦቢ​ያ​ንና ሰን​ባ​ላ​ጥን፥ ነቢ​ይ​ቱ​ንም ኖዓ​ድ​ያን ያስ​ፈ​ራ​ሩኝ ዘንድ የፈ​ለ​ጉ​ትን፥ የቀ​ሩ​ት​ንም ነቢ​ያት አስብ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 አምላኬ ሆይ፤ ስለ ፈጸሙት ድርጊት ጦቢያንና ሰንባላጥን ዐስብ፤ ሊያስፈራሩኝ የሞከሩትን ነቢያቱን ኖዓድያንና ሌሎቹን ነቢያትም ዐስብ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 አምላኬ ሆይ፥ ጦቢያን፥ ሰንባላጥን ስለዚህ ሥራቸው ደግሞም ሊያስፈራሩኝ ነቢያቱን ኖዓድያና የተቀሩት ነቢያትን አስብ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 እኔም “አምላክ ሆይ፥ ጦቢያና ሰንባላጥ ያደረጉትን ሁሉ ተመልከት፤ ፍረድባቸውም፤ ኖዓድያ የተባለችው ሴት ነቢይትና ሌሎቹም ነቢያት እኔን ለማስፈራራት ያደረጉትን ሁሉ አስብ” በማለት ጸለይኩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 አምላኬ ሆይ፥ ስለዚህ ሥራቸው ጦብያንና ሰንባላጥን ያስፈራሩኝም ዘንድ የወደዱትን ነቢይቱን ኖዓድያን የቀሩትንም ነቢያት አስብ።

参见章节 复制




ነህምያ 6:14
26 交叉引用  

“አም​ላኬ ሆይ፥ ክህ​ነ​ትን የክ​ህ​ነ​ት​ንና የሌ​ዋ​ው​ያ​ን​ንም ቃል ኪዳን ስላ​ፈ​ረሱ አስ​ባ​ቸው።”


አም​ላኬ ሆይ፥ ለዚህ ሕዝብ ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ሁሉ ለበ​ጎ​ነት አስ​ብ​ልኝ።


በመ​ከራ መካ​ከል እንኳ ብሄድ፥ አንተ ታድ​ነ​ኛ​ለህ፤ በጠ​ላ​ቶች ቍጣ ላይ እጆ​ች​ህን ትዘ​ረ​ጋ​ለህ፥ ቀኝ​ህም ያድ​ነ​ኛል


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጠ​ብ​ቀ​ኛል፥ የሚ​ያ​ሳ​ጣ​ኝም የለም።


አቤቱ፥ ወደ አንተ የለ​መ​ን​ሁ​ትን ጸሎ​ቴን ስማኝ፥ ከጠ​ላ​ትም ጥር​ጥር ነፍ​ሴን አድ​ናት።


የአ​ሮን እኅት ነቢ​ይቱ ማር​ያ​ምም ከበሮ በእ​ጅዋ ወሰ​ደች፤ ሴቶ​ችም ሁሉ በከ​በ​ሮና በዝ​ማሬ በኋ​ላዋ ወጡ።


ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በስሜ የሐ​ሰት ትን​ቢት ስለ​ሚ​ና​ገሩ ነቢ​ያት ስላ​ላ​ክ​ኋ​ቸው፦ በዚ​ህች ሀገር ሰይ​ፍና ረሃብ አይ​ሆ​ንም ስለ​ሚሉ ነቢ​ያት እን​ዲህ ይላል፥ “እነ​ዚያ ነቢ​ያት በሰ​ይ​ፍና በራብ ይጠ​ፋሉ።


ወደ ሜዳ ብወጣ፥ እነሆ በሰ​ይፍ የሞቱ አሉ፤ ወደ ከተ​ማም ብገባ፥ እነሆ በራብ የከሱ አሉ፤ ነቢ​ዩና ካህኑ ወደ​ማ​ያ​ው​ቋት ሀገር ሄደ​ዋ​ልና።”


ከዚ​ህም በኋላ እን​ዲህ ሆነ፤ በዚያ ዓመት፥ በይ​ሁዳ ንጉሥ በሴ​ዴ​ቅ​ያስ መን​ግ​ሥት መጀ​መ​ሪያ፥ በአ​ራ​ተ​ኛው ዓመት በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ወር ሐሰ​ተ​ኛው ነቢይ የገ​ባ​ዖን ሰው የዓ​ዙር ልጅ ሐና​ንያ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በካ​ህ​ና​ትና በሕ​ዝብ ሁሉ ፊት እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረኝ፦


ሐሰ​ተ​ኛው ነቢይ ሐና​ን​ያም በሕ​ዝቡ ሁሉ ፊት ቀን​በ​ሩን ከነ​ቢዩ ከኤ​ር​ም​ያስ አን​ገት ወስዶ ሰበ​ረው።


ነቢ​ዩም ኤር​ም​ያስ ሐሰ​ተ​ኛ​ውን ሐና​ን​ያን፥ “ሐና​ንያ ሆይ ስማ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አል​ላ​ከ​ህም፤ ነገር ግን ይህ ሕዝብ በሐ​ሰት እን​ዲ​ታ​መን አድ​ር​ገ​ሃል።


ብዙ ሐሰተኞች ነቢያትም ይነሣሉ፤ ብዙዎችንም ያስታሉ፤


ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፤ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ።


“የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውስጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ።


ኢያኔስና ኢያንበሬስም ሙሴን እንደ ተቃወሙት፥ እንዲሁ እነዚህ ደግሞ አእምሮአቸው የጠፋባቸው ስለ እምነትም የተጣሉ ሰዎች ሆነው እውነትን ይቃወማሉ።


ማንም ወንድሙን ሞት የማይገባውን ኃጢአት ሲያደርግ ቢያየው ይለምን፥ ሞትም የማይገባውን ኃጢአት ላደረጉት ሕይወት ይሰጥለታል። ሞት የሚገባው ኃጢአት አለ፤ ስለዚያ እንዲጠይቅ አልልም።


አውሬውም ተያዘ፤ በእርሱም ፊት ተአምራትን እያደረገ የአውሬውን ምልክት የተቀበሉትን ለምስሉም የሰገዱትን ያሳተ ሐሰተኛው ነቢይ ከእርሱ ጋር ተያዘ፤ ሁለቱም በሕይወት ሳሉ በዲን ወደሚቃጠል ወደ እሳት ባሕር ተጣሉ።


跟着我们:

广告


广告