Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ነህምያ 6:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 እኔም ወደ መሔ​ጣ​ብ​ኤል ልጅ ወደ ዶልያ ልጅ ወደ ሴሜይ ቤት ገባሁ፤ እር​ሱም ተዘ​ግቶ ነበ​ርና፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በመ​ቅ​ደሱ ውስጥ እን​ግባ፤ የመ​ቅ​ደ​ሱ​ንም ደጆች እን​ዝጋ፤ እነ​ርሱ በሌ​ሊት ይገ​ድ​ሉህ ዘንድ ይመ​ጣ​ሉና” አለኝ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 አንድ ቀን ቤቱ በላዩ ላይ ተዘግቶበት ወደ ነበረው ወደ መሄጣብኤል ልጅ ወደ ድላያ ልጅ ወደ ሸማያ ሄድሁ፤ እርሱም፣ “ሰዎች ሊገድሉህ ይመጣሉ፤ በርግጥም በሌሊት ሊገድሉህ ይመጣሉ፤ በእግዚአብሔር ቤት ባለው በቤተ መቅደሱ ውስጥ እንገናኝ፤ የቤተ መቅደሱንም በሮች እንዝጋቸው” አለኝ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 እኔም ወደ ሜሔጣብኤል ልጅ፥ ወደ ዴላያ ልጅ፥ ወደ ሼማዕያ ቤት ሄድሁ፤ እርሱም ተዘግቶ ነበርና፦ “በእግዚአብሔር ቤት፥ በመቅደሱ ውስጥ እንገናኝ፥ የመቅደሱንም በሮች እንዝጋ፤ ሊገድሉህ ይመጣሉና፥ በሌሊት ሊገድሉህ ይመጣሉና” አለ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 በዚህም ጊዜ ከቤቱ እንዳይወጣ ተዘግቶበት ወደነበረው የመሄጣብኤል የልጅ ልጅ ወደ ሆነው ወደ ደላያ ልጅ ሸማዕያ ዘንድ ሄድኩ፤ እርሱም “በሌሊት ሊገድሉህ ስለሚመጡ አንተና እኔ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ ገብተን በሮቹን በመዝጋት እንደበቅ” አለኝ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 እኔም ወደ መሔጣብኤል ልጅ ወደ ድላያ ልጅ ወደ ሸማያ ቤት ገባሁ፥ እርሱም ተዘግቶ ነበርና፦ በእግዚአብሔር ቤት በመቅደሱ ውስጥ እንገናኝ የመቅደሱንም ደጆች እንዝጋ፥ እነርሱ መጥተው ይገድሉሃልና፥ በሌሊትም ይገድሉህ ዘንድ ይመጣሉና አለ።

参见章节 复制




ነህምያ 6:10
21 交叉引用  

የአ​ክ​ቦር ልጅ በአ​ል​ሐ​ና​ንም ሞተ፤ በእ​ር​ሱም ፈንታ አዳር ነገሠ፤ የከ​ተ​ማ​ውም ስም ፎጎር ነው፤ ሚስ​ቱም የሜ​ዛ​አብ ልጅ መጥ​ሬድ የወ​ለ​ደ​ቻት ምኤ​ጠ​ብ​ኤል ትባ​ላ​ለች።


በቤ​ቱም ግንብ ዙሪያ፥ በመ​ቅ​ደ​ሱና በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳኑ ግንብ ዙሪያ ደርብ ሠራ፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ጓዳ​ዎች አደ​ረገ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ስድ​ስት ዓመት ሸሸ​ገ​ችው። ጎቶ​ል​ያም በሀ​ገሩ ላይ ነገ​ሠች።


የአ​ክ​ዓ​ብን ቤት ሁሉ ታጠ​ፋ​ለህ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘንድ አጥር ተጠ​ግቶ እስ​ከ​ሚ​ሸን የቀ​ረ​በ​ውን ሁሉና ከእ​ነ​ርሱ የቀ​ረ​ውን ሁሉ ታጠ​ፋ​ለህ።


አካ​ዝም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ዕቃ​ዎች ሁሉ ወስዶ ሰባ​በ​ራ​ቸው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት ደጆች ዘጋ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ማዕ​ዘን ሁሉ ለራሱ መሠ​ዊያ ሠራ።


በመ​ን​ግ​ሥ​ቱም በጸና ጊዜ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ደጆች ከፈተ፤ አደ​ሳ​ቸ​ውም።


ደግ​ሞም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ደጆች ዘግ​ተ​ዋል፤ መብ​ራ​ቶ​ቹ​ንም አጥ​ፍ​ተ​ዋል፤ በመ​ቅ​ደ​ሱም ውስጥ ለእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ አላ​ጠ​ኑም፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት አላ​ቀ​ረ​ቡም።


ከኤ​ራም ልጆ​ችም አል​ዓ​ዛር፥ ይሲያ፥ ሚል​ክያ፥ ሰማያ፥ ስም​ዖን፥


ወደ አለ​ቆ​ቹም ወደ አል​ዓ​ዛር፥ ወደ አር​ኤል፥ ወደ ሰማ​አያ፥ ወደ ሀሎ​ናም፥ ወደ ያሪብ፥ ወደ ሄል​ና​ታን፥ ወደ ናታን፥ ወደ ዘካ​ር​ያስ፥ ወደ ሜሱ​ላም፥ ደግ​ሞም ወደ ዐዋ​ቂ​ዎቹ ወደ ዮያ​ሪ​ብና ወደ ሄል​ና​ታን ላክሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ልኮት እን​ዳ​ል​ነ​በረ፥ በእኔ ላይ ግን ትን​ቢት እንደ ተና​ገረ፥ እነሆ፥ ዐወ​ቅሁ፤ ጦብ​ያና ሰን​ባ​ላ​ጥም ገዝ​ተ​ውት ነበር።


እስከ መቼ በነ​ፍሴ ኀዘ​ንን አኖ​ራ​ለሁ? እስከ መቼ ልቤ ሁል​ጊዜ ትጨ​ነ​ቅ​ብ​ኛ​ለች? እስከ መቼ ጠላ​ቶች በላዬ ይታ​በ​ያሉ?


ነፍ​ሴ​ንም የሚ​ሹ​አት በረ​ቱ​ብኝ፥ መከ​ራ​ዬ​ንም የሚ​ፈ​ልጉ ከን​ቱን ተና​ገሩ፥ ሁል​ጊ​ዜም ያጠ​ፉኝ ዘንድ በሽ​ን​ገላ ይመ​ክ​ራሉ።


በክፉዎች አፍ የሀገር ወጥመድ አለ፥ የጻድቃን ዕውቀት ግን መልካም ጎዳና ናት።


ኤር​ም​ያ​ስም ባሮ​ክን እን​ዲህ ሲል አዘ​ዘው፥ “እኔ እስ​ረኛ ነኝ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤትም እገባ ዘንድ አል​ች​ልም።


መን​ፈ​ስም ወደ እኔ መጣ፤ በእ​ግ​ሬም አቆ​መኝ፤ ተና​ገ​ረ​ኝም እን​ዲ​ህም አለኝ፥ “ሂድ ገብ​ተህ ቤት​ህን ዝጋ።


በመሠዊያዬ ላይ እሳትን በከንቱ እንዳታቃጥሉ ከእናንተ ዘንድ ደጅ የሚዘጋ ሰው ምነው በተገኘ! በእናንተ ደስ አይለኝም፥ ቍርባንንም ከእጃችሁ አልቀበልም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


“የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውስጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ።


ሥራው ክፉ የሆነ ሁሉ ብር​ሃ​ንን ይጠ​ላ​ልና፤ ክፉም ስለ​ሆነ ሥራው እን​ዳ​ይ​ገ​ለ​ጥ​በት ወደ ብር​ሃን አይ​መ​ጣም።


ከተ​ማ​ውም ሁሉ ታወከ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ እየ​ሮጡ ሄደው ጳው​ሎ​ስን ጐት​ተው ከቤተ መቅ​ደስ አወ​ጡት፤ በሩ​ንም ሁሉ ዘጉ።


跟着我们:

广告


广告