Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ነህምያ 5:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ደግ​ሞም አልሁ፥ “የም​ታ​ደ​ር​ጉት ነገር መል​ካም አይ​ደ​ለም፤ ጠላ​ቶ​ቻ​ችን አሕ​ዛብ እን​ዳ​ይ​ሰ​ድ​ቡን አም​ላ​ካ​ች​ንን በመ​ፍ​ራት ትሄዱ ዘንድ አይ​ገ​ባ​ች​ሁ​ምን?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ስለዚህ በመቀጠል እንዲህ አልሁ፤ “ይህ የምታደርጉት ነገር ትክክል አይደለም፤ የጠላቶቻችንን የአሕዛብን ስድብ ለማስወገድ የአምላካችንን መንገድ በፍርሀት መከተል አይገባችሁምን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 እንዲህም አልኳቸው፦ የምታደርጉት ነገር መልካም አይደለም፤ ጠላቶቻችን አሕዛብ እንዳይሰድቡን አምላካችንን በመፍራት መሄድ አይገባችሁምን?

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 እኔ ግን ንግግሬን በመቀጠል እንዲህ አልኳቸው፤ “ያደረጋችኹት ነገር ትክክል አይደለም! እግዚአብሔርን መፍራትና ትክክል የሆነውን ነገር ማድረግ በተገባችሁ ነበር፤ ይህን አድርጋችሁ ቢሆን ኖሮ፥ አሕዛብ ጠላቶቻችን ባልተዘባበቱብንም ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ደግሞም አልሁ፦ የምታደርጉት ነገር መልካም አይደለም፥ ጠላቶቻችን አሕዛብ እንዳይሰድቡን አምላካችንን በመፍራት ትሄዱ ዘንድ አይገባችሁምን?

参见章节 复制




ነህምያ 5:9
21 交叉引用  

አብ​ር​ሃ​ምም አለ፥ “ምን​አ​ል​ባት በዚህ ስፍራ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት ስለ​ሌለ በሚ​ስቴ ምክ​ን​ያት ይገ​ድ​ሉ​ኛል ብዬ ነው።


በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ዮሴፍ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ትድኑ ዘንድ ይህን አድ​ርጉ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እፈ​ራ​ለ​ሁና።


ነገር ግን በዚህ ነገር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠላ​ቶች መነ​ሣ​ሣት ምክ​ን​ያት አድ​ር​ገ​ሃ​ልና ስለ​ዚህ ደግሞ የተ​ወ​ለ​ደ​ልህ ልጅ ፈጽሞ ይሞ​ታል” አለው።


አም​ላ​ካ​ችን ሆይ፥ ተን​ቀ​ና​ልና ስማ፤ ስድ​ባ​ቸ​ውን በራ​ሳ​ቸው ላይ መል​ስ​ባ​ቸው፤ በም​ርኮ ሀገር ለብ​ዝ​በዛ አሳ​ል​ፈህ ስጣ​ቸው።


እኔ ደግሞ፥ ወን​ድ​ሞ​ችም፥ ብላ​ቴ​ኖ​ችም ገን​ዘ​ብና እህል ለእ​ነ​ርሱ አበ​ድ​ረ​ናል፤ እባ​ካ​ችሁ፥ ይህን ወለድ እን​ተ​ው​ላ​ቸው።


ከእኔ አስ​ቀ​ድ​መው የነ​በ​ሩት አለ​ቆች ግን በሕ​ዝቡ ላይ አክ​ብ​ደው ነበር፤ ስለ እን​ጀ​ራ​ውና ስለ ወይኑ አርባ ሰቅል ብር ይወ​ስዱ ነበር፤ ሎሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ደግሞ በሕ​ዝቡ ላይ ይሰ​ለ​ጥኑ ነበር። እኔ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስለ ፈራሁ እን​ዲህ አላ​ደ​ረ​ግ​ሁም።


በመ​ን​ገ​ድህ ሁሉ ይጠ​ብ​ቁህ ዘንድ መላ​እ​ክ​ቱን ስለ አንተ ያዝ​ዛ​ቸ​ዋ​ልና፤


ክፉ ሰው ወዳጆቹን ይዋሻል፥ መልካምም ወዳልሆኑ መንገዶች ይመራቸዋል።


ጻድቅን ሰው ማዋረድ መልካም አይደለም። በእውነት ለሚፈርዱም መዋሸት መልካም አይደለም።


የኃጥኣንን ፊት ማድነቅ መልካም አይደለም። በፍርድ ጊዜም እውነትን ማራቅ መልካም አይደለም፥


ነፍስ ዕውቀት የሌለባት ትሆን ዘንድ መልካም አይደለም፤ እግሩንም የሚያፈጥን ከመንገድ ይስታል።


የነገሩትን የሚጠብቅ ልጅ ከጥፋት የራቀ ነው፥ የሚቀበልም እርሱን ይቀበለዋል።


ወደ ገቡ​ባ​ቸ​ውም ወደ አሕ​ዛብ በመጡ ጊዜ፥ ሰዎች እነ​ር​ሱን፦ ከም​ድ​ራ​ቸው የወጡ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝብ እነ​ዚህ ናቸው ሲሉ​አ​ቸው ቅዱስ ስሜን አረ​ከሱ።


ወን​ድ​ምህ ከአ​ንተ ጋር ይኖር ዘንድ ከእ​ርሱ ምንም ወለድ ወይም ትርፍ አት​ው​ሰድ፤ ነገር ግን አም​ላ​ክ​ህን ፍራ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና።


በይ​ሁዳ፥ በሰ​ማ​ር​ያና በገ​ሊላ ያሉ አብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ናት ሁሉ በሰ​ላም ኖሩ፤ ታነ​ጹም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም በመ​ፍ​ራት ጸን​ተው ኖሩ፤ ሕዝ​ቡም በመ​ን​ፈስ ቅዱስ አጽ​ና​ኝ​ነት በዙ።


እንደ ተጻ​ፈም “እነሆ፥ በእ​ና​ንተ ምክ​ን​ያት አሕ​ዛብ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም ይሰ​ድ​ባሉ።”


እንግዲህ ቆነጃጅት ሊያገቡ፥ ልጆችንም ሊወልዱ፥ ቤቶቻቸውንም ሊያስተዳድሩ፥ ተቃዋሚውም የሚሳደብበትን አንድን ምክንያት ስንኳ እንዳይሰጡ እፈቅዳለሁ፤


ስለሚመለከቱት ስለ መልካም ሥራችሁ፥ ክፉ እንደምታደርጉ በዚያ እናንተን በሚያሙበት ነገር፥ በሚጎበኝበት ቀን እግዚአብሔርን ያከብሩት ዘንድ በአሕዛብ መካከል ኑሮአችሁ መልካም ይሁን።


ልጆቼ ሆይ፥ ይህ አይ​ሆ​ንም፤ እኔ የም​ሰ​ማው ይህ ነገር መል​ካም አይ​ደ​ለ​ምና እን​ዲህ አታ​ድ​ርጉ። ሕዝ​ቡ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከማ​ገ​ል​ገል አት​ከ​ል​ክ​ሉ​አ​ቸው።


跟着我们:

广告


广告