Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ነህምያ 5:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ከእኔ አስ​ቀ​ድ​መው የነ​በ​ሩት አለ​ቆች ግን በሕ​ዝቡ ላይ አክ​ብ​ደው ነበር፤ ስለ እን​ጀ​ራ​ውና ስለ ወይኑ አርባ ሰቅል ብር ይወ​ስዱ ነበር፤ ሎሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ደግሞ በሕ​ዝቡ ላይ ይሰ​ለ​ጥኑ ነበር። እኔ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስለ ፈራሁ እን​ዲህ አላ​ደ​ረ​ግ​ሁም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ከእኔ በፊት የነበሩት የቀድሞዎቹ አገረ ገዦች ግን ከምግቡና ከወይኑ ሌላ፣ በሕዝቡ ላይ ከባድ ሸክም በመጫን አርባ ሰቅል ብር ይወስዱ ነበር፤ ረዳቶቻቸውም እንዲሁ ይጭኑባቸው ነበር። እኔ ግን እግዚአብሔርን ከመፍራቴ የተነሣ እንዲህ ያለውን አላደረግሁም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ከእኔ በፊት የነበሩት የቀድሞ ገዢዎች ግን በሕዝቡ ላይ አክብደውባቸው ነበር፥ ምግብ፥ ወይና አርባ ሰቅል ብር ከእነሱ ይወስዱ ነበር፤ አገልጋዮቻቸው ደግሞ ሕዝቡን ይጨቁኑአቸው ነበር፤ እኔ ግን እግዚአብሔርን ስለ ፈራሁ እንዲህ አላደረግሁም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ከእኔ በፊት የሕዝብ ገዢ ሆኖ የተሾመው ሁሉ በሕዝቡ ላይ ከባድ ሸክም በመሆን፥ በየቀኑ ለምግብና ለመጠጥ የሚሆን አርባ ብር ያስከፍላቸው ነበር፤ የገዢዎቹም አገልጋዮች እንኳ በሕዝቡ ላይ ሠልጥነውባቸው ይጨቊኑአቸው ነበር፤ እኔ ግን እግዚአብሔርን ስለምፈራ እንደዚያ አላደረግሁም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ከእኔ አስቀድመው የነበሩት አለቆች ግን በሕዝቡ ላይ አክብደው ነበር፥ ስለ እንጀራውና ስለ ወይኑ አርባ ሰቅል ብር ይወስዱ ነበር፥ ሎሌዎቻቸውም ደግሞ በሕዝቡ ላይ ይሠለጥኑ ነበር፥ እኔ ግን እግዚአብሔርን ስለ ፈራሁ እንዲህ አላደረግሁም።

参见章节 复制




ነህምያ 5:15
19 交叉引用  

አብ​ር​ሃ​ምም አለ፥ “ምን​አ​ል​ባት በዚህ ስፍራ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት ስለ​ሌለ በሚ​ስቴ ምክ​ን​ያት ይገ​ድ​ሉ​ኛል ብዬ ነው።


በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ዮሴፍ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ትድኑ ዘንድ ይህን አድ​ርጉ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እፈ​ራ​ለ​ሁና።


ደግ​ሞም የቅ​ጥ​ሩን ሥራ ሠራሁ፤ እር​ሻም አል​ገ​ዛ​ሁም፤ ብላ​ቴ​ኖ​ችም ሁሉ ወደ​ዚ​ያው ወደ ሥራው ተሰ​በ​ሰቡ።


ደግ​ሞም አልሁ፥ “የም​ታ​ደ​ር​ጉት ነገር መል​ካም አይ​ደ​ለም፤ ጠላ​ቶ​ቻ​ችን አሕ​ዛብ እን​ዳ​ይ​ሰ​ድ​ቡን አም​ላ​ካ​ች​ንን በመ​ፍ​ራት ትሄዱ ዘንድ አይ​ገ​ባ​ች​ሁ​ምን?


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግርማ አስ​ደ​ን​ግ​ጦ​ኛ​ልና፤ በእ​ር​ሱም ከመ​ያዝ በም​ክ​ን​ያት ማም​ለጥ አል​ቻ​ል​ሁም።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባሪ​ያ​ዎች ሆይ፥ አመ​ስ​ግ​ኑት፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም አመ​ስ​ግኑ።


እግዚአብሔርን የሚፈልግ ዕውቀትን ከጽድቅ ጋር ያገኛል፥


ከእ​ና​ንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ፥ ማን ነው? የባ​ሪ​ያ​ው​ንም ቃል ይስማ፤ በጨ​ለ​ማም የም​ት​ሄዱ፥ ብር​ሃ​ንም የሌ​ላ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ታመኑ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተደ​ገፉ፤


በዐ​ና​ቶ​ትም ያለ​ውን እርሻ ከአ​ጎቴ ልጅ ከአ​ና​ም​ኤል ገዛሁ፤ ዐሥራ ሰባት ሰቅል ብርም መዘ​ን​ሁ​ለት።


ባሪ​ያ​ዎች ሠል​ጥ​ነ​ው​ብ​ናል፤ ከእ​ጃ​ቸ​ውም የሚ​ታ​ደ​ገን የለም።


ወንድሞቻችሁንም ብቻ እጅ ብትነሡ ምን ብልጫ ታደርጋላችሁ? አሕዛብስ ያንኑ ያደርጉ የለምን?


ከእ​ና​ንተ ዘንድ በነ​በ​ር​ሁ​በት ጊዜም፥ ስቸ​ገር ገን​ዘ​ባ​ች​ሁን አል​ተ​መ​ኘ​ሁም። ባል​በ​ቃ​ኝም ጊዜ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ከመ​ቄ​ዶ​ንያ መጥ​ተው አሙ​አ​ሉ​ልኝ፤ በእ​ና​ን​ተም ላይ እን​ዳ​ል​ከ​ብ​ድ​ባ​ችሁ በሁሉ ተጠ​ነ​ቀ​ቅሁ፤ ወደ ፊትም እጠ​ነ​ቀ​ቃ​ለሁ።


እከ​ብ​ድ​ባ​ችሁ ዘንድ ወደ እና​ንተ ካለ​መ​ም​ጣቴ በቀር፥ ከአ​ብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ናት ሁሉ ያሳ​ነ​ስ​ኋ​ችሁ በም​ን​ድን ነው? ይህ​ቺን በደ​ሌን ይቅር በሉኝ።


ከዘ​ራ​ች​ሁና ከወ​ይ​ና​ች​ሁም ዐሥ​ራት ወስዶ ለጃ​ን​ደ​ረ​ቦ​ቹና ለሎ​ሌ​ዎቹ ይሰ​ጣ​ቸ​ዋል።


跟着我们:

广告


广告