Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ነህምያ 4:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 እኔና ወን​ድ​ሞ​ችም፥ ብላ​ቴ​ኖ​ችም በኋ​ላ​ዬም የነ​በ​ሩት ጠባ​ቂ​ዎች ልብ​ሳ​ች​ንን አና​ወ​ል​ቅም ነበር። ወደ ውኃም ስን​ሄድ መሣ​ሪ​ያ​ች​ንን እን​ደ​ታ​ጠ​ቅን እን​ሄድ ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 እኔም ሆንሁ ወንድሞቼ፣ ሰዎቼም ሆኑ ከእኔ ጋራ ያሉት ጠባቂዎች ልብሳችንን አላወለቅንም፤ ለውሃ እንኳ በምንሄድበት ጊዜ እያንዳንዱ ሰው የጦር መሣሪያውን እንደ ያዘ ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 እኔም ሆንኩ የሥራ ጓደኞቼ፥ አገልጋዮቼም ሆኑ የክብር ዘቦቼ፥ ሁላችንም ሌሊት እንኳ ልብሳችንን አናወልቅም ነበር። በዚህም ዐይነት ውሃ ስንቀዳ እንኳ መሣሪያችን ከእጃችን አልተለየም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 እኔና ወንድሞቼም ብላቴኖቼም በኋላዬም የነበሩት ጠባቂዎች ልብሳችንን አናወልቅም ነበር።

参见章节 复制




ነህምያ 4:23
8 交叉引用  

ደግ​ሞም በዚያ ጊዜ ሕዝ​ቡን፥ “ሁላ​ችሁ ከብ​ላ​ቴ​ኖ​ቻ​ችሁ ጋር በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ውስጥ እደሩ፤ በሌ​ሊ​ትም ጠባ​ቂ​ዎች ሁኑ​ልን፤ በቀ​ንም ሥሩ” አል​ኋ​ቸው።


በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም በአ​ይ​ሁድ ላይ ትልቅ የሕ​ዝ​ቡና የሚ​ስ​ቶ​ቻ​ቸው ጩኸት ሆነ።


ደግ​ሞም የቅ​ጥ​ሩን ሥራ ሠራሁ፤ እር​ሻም አል​ገ​ዛ​ሁም፤ ብላ​ቴ​ኖ​ችም ሁሉ ወደ​ዚ​ያው ወደ ሥራው ተሰ​በ​ሰቡ።


ወን​ድ​ሜን ሃና​ኒ​ንና የግ​ን​ቡን አለቃ ሐና​ን​ያ​ንም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ ሾም​ኋ​ቸው፤ እር​ሱም እው​ነ​ተኛ ከሌ​ሎ​ቹም ይልቅ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ ሰው ነበረ።


አንዱ ከሌ​ላው ርቆ አይ​ቆ​ምም፤ የጦር መሣ​ሪ​ያ​ቸ​ውን ይዘው ይሮ​ጣሉ፤ በመ​ሣ​ሪ​ያ​ቸው ላይ ይወ​ድ​ቃሉ፤ እነ​ር​ሱም አይ​ጠ​ፉም።


ነገር ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ አሁን እኔ ባለ​ሁ​በት አለሁ፤ ለእ​ኔም የሰ​ጠኝ ጸጋው ለከ​ንቱ የሆ​ነ​ብኝ አይ​ደ​ለም፤ እኔም ከሁሉ ይልቅ ደከ​ምሁ፤ ነገር ግን በእኔ ላይ ያደ​ረው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ አጸ​ናኝ እንጂ እኔ አይ​ደ​ለ​ሁም።


በብ​ዙ​ዎች ደስ​ተ​ኞች መካ​ከል መሰ​ን​ቆን ምቱ፤ በዚያ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የጽ​ድቅ ሥራን፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ውስጥ ጽድ​ቅ​ንና ኀይ​ልን ያቀ​ር​ባሉ። ያን​ጊ​ዜም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝብ ወደ ከተ​ማ​ዎቹ ወረዱ።


አቤ​ሜ​ሌ​ክና ከእ​ርሱ ጋር ያሉ​ትም ሕዝብ ሁሉ ወደ ሄር​ሞን ተራራ ወጡ፤ አቤ​ሜ​ሌ​ክም በእጁ መጥ​ረ​ቢያ ወስዶ የዛ​ፉን ቅር​ን​ጫፍ ቈረጠ፤ አን​ሥ​ቶም በጫ​ን​ቃው ላይ ተሸ​ከ​መው፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ለነ​በ​ሩት ሕዝብ፥ “እኔ ሳደ​ርግ ያያ​ች​ሁ​ትን፥ እና​ን​ተም ፈጥ​ና​ችሁ እኔ እን​ዳ​ደ​ረ​ግሁ አድ​ርጉ” አላ​ቸው።


跟着我们:

广告


广告