ነህምያ 3:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)30 ከእርሱም በኋላ የሰሎምያ ልጅ ሐናንያና የሴሌፍ ስድስተኛው ልጁ ሐኖን ሌላውን ክፍል ሠሩ። ከዚያም በኋላ የበራክያ ልጅ ሜሱላም በሙዳየ ምጽዋቱ አንጻር ያለውን ሠራ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም30 ከርሱ ቀጥሎ ያለውን ሌላ ክፍል ደግሞ የሰሌምያ ልጅ ሐናንያና የሴሌፍ ስድስተኛ ልጅ ሐኖን መልሰው ሠሩ። ከእነርሱም ቀጥሎ የቤራክያ ልጅ ሜሱላም ከመኖሪያው ትይዩ ያለውን መልሶ ሠራ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)30 ከእርሱ በኋላ የሼሌምያ ልጅ ሐናንያና የጻላፍ ስድስተኛው ልጁ ሐኑን ሌላውን ክፍል አደሱ። ከእርሱ በኋላ የቤሬክያ ልጅ ሜሹላም ከክፍሉ ፊት ለፊት ያለውን አደሰ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም30 የሼሌምያ ልጅ ሐናንያና የጻላፍ ስድስተኛ ልጅ ሐኑን ለሁለተኛ ጊዜ የተሰጣቸውን ድርሻ ሠሩ። የበራክያ ልጅ መሹላምም በመኖሪያ ቤቱ ፊት ለፊት በኩል ያለውን ሠራ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)30 ከእርሱ በኋላ የሰሌምያ ልጅ ሐናንያና የሴሌፍ ስድስተኛው ልጁ ሐኖን ሌላውን ክፍል አደሱ። ከዚያም በኋላ የበራክያ ልጅ ሜሱላም በጓዳው አንጻር ያለውን አደሰ። 参见章节 |