Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ነህምያ 3:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 የኡ​ዛይ ልጅ ፋልል በማ​ዕ​ዘኑ አን​ጻር ያለ​ው​ንና በዘ​በ​ኞች አደ​ባ​ባይ አጠ​ገብ ከላ​ይ​ኛው የን​ጉሡ ቤት ወጥቶ የቆ​መ​ውን ግንብ ሠራ። ከእ​ር​ሱም በኋላ የፋ​ሮስ ልጅ ፈዳያ ሠራ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 የኡዛይ ልጅ ፋላል ከቅጥሩ ማእዘን ትይዩና በዘብ መጠበቂያው አደባባይ አጠገብ ካለው ከላይኛው ቤተ መንግሥት መጠበቂያ ግንብ ጀምሮ ያለውን መልሶ ሠራ። ከርሱም ቀጥሎ የፋሮስ ልጅ ፈዳያና

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 የኡዛይ ልጅ ፓላል በግንቡ መደገፊያ ፊት ለፊት ያለውንና በዘበኞች አደባባይ አጠገብ ከላይኛው የንጉሡ ቤት ወጥቶ የቆመውን ግንብ ሠራ፥ ከእርሱም በኋላ የፋኖስ ልጅ ፈዳያ ሠራ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25-26 የዑዛይ ልጅ ፓላል ከቅጽሩ ማእዘንና በዘብ መጠበቂያው አደባባይ አጠገብ ከሚገኘው ከላይኛው ቤተ መንግሥት መጠበቂያ ግንብ ጀምሮ ያለውን ክፍል ሁሉ ሠራ። የፓርዖሽ ልጅ ፐዳያ ደግሞ በውሃው ቅጽር በር አጠገብ ወደምሥራቅ የሚያመለክተውን ስፍራና የቤተ መቅደሱን መጠበቂያ ግንብ ይኸውም የቤተ መቅደሱ ሠራተኞች በሚኖሩበት የከተማይቱ አንድ ክፍል በሆነው “ዖፌል” ተብሎ በሚጠራው ስፍራ አጠገብ ያለውን ክፍል ሠራ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 የኡዛይ ልጅ ፋላል በማዕዘኑ አንጻር ያለውንና በዘበኞች አደባባይ አጠገብ ከላይኛው የንጉሡ ቤት ወጥቶ የቆመውን ግንብ ሠራ፥ ከእርሱም በኋላ የፋኖስ ልጅ ፈዳያ ሠራ።

参见章节 复制




ነህምያ 3:25
12 交叉引用  

የፋ​ሮስ ልጆች ሁለት ሺህ መቶ ሰባ ሁለት።


ከኤ​ፍ​ሬ​ምም በር በላይ፥ በአ​ሮ​ጌው በርና በዓሣ በር፥ በአ​ና​ን​ኤ​ልም ግንብ፥ በሃ​ሜአ ግንብ እስከ በጎች በር ድረስ ሄዱ፤ በዘ​በ​ኞ​ችም በር አጠ​ገብ ቆሙ።


የፋ​ሮስ ልጆች ሁለት ሺህ አንድ መቶ ሰባ ሁለት።


ጸሓ​ፊ​ውም ዕዝራ ስለ​ዚህ ነገር በተ​ሠራ በዕ​ን​ጨት መረ​ባ​ርብ ላይ ቆሞ ነበር፤ በአ​ጠ​ገቡ መቲ​ትያ፥ ሰምያ፥ ሐና​ንያ፤ ኦርያ፥ ሕል​ቅያ፥ መዕ​ሢያ በቀኙ በኩል፥ ፈድያ፥ ሚሳ​ኤል፥ ሚል​ክያ፥ ሐሱም፥ ሐስ​በ​ዳና፥ ዘካ​ር​ያስ፥ ሜሱ​ላም በግ​ራው በኩል ቆመው ነበር።


“ለራሴ ሰፊ ቤት፥ ትል​ቅም ሰገ​ነት እሠ​ራ​ለሁ ለሚል፥ መስ​ኮ​ት​ንም ለሚ​ያ​ወጣ፥ በዝ​ግ​ባም ሥራ ለሚ​ያ​ስ​ጌጥ፥ በቀይ ቀለ​ምም ለሚ​ቀ​ባው ወዮ​ለት፤


በዚያ ጊዜም የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ሠራ​ዊት ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ከብቦ ነበር፤ ነቢዩ ኤር​ም​ያ​ስም በይ​ሁዳ ንጉሥ ቤት በነ​በ​ረው በግ​ዞት ቤት አደ​ባ​ባይ ታስሮ ነበር።


ኤር​ም​ያስ ገና በግ​ዞት ቤት አደ​ባ​ባይ ታስሮ ሳለ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ሁለ​ተኛ ጊዜ እን​ዲህ ሲል መጣ​ለት፦


ንጉ​ሡም ሴዴ​ቅ​ያስ አዘዘ፤ ኤር​ም​ያ​ስ​ንም በግ​ዞት ቤቱ ቅጥር ግቢ አኖ​ሩት፤ እን​ጀ​ራም ሁሉ ከከ​ተማ እስ​ኪ​ጠፋ ድረስ ዕለት ዕለት አንድ አንድ እን​ጀራ ከውጪ ጋጋ​ሪ​ዎች እያ​መጡ ይሰ​ጡት ነበር። እን​ዲ​ሁም ኤር​ም​ያስ በግ​ዞት ቤት ቅጥር ግቢ ተቀ​ምጦ ነበር።


ኤር​ም​ያ​ስ​ንም በገ​መዱ ጐተ​ቱት፤ ከጕ​ድ​ጓ​ድም አወ​ጡት፤ ኤር​ም​ያ​ስም በግ​ዞት ቤት አደ​ባ​ባይ ተቀ​መጠ።


ከለ​ዳ​ው​ያ​ንም የን​ጉ​ሡ​ንና የሕ​ዝ​ቡን ቤቶች በእ​ሳት አቃ​ጠሉ፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ቅጥር አፈ​ረሱ።


አንተም የመንጋ ግንብ ሆይ፥ የጽዮን ሴት ልጅ አምባ፥ ወደ አንተ ትመጣለች፥ የቀደመችው ግዛት፥ የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ መንግሥት ትደርሳለች።


跟着我们:

广告


广告