ነህምያ 3:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 በአጠገቡም የመሴፋ ገዢ የኢያሱ ልጅ አዙር በማዕዘኑ አጠገብ በመወጣጫው ግንብ አንጻር ያለውን ሌላውን ክፍል ሠራ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም19 ከርሱም ቀጥሎ ወደ ጦር መሣሪያ ግምጃ ቤት በሚያወጣውና እስከ ማእዘኑ በሚደርሰው ትይዩ ያለውን ሌላ ክፍል የምጽጳ ገዥ የኢያሱ ልጅ ኤጽር መልሶ ሠራ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 በአጠገቡ የሚጽጳ ገዢ የኢያሱ ልጅ ዔዜር በግንቡ መደገፊያ ወደ ጦር መሣሪያ ግምጃ ቤት መወጣጫ ፊት ለፊት ያለውን ሁለተኛውን ክፍል አደሰ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 የምጽጳ ወረዳ ገዥ የሆነው የኢያሱ ልጅ ዔዜር በጦር መሣሪያው ግምጃ ቤት ፊት ለፊት ያለውን እስከ ቅጽሩ መመለሻ ማእዘን ድረስ ያለውን ሁሉ ሠራ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 በአጠገቡም የምጽጳ አለቃ የኢያሱ ልጅ ኤጽር በማዕዘኑ አጠገብ በጦር መሣሪያ ቤት አንጻር ሌላውን ክፍል አደሰ። 参见章节 |