Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ነህምያ 3:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ሐኖ​ንና የዘ​ናን ሰዎ​ችም የሸ​ለ​ቆ​ውን በር አደሱ፤ ሠሩት፤ ሳን​ቃ​ዎ​ቹ​ንም አቆሙ፥ ቍል​ፎ​ቹ​ንና መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንም አደ​ረጉ፤ ደግ​ሞም እስከ ጕድፍ መጣያ በር ድረስ አንድ ሺህ ክንድ የሚ​ሆን ቅጥር ሠሩ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 “የሸለቆ በር” ተብሎ የሚጠራውን የሐኖንና የዛኖ ነዋሪዎች ዐደሱት፤ መልሰው ሠሩት፤ ከሠሩትም በኋላ መዝጊያዎቹን በየቦታቸው አኖሩ፤ መወርወሪያዎቹንና መቀርቀሪያዎቹንም አበጁ። እንዲሁም የቈሻሻ መጣያ በር ተብሎ እስከሚጠራው ድረስ ያለውን አንድ ሺሕ ክንድ ቅጥር መልሰው ሠሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ሐኑንና የዛኖሐ ሰዎችም “የሸለቆ በር” አደሱ፤ መልሰው ሠሩት፥ ሳንቃዎቹንም አቆሙ፥ ቁልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም አበጁ፤ ደግሞም እስከ “የፍግ በር” ድረስ አንድ ሺህ ክንድ የሚሆን ቅጥር ሠሩ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ሐኑንና የዛኖሐ ነዋሪዎች ተባብረው የሸለቆውን ቅጽር በር በማደስ ሠሩ፤ ለቅጽር በሩም መዝጊያዎችን አቁመው ቊልፎችንና መወርወሪያዎችን አበጁለት፤ እስከ ጒድፍ መጣያ ቅጽር በር 440 ሜትር ርዝመት ያለውንም ቅጽር እንደገና ሠሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ሐኖንና የዛኖዋ ሰዎችም የሸለቆውን በር አደሱ፥ ሠሩት፥ ሳንቃዎቹንም አቆሙ፥ ቁልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም አደረጉ፥ ደግሞም እስከ ጉድፍ መጣያው በር ድረስ አንድ ሺህ ክንድ የሚሆን ቅጥር ሠሩ።

参见章节 复制




ነህምያ 3:13
7 交叉引用  

ሚስቱ አይ​ሂ​ዳም የጌ​ዶ​ርን አባት ያሬ​ድን፥ የሦ​ኮ​ንም አባት ሔቤ​ርን፥ የዛ​ኖ​ዋ​ንም አባት ይቁ​ቲ​ኤ​ልን ወለ​ደች። እነ​ዚህ ሞሬድ ያገ​ባት የፈ​ር​ዖን ልጅ የቢ​ትያ ልጆች ናቸው።


ዖዝ​ያ​ንም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በማ​ዕ​ዘኑ በርና በሸ​ለ​ቆው በር፥ ቅጥ​ሩም በዞ​ረ​በት ማዕ​ዘን አጠ​ገብ ግን​ቦ​ችን ሠርቶ መሸ​ጋ​ቸው።


በዛ​ኖህ፥ በዓ​ዶ​ላም፥ በመ​ን​ደ​ሮ​ቻ​ቸ​ውም፥ በለ​ኪ​ሶና በእ​ር​ሻ​ዎ​ችዋ፥ በዓ​ዜ​ቃና በመ​ን​ደ​ሮ​ችዋ ተቀ​መጡ። እን​ዲሁ ከቤ​ር​ሳ​ቤህ ጀምሮ እስከ ሄኖም ሸለቆ ድረስ ሰፈሩ።


በሸ​ለ​ቆ​ውም በር ወጣሁ፤ ወደ በለ​ስም ምን​ጭና ወደ ጕድፍ መጣ​ያው በር ሄድሁ፤ የፈ​ረ​ሰ​ው​ንም የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ቅጥር፥ በእ​ሳ​ትም የተ​ቃ​ጠ​ሉ​ትን በሮ​ች​ዋን ተመ​ለ​ከ​ትሁ።


በሌ​ሊ​ትም በፈ​ፋው በኩል ወጥቼ ቅጥ​ሩን ተመ​ለ​ከ​ትሁ፤ በሸ​ለ​ቆ​ውም በር ገባሁ፤ እን​ዲ​ሁም ተመ​ለ​ስሁ።


ራሜ፥ ጣኖ፥ ኢዱ​ቶት፥ መሐ​ንስ፤


ኢያ​ሬ​ዬል፥ ኢያ​ሪ​ቅም፥ ዘቃ​ይ​ንም፤


跟着我们:

广告


广告