Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ነህምያ 2:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ሖሮ​ና​ዊ​ውም ሰን​ባ​ላጥ፥ አገ​ል​ጋ​ዩም አሞ​ና​ዊው ጦቢያ፥ ዓረ​ባ​ዊ​ውም ጌሳም በሰሙ ጊዜ በን​ቀት ሳቁ​ብን፤ ቀላል አድ​ር​ገ​ው​ንም ወደ እኛ መጡና፥ “ይህ የም​ታ​ደ​ር​ጉት ነገር ምን​ድን ነው? በውኑ በን​ጉሡ ላይ ትሸ​ፍቱ ዘንድ ትወ​ድ​ዳ​ላ​ች​ሁን?” አሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ነገር ግን ሖሮናዊው ሰንባላጥ፣ አሞናዊው ሹም ጦቢያና ዐረባዊው ጌሳም ይህን ሲሰሙ አፌዙብን፤ አንቋሸሹንም፤ እንዲሁም፣ “የምታደርጉት ይህ ምንድን ነው? በንጉሡ ላይ ልታምፁ ትፈልጋላችሁን?” አሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ሖሮናዊው ሳንባላጥ፥ አገልጋይ የሆነው አሞናዊው ጦብያና ዓረባዊው ጌሻም ይህንን ሰሙ፤ አፌዙብን፤ አንቋሸሹንም፤ “ይህ የምታደርጉት ነገር ምንድነው? በንጉሡ ላይ እያመፃችሁ ነውን?” አሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ነገር ግን ሰንባላጥና ጦቢያ እንዲሁም ጌሼም ተብሎ የሚጠራው አንድ የዐረብ ተወላጅ እኛ ያወጣነውን የሥራ ዕቅድ በሰሙ ጊዜ በእኛ ላይ እየዘበቱ በመሳቅ “ይህ የምትሠሩት ሥራ ምንድን ነው? ወይስ በንጉሠ ነገሥቱ ላይ ማመፅ ትፈልጋላችሁን?” ሲሉ ጠየቁን።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ሖሮናዊውም ሰንባላጥ፥ ባሪያውም አሞናዊው ጦብያ፥ ዓረባዊዉም ጌሳም በሰሙ ጊዜ በንቀት ሳቁብን፤ ቀላል አድርገውንም፦ “ይህ የምታደርጉት ነገር ምንድር ነው? በውኑ በንጉሡ ላይ ትሸፍቱ ዘንድ ትወድዳላችሁን?” አሉ።

参见章节 复制




ነህምያ 2:19
22 交叉引用  

ከዋ​ነ​ኛ​ውም ካህን ከኤ​ል​ያ​ሴብ ልጅ ከዮ​ዳሔ ልጆች አንዱ ለሐ​ሮ​ና​ዊው ለሰ​ን​ባ​ላጥ አማች ነበረ፤ ከእ​ኔም ዘንድ አባ​ረ​ር​ሁት።


ሖሮ​ና​ዊ​ውም ሰን​ባ​ላ​ጥና አገ​ል​ጋዩ አሞ​ና​ዊው ጦብያ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መል​ካ​ምን ነገር የሚሻ ሰው እንደ መጣ በሰሙ ጊዜ እጅግ ተበ​ሳጩ።


ሰን​ባ​ላ​ጥም ቅጥ​ሩን እንደ ሠራን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቈጣ፤ ተበ​ሳ​ጨም፤ በአ​ይ​ሁ​ድም ሳቀ​ባ​ቸው።


“አን​ተና አይ​ሁድ ዓመፃ እን​ድ​ታ​ስቡ፥ ስለ​ዚ​ህም ቅጥ​ሩን እን​ድ​ት​ሠራ፥ ንጉ​ሣ​ቸ​ውም ትሆን ዘንድ እን​ድ​ት​ወ​ድድ በአ​ሕ​ዛብ ዘንድ ተሰ​ም​ቶ​አል።


እነ​ር​ሱም ሁሉ ሥራው እን​ዳ​ይ​ፈ​ጸም፥ “እጃ​ቸው ይደ​ክ​ማል” ብለው አስ​ፈ​ራ​ሩን፤ ስለ​ዚ​ህም እጆ​ችን አበ​ረ​ታሁ።


“አሁን ግን በዕ​ድሜ ከእኔ የሚ​ያ​ንሱ ለመ​ዘ​ባ​በት በእኔ ላይ ሳቁ፤ አባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን የና​ቅ​ሁ​ባ​ቸ​ውና እንደ መን​ጋዬ ውሾች ያል​ቈ​ጠ​ር​ኋ​ቸው ዛሬ ለብ​ቻ​ቸው ይገ​ሥ​ጹ​ኛል።


በውኃ ባሰ​ጠ​ሙን ነበር ብዬ በተ​ጠ​ራ​ጠ​ርሁ ነበር፤


የኀ​ያ​ላን አም​ላክ አቤቱ፥ በባ​ሪ​ያህ ጸሎት ላይ እስከ መቼ ትቈ​ጣ​ለህ?


ጀር​ባ​ውን ከመ​ስ​ገ​ጃ​ቸው መለሰ፥ እጆ​ቹም በቅ​ር​ጫት ተገዙ።


በመ​ከ​ራህ ጊዜ ጠራ​ኸኝ፥ አዳ​ን​ሁ​ህም፥ በተ​ሰ​ወረ ዐው​ሎም መለ​ስ​ሁ​ልህ፥ በክ​ር​ክር ውኃ ዘን​ድም ፈተ​ን​ሁህ።


በም​ክ​ርና በከ​ን​ፈር ንግ​ግር ጦር​ነት ይሆ​ና​ልን? አሁ​ንም በእኔ ላይ ያመ​ፅ​ኸው በማን ተማ​ም​ነህ ነው?


በተ​ና​ገ​ርሁ ቍጥር እጮ​ኻ​ለሁ፤ ግፍና ጥፋት ብዬ እጠ​ራ​ለሁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ቀኑን ሁሉ ስድ​ብና ዋዛ ሆኖ​ብ​ኛ​ልና።


እስ​ማ​ኤ​ልም በመ​ሴፋ የነ​በ​ረ​ውን የሕ​ዝ​ቡን ቅሬታ ሁሉ፥ የን​ጉ​ሡን ሴቶች ልጆች፥ የአ​ዛ​ዦች አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳን ለአ​ኪ​ቃም ልጅ ለጎ​ዶ​ል​ያስ የሰ​ጠ​ውን በመ​ሴፋ የቀ​ሩ​ትን ሕዝብ ሁሉ መለሰ፤ የና​ታ​ን​ያም ልጅ እስ​ማ​ኤል ወደ አሞን ልጆች ይሄድ ዘንድ ተነሣ።


“ብላቴናይቱ ተኝታለች እንጂ አልሞተችምና ፈቀቅ በሉ፤” አላቸው። በጣምም ሳቁበት።


በጣምም ሳቁበት። እርሱ ግን ሁሉን አስወጥቶ የብላቴናይቱን አባትና እናት ከእርሱ ጋር የነበሩትንም ይዞ ብላቴናይቱ ወዳለችበት ገባ።


እን​ዲ​ህም እያሉ ይከ​ስ​ሱት ጀመር፥ “ይህ ሰው ለቄ​ሣር ግብር እን​ዳ​ይ​ሰጡ ሲከ​ለ​ክ​ልና ሕዝ​ቡን ሲያ​ሳ​ምፅ፥ ራሱ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ክር​ስ​ቶ​ስን ሲያ​ደ​ርግ አገ​ኘ​ነው።”


ስለ​ዚ​ህም ጲላ​ጦስ ሊፈ​ታው ወድዶ ነበር፤ አይ​ሁድ ግን፥ “ይህን ከፈ​ታ​ኸው የቄ​ሣር ወዳጅ አይ​ደ​ለ​ህም፤ ራሱን ንጉሥ የሚ​ያ​ደ​ርግ ሰው ሁሉ በቄ​ሣር ላይ የሚ​ያ​ምፅ ነውና” ብለው ጮሁ።


ይህን ሰው ሲሳ​ደ​ብና ወን​ጀል ሲሠራ፥ አይ​ሁ​ድ​ንም ሁሉ በየ​ሀ​ገሩ ሲያ​ውክ፥ ናዝ​ራ​ው​ያን የተ​ባ​ሉት ወገ​ኖች የሚ​ያ​ስ​ተ​ም​ሩ​ት​ንም ክህ​ደት ሲያ​ስ​ተ​ምር አግ​ኝ​ተ​ነ​ዋል።


የገ​ረ​ፉ​አ​ቸው፥ የዘ​በ​ቱ​ባ​ቸ​ውና ያሠ​ሩ​አ​ቸው ወደ ወህኒ ያገ​ቡ​አ​ቸ​ውም አሉ።


跟着我们:

广告


广告