Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ነህምያ 13:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ደግ​ሞም በዚያ ወራት የአ​ዛ​ጦ​ን​ንና የአ​ሞ​ንን፥ የሞ​ዓ​ብ​ንም ሴቶች ያገ​ቡ​ትን አይ​ሁድ አየሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 በእነዚያም ቀናት የአሽዶድን፣ የአሞንንና የሞዓብን ሴቶች ያገቡ አይሁድ አገኘሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ደግሞም በዚያ ወራት የአዛጦንና የአሞንን የሞዓብንም ሴቶች ያገቡትን አይሁድ አየሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 በዚያው ወራት ደግሞ ከአይሁድ ሕዝብ ብዙዎቹ የአሽዶድ፥ የዐሞንና የሞአብ አገር ሴቶችን ማግባታቸውን ተገነዘብኩ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ደግሞም በዚያ ወራት የአዛጦንና የአሞንን የሞዓብንም ሴቶች ያገቡትን አይሁድ አየሁ።

参见章节 复制




ነህምያ 13:23
16 交叉引用  

ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞን ሴቶ​ችን ይወድ ነበር፥ ከባ​ዕ​ዳን ሕዝ​ብም የፈ​ር​ዖ​ንን ልጅ፥ ሞዓ​ባ​ው​ያ​ት​ንና አሞ​ና​ው​ያ​ትን፥ ሶር​ያ​ው​ያ​ት​ንና ሲዶ​ና​ው​ያ​ትን፥ ኤዶ​ማ​ው​ያ​ት​ንና አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ት​ንም፥ ኬጤ​ዎ​ና​ው​ያ​ት​ንም፦ ሚስ​ቶ​ችን አገባ።


ካህ​ኑም ዕዝራ ተነ​ሥቶ፥ “ተላ​ል​ፋ​ች​ኋል፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን በደል ታበዙ ዘንድ እን​ግ​ዶ​ችን ሴቶች አግ​ብ​ታ​ች​ኋል።


እነ​ዚህ ሁሉ እን​ግ​ዶ​ቹን ሚስ​ቶች አግ​ብ​ተው ነበር፤ ከእ​ነ​ዚ​ህም ሚስ​ቶች ዐያ​ሌ​ዎቹ ልጆ​ችን ወል​ደው ነበር።


ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ን​ንም ለም​ድር አሕ​ዛብ አን​ሰ​ጥም፤ ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ለል​ጆ​ቻ​ችን አን​ወ​ስ​ድም፤


የም​ድ​ር​ንም አሕ​ዛብ ሸቀ​ጥና ልዩ ልዩ እህል ሊገ​በዩ በሰ​ን​በት ቀን ቢያ​መጡ በሰ​ን​በት ወይም በተ​ቀ​ደ​ሰው ቀን ከእ​ነ​ርሱ አን​ገ​ዛም፤ ሰባ​ተ​ኛ​ው​ንም ዓመት እና​ከ​ብ​ራ​ለን፤ ከሰ​ውም ዕዳ ማስ​ከ​ፈ​ልን እን​ተ​ዋ​ለን።


በዚ​ያም ቀን የሙ​ሴን መጽ​ሐፍ በሕ​ዝቡ ጆሮ አነ​በቡ፤ አሞ​ና​ው​ያ​ንና ሞዓ​ባ​ው​ያ​ንም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጉባኤ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እን​ዳ​ይ​ገቡ የሚል በዚያ አገኙ።


ከል​ጆ​ቻ​ቸ​ውም እኩ​ሌ​ቶቹ በአ​ዛ​ጦን ቋንቋ ይና​ገሩ ነበር፤ በሌ​ሎች ሕዝብ ቋንቋ የሚ​ና​ገ​ሩም ነበሩ፤ በአ​ይ​ሁ​ድም ቋንቋ መና​ገር አያ​ው​ቁም ነበር።


እን​ዲሁ እን​ግ​ዲህ ይህን ሁሉ ታላቅ ክፋት ስት​ሠሩ፥ እን​ግ​ዶ​ች​ንም ሴቶች በማ​ግ​ባት አም​ላ​ካ​ች​ንን ስት​በ​ድሉ አን​ስ​ማ​ባ​ችሁ።”


ሰን​ባ​ላ​ጥና ጦብ​ያም፥ ዓረ​ባ​ው​ያ​ንም፥ አሞ​ና​ው​ያ​ንም፥ አዛ​ጦ​ና​ው​ያ​ንም የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቅጥር እየ​ታ​ደሰ እንደ ሄደ፥ የፈ​ረ​ሰ​ውም ሊጠ​ገን እንደ ተጀ​መረ በሰሙ ጊዜ እጅግ ተቈጡ።


በዚህ ቀን የማ​ዝ​ዝ​ህን ነገር ጠብቅ፤ እነሆ፥ እኔ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ዊ​ውን፥ ከነ​ዓ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ኬጤ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ኤዌ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም ከፊ​ትህ አወ​ጣ​ለሁ።


ተጠ​ራ​ጣ​ሪ​ዎች አት​ሁኑ፤ ወደ​ማ​ያ​ምኑ ሰዎች አን​ድ​ነ​ትም አት​ሂዱ፤ ጽድ​ቅን ከኀ​ጢ​አት ጋር አንድ የሚ​ያ​ደ​ር​ጋት ማን ነው? ብር​ሃ​ን​ንስ ከጨ​ለማ ጋር የሚ​ቀ​ላ​ቅል ማን ነው?


“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልት​ወ​ር​ሳት ወደ​ም​ት​ገ​ባ​ባት ምድር ባመ​ጣህ ጊዜ፥ ከፊ​ት​ህም ብዙና ታላ​ላቅ አሕ​ዛ​ብን፥ ከአ​ንተ የበ​ለ​ጡ​ትን፥ የበ​ረ​ቱ​ት​ንም ሰባ​ቱን አሕ​ዛብ፥ ኬጤ​ዎ​ና​ዊ​ውን፥ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ከነ​ዓ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ኤዌ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም ባወጣ ጊዜ፥


እነርሱም ከሞዓባውያን ሴቶች ሚስት አገቡ፣ የአንዲቱ ስም ዖርፋ የሁለተኛይቱም ስም ሩት ነበረ። በዚያም አሥር ዓመት ያህል ተቀመጡ።


ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ወሰ​ዱ​አት፤ ከአ​ቤ​ኔ​ዜ​ርም ወደ አዛ​ጦን ይዘ​ዋት መጡ።


跟着我们:

广告


广告