ነህምያ 13:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)21 እኔም አስመሰከርሁባቸውና፥ “ከቅጥሩ ውጭ ለምን ታድራላችሁ? እንደ ገና ብታደርጉት እጆችን አነሣባችኋለሁ” አልኋቸው። ከዚያም ጊዜ ጀምሮ በሰንበት ቀን እንደ ገና አልመጡም። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም21 እኔ ግን፣ “ከቅጥሩ ውጭ የምታድሩት ለምንድን ነው? እንዲህ ያለውን ነገር ዳግመኛ ብታደርጉ እጄን አነሣባችኋለሁ” ስል አስጠነቀቅኋቸው፤ እነርሱም ከዚያ ጊዜ ጀምሮ በሰንበት ቀን አልመጡም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)21 እኔም አስመሰከርሁባቸውና፦ በቅጥሩ ውጭ ለምን ታድራላችሁ? እንደገና ብታደርጉት እጆቼን አነሣባችኋለሁ አልኋቸው። ከዚያም ወዲያ በሰንበት ቀን እንደገና አልመጡም። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም21 እኔም “ማለድ ብላችሁ ለመግባት በማሰብ በዚያ ማደራችሁ ጥቅም የለውም፤ እንዲህ ማድረጋችሁን የምትቀጥሉ ከሆነ በእናንተ ላይ የኀይል እርምጃ ለመውሰድ እገደዳለሁ” ብዬ አስጠነቀቅኋቸው፤ ከዚያን ጊዜም ጀምሮ በሰንበት ቀን መምጣታቸውን አቆሙ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)21 እኔም አስመሰከርሁባቸውና፦ በቅጥሩ ውጭ ለምን ታድራላችሁ? እንደ ገና ብታደርጉት እጆቼን አነሣባችኋለሁ አልኋቸው። ከዚያም ወዲያ በሰንበት ቀን እንደ ገና አልመጡም። 参见章节 |