Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ነህምያ 12:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 ካህ​ና​ቱና ሌዋ​ው​ያ​ኑም ራሳ​ቸ​ውን አነጹ፤ ሕዝ​ቡ​ንም፥ በረ​ኞ​ች​ንም ቅጥ​ሩ​ንም አነጹ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ካህናቱና ሌዋውያኑ በሥርዐቱ መሠረት ራሳቸውን ካነጹ በኋላ፣ ሕዝቡን፣ ቅጥሩንና በሮቹን አነጹ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ካህናቱና ሌዋውያኑም ራሳቸውን አነጹ፤ ሕዝቡን፥ በሮቹንና ቅጥሩንም አነጹ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 ካህናቱና ሌዋውያኑም ስለ ሕዝቡ ራሳቸው ስለ ከተማይቱ በሮችና ስለ ቅጽሩ የማንጻትን ሥርየት ፈጸሙ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 ካህናቱና ሌዋውያኑም ራሳቸውን አነጹ፥ ሕዝቡንም በሮቹንም ቅጥሩንም አነጹ።

参见章节 复制




ነህምያ 12:30
14 交叉引用  

ያዕ​ቆ​ብም ለቤተ ሰቡና ከእ​ርሱ ጋር ላሉት ሁሉ እን​ዲህ አለ፥ “ከእ​ና​ንተ ጋር ያሉ እን​ግ​ዶች አማ​ል​ክ​ትን ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ አስ​ወ​ግዱ፤ ንጹ​ሓ​ንም ሁኑ፤ ልብ​ሳ​ች​ሁ​ንም እጠቡ፤


የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም አም​ላክ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ያመጡ ዘንድ ካህ​ና​ቱና ሌዋ​ው​ያኑ ራሳ​ቸ​ውን አነጹ።


ነገር ግን ካህ​ናቱ ጥቂ​ቶች ነበ​ሩና የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ለመ​ግ​ፈፍ አይ​ች​ሉም ነበር፤ ስለ​ዚ​ህም ሌዋ​ው​ያን በቅን ልብ ከካ​ህ​ናት ይልቅ ይቀ​ደሱ ነበ​ርና ሥራው እስ​ኪ​ፈ​ጸም ድረስ፥ ካህ​ና​ቱም እስ​ኪ​ቀ​ደሱ ድረስ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ሌዋ​ው​ያን ያግ​ዙ​አ​ቸው ነበር።


እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ሌዋ​ው​ያን ሆይ፥ ስሙኝ፤ ራሳ​ች​ሁን አንጹ፤ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ሁ​ንም አም​ላክ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ቀድሱ፤ ርኩ​ስን ነገር ሁሉ ከመ​ቅ​ደሱ አስ​ወ​ግዱ።


ከም​ር​ኮም ተመ​ል​ሰው የመ​ጡት የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ይፈ​ልጉ ዘንድ ራሳ​ቸ​ውን ከም​ድር አሕ​ዛብ ርኵ​ሰት ለይ​ተው ወደ እነ​ርሱ መጥ​ተው የነ​በ​ሩት ሁሉ ፋሲ​ካ​ውን በሉ፤


ከቤት ጌል​ጋ​ልና ከጌባ፥ ከአ​ዝ​ማ​ዊ​ትም እርሻ መዘ​ም​ራኑ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ዙርያ ለራ​ሳ​ቸው መን​ደ​ሮች ሠር​ተ​ዋ​ልና።


ሌዋ​ው​ያ​ኑ​ንም ራሳ​ቸ​ውን እን​ዲ​ያ​ነጹ፥ መጥ​ተ​ውም በሮ​ቹን እን​ዲ​ጠ​ብቁ፥ የሰ​ን​በ​ት​ንም ቀን እን​ዲ​ቀ​ድሱ ነገ​ር​ኋ​ቸው። “አም​ላኬ ሆይ፥ ስለ​ዚህ ደግሞ አስ​በኝ፥ እንደ ምሕ​ረ​ት​ህም ብዛት ራራ​ልኝ” አልሁ።


ከእ​ን​ግዳ ነገ​ርም ሁሉ አነ​ጻ​ኋ​ቸው፤ ለካ​ህ​ና​ቱና ለሌ​ዋ​ው​ያ​ኑም ለእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው በየ​ሰ​ሞ​ና​ቸው፥


የግ​ብ​ዣ​ውም ቀኖች በተ​ፈ​ጸሙ ጊዜ ኢዮብ ይል​ክና ይቀ​ድ​ሳ​ቸው ነበር፤ በማ​ለ​ዳም ገሥ​ግሦ፦ ስለ ልጆቹ በቍ​ጥ​ራ​ቸው መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ርብ ነበር፤ አንድ ወይ​ፈን ስለ ነፍ​ሳ​ቸው የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ርብ ነበር፤ ኢዮብ፥ “ምና​ል​ባት ልጆቼ በል​ባ​ቸው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ክፉ ነገር ያስቡ ይሆ​ናል” ይል ነበ​ርና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ውረድ፤ ዛሬና ነገ ራሳ​ቸ​ውን ያንጹ፤ ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም ያጥቡ ዘንድ ሕዝ​ቡን እዘ​ዛ​ቸው።


ሕዝ​ቡ​ንም፥ “ለሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ተዘ​ጋጁ፤ ወደ ሴቶ​ቻ​ች​ሁም አት​ቅ​ረቡ” አለ።


ሊቀ ካህ​ናት ሁሉ ስለ ኀጢ​አት መባ​ንና መሥ​ዋ​ዕ​ትን ሊያ​ቀ​ርብ ከሰው ተመ​ርጦ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሆ​ነው ነገር ሁሉ ስለ ሰው ይሾ​ማ​ልና።


በዚ​ህም ምክ​ን​ያት ስለ ሕዝብ እን​ደ​ሚ​ያ​ቀ​ርብ እን​ዲሁ ስለ ራሱ ደግሞ መሥ​ዋ​ዕ​ትን ስለ ኀጢ​አት ማቅ​ረብ ይገ​ባ​ዋል።


跟着我们:

广告


广告