Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ነህምያ 10:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 ስለ አም​ላ​ካ​ች​ንም ቤት ሥራ ሁሉ በየ​ዓ​መቱ የሰ​ቅል ሢሶ እና​መጣ ዘንድ ሥር​ዐት በራ​ሳ​ችን ላይ እና​ደ​ር​ጋ​ለን።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 “በየዓመቱ ለእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት የሚሆን የሰቅል አንድ ሦስተኛ ለመስጠት ቃል እንገባለን፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 የምድሪቱ ሕዝቦች ሸቀጥ ወይም ልዩ ልዩ እህል ለመሸጥ በሰንበት ቀን ቢያመጡ፥ በሰንበት ወይም በተቀደሰ ቀን ከእነርሱ አንገዛም፤ በሰባተኛው ዓመትም ምድሪቱን እናሳርፋታለን፥ ዕዳንም ሁሉ እንሰርዛለን።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 በየዓመቱ ለቤተ መቅደሱ አገልግሎት የሚውል እያንዳንዳችን የጥሬ ብር አንድ ሦስተኛ እጅ በማምጣት እንሰጣለን።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32-33 ስለ አምላካችንም ቤት አገልግሎት፥ ስለ ገጸ ኅብስትም፥ ዘወትርም በሰንበትና በመባቻ ስለ ማቅረብ ስለ እህሉ ቁርባንና ስለሚቃጠል መሥዋዕት፥ ስለ በዓላትም፥ ስለ ተቀደሱትም ነገሮች፥ ለእስራኤልም ስለሚያስተሰርየው ስለ ኃጢአት መሥዋዕት፥ ስለ አምላካችንም ቤት ሥራ ሁሉ በየዓመቱ የሰቅል ሢሶ እናመጣ ዘንድ ትእዛዝ በራሳችን ላይ አደረግን።

参见章节 复制




ነህምያ 10:32
12 交叉引用  

ለሐ​ው​ልት ያቆ​ም​ኋት ይህ​ችም ድን​ጋይ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ትሆ​ን​ል​ኛ​ለች፤ ከሰ​ጠ​ኸ​ኝም ሁሉ ለአ​ንተ ከዐ​ሥር እጅ አን​ዱን እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።”


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤተ መቅ​ደስ ሕንጻ ወደ ኋላ እን​ዳ​ይል ዳዊት ከየ​ሀ​ገሩ በማ​ረ​ካ​ቸ​ውና በሰ​በ​ሰ​ባ​ቸው በቀ​ደ​ሳ​ቸ​ውም ላይ የተ​ሾሙ ናቸው።


በዚ​ያም ወራት በይ​ሁዳ በሰ​ን​በት ቀን የወ​ይን መጭ​መ​ቂ​ያን የሚ​ረ​ግ​ጡ​ትን፥ ነዶም የሚ​ከ​ም​ሩ​ትን፥ የወ​ይ​ኑን ጠጅና የወ​ይ​ኑን ዘለላ፤ በለ​ሱ​ንም፥ ልዩ ልዩም ዓይ​ነት ሸክም በአ​ህ​ዮች ላይ የሚ​ጭ​ኑ​ትን፥ በሰ​ን​በ​ትም ቀን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም የሚ​ያ​ስ​ገ​ቡ​ትን አየሁ፤ ገበ​ያም ባደ​ረ​ጉ​በት ቀን አስ​መ​ሰ​ከ​ር​ሁ​ባ​ቸው።


አባ​ቶ​ቻ​ችሁ እን​ደ​ዚህ አድ​ር​ገው አል​ነ​በ​ረ​ምን? አም​ላ​ካ​ች​ንስ ይህን ክፉ ነገር ሁሉ በእ​ኛና በዚች ከተማ ላይ አም​ጥቶ አል​ነ​በ​ረ​ምን? እና​ን​ተስ ሰን​በ​ትን በማ​ር​ከ​ሳ​ችሁ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ መዓ​ትን ትጨ​ም​ራ​ላ​ችሁ?”


እኔም አስ​መ​ሰ​ከ​ር​ሁ​ባ​ቸ​ውና፥ “ከቅ​ጥሩ ውጭ ለምን ታድ​ራ​ላ​ችሁ? እንደ ገና ብታ​ደ​ር​ጉት እጆ​ችን አነ​ሣ​ባ​ች​ኋ​ለሁ” አል​ኋ​ቸው። ከዚ​ያም ጊዜ ጀምሮ በሰ​ን​በት ቀን እንደ ገና አል​መ​ጡም።


እኔ ደግሞ፥ ወን​ድ​ሞ​ችም፥ ብላ​ቴ​ኖ​ችም ገን​ዘ​ብና እህል ለእ​ነ​ርሱ አበ​ድ​ረ​ናል፤ እባ​ካ​ችሁ፥ ይህን ወለድ እን​ተ​ው​ላ​ቸው።


የተ​ቀ​ደ​ሰ​ው​ንም ሰን​በ​ት​ህን አስ​ታ​ወ​ቅ​ሃ​ቸው፤ ትእ​ዛ​ዝ​ንና ሥር​ዐ​ትን፥ ሕግ​ንም በባ​ሪ​ያህ በሙሴ እጅ አዘ​ዝ​ሃ​ቸው።


በሰ​ባ​ተ​ኛው ዓመት ግን ተዋት፤ አሳ​ር​ፋ​ትም፤ የሕ​ዝ​ብ​ህም ድሆች ይበ​ሉ​ታል፤ እነ​ርሱ ያስ​ቀ​ሩ​ት​ንም የሜዳ እን​ስሳ ይብ​ላው። እን​ዲ​ሁም በወ​ይ​ን​ህና በወ​ይ​ራህ አድ​ርግ።


እግዚአብሔርን በእውነት በአገኘኸው ሀብትህ አክብረው። ከእውነተኛ ፍሬህም ሁሉ ቀዳምያቱን አግባለት።


ፈቃድ ካለም፥ ሰው በሚ​ቻ​ለው መጠን ቢሰጥ ይመ​ሰ​ገ​ናል፤ በማ​ይ​ቻ​ለ​ውም መጠን አይ​ደ​ለም።


跟着我们:

广告


广告