ነህምያ 10:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)31 የምድርንም አሕዛብ ሸቀጥና ልዩ ልዩ እህል ሊገበዩ በሰንበት ቀን ቢያመጡ በሰንበት ወይም በተቀደሰው ቀን ከእነርሱ አንገዛም፤ ሰባተኛውንም ዓመት እናከብራለን፤ ከሰውም ዕዳ ማስከፈልን እንተዋለን። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም31 “አሕዛብ ጎረቤቶቻችን በሰንበት ቀን ለመሸጥ ሸቀጣ ሸቀጥ ወይም እህል ቢያመጡ፣ በሰንበት ወይም በማናቸውም በተቀደሰ ቀን ከእነርሱ አንገዛም። በየሰባት ዓመቱም ምድሪቱን እናሳርፋለን፤ ዕዳንም ሁሉ እንሠርዛለን። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)31 ሴቶች ልጆቻችንን ለምድሪቱ ሕዝቦች አንሰጥም፥ ሴቶች ልጆቻቸውንም ለወንዶች ልጆቻችን አንወስድም፤ 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም31 የባዕዳን አገር ሕዝቦች በሰንበት ቀን ወይም በሌሎች በዓላት እህልም ሆነ ሌላ የንግድ ሸቀጥ ይዘው ቢመጡ፥ ከእነርሱ አንገዛም። በየሰባት ዓመት አንድ ጊዜ ምድሪቱን አናርስም፤ ያበደርነውንም ዕዳ ሁሉ እንሰርዛለን። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)31 የምድርን አሕዛብ ሸቀጥና ልዩ ልዩ እህል ሊገበዩ በሰንበት ቀን ቢያመጡ፥ በሰንበት ወይም በተቀደሰው ቀን ከእነርሱ አንገዛም፥ የሰባተኛውንም ዓመት ፍሬና ዕዳን ማስከፈል እንተዋለን ብለው ማሉ። 参见章节 |