ናሆም 2:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 መሳፍንቱን ያስባል፣ በአረማመዳቸው ይሰናከላሉ፣ ፈጥነው በቅጥርዋ ላይ ይወጣሉ፥ መጠጊያም ተዘጋጀለት። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም5 ምርጥ ተዋጊዎቹን ይጠራል፤ ዳሩ ግን መንገድ ላይ ይሰናከላሉ፤ ወደ ከተማዪቱ ቅጥር ይሮጣሉ፤ መከላከያ ጋሻውም በቦታው አለ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 ሰረገሎች በመንገድ ላይ ይከንፋሉ፥ በአደባባዮችም ወዲህና ወዲያ ይጣደፋሉ፤ መልካቸው እንደ ፋና ነው፥ እንደ መብረቅም ይወረወራሉ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 እርሱ የጦር ሹማምንቱን ይጠራል፤ እነርሱም እየተደናቀፉ ወደፊት ይመጣሉ፤ የጠላት ወታደሮች እየሮጡ ወደ ከተማይቱ ቅጽር ይወጣሉ፤ የሚወረወርባቸውንም ፍላጻ በትልቁ ጋሻቸው ይከላከላሉ። 参见章节 |