Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሚክያስ 3:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ከእግዚአብሔርም ዘንድ መልስ የለምና ባለ ራእዩቹ ያፍራሉ፥ ምዋርተኞችም ይዋረዳሉ፥ ሁሉም ከንፈራቸውን ይሸፍናሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ባለራእዮች ያፍራሉ፤ ጠንቋዮችም ይዋረዳሉ፤ ሁሉም ፊታቸውን ይሸፍናሉ፤ ከእግዚአብሔር መልስ የለምና።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ትንቢተኞች ይዋረዳሉ፥ ጠንቋዮችም ያፍራሉ፤ ሁሉም ከንፈራቸውን ይሸፍናሉ፤ ከእግዚአብሔር ዘንድ መልስ የለምና።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ‘ራእይ እናያለን፥ ትንቢት እንናገራለን’ የሚሉ ሁሉ ስለማይሳካላቸው ይዋረዳሉ፤ እግዚአብሔርም መልስ ስለማይሰጣቸው ከማፈራቸው የተነሣ ፊታቸውን በእጃቸው ሸፍነው ይሄዳሉ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ከእግዚአብሔርም ዘንድ መልስ የለምና ባለ ራእዩቹ ያፍራሉ፥ ምዋርተኞችም ይዋረዳሉ፥ ሁሉም ከንፈራቸውን ይሸፍናሉ።

参见章节 复制




ሚክያስ 3:7
19 交叉引用  

እኔ ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ደስ ይለ​ኛል፥ ለያ​ዕ​ቆ​ብም አም​ላክ እዘ​ም​ራ​ለሁ፥


ጠን​ቋ​ዮ​ችም ቍስል ስለ ነበ​ረ​ባ​ቸው በሙሴ ፊት መቆም አል​ቻ​ሉም፤ ቍስል ጠን​ቋ​ዮ​ች​ንና ግብ​ፃ​ው​ያ​ንን ሁሉ ይዞ​አ​ቸው ነበ​ርና።


በሟ​ርት ሙት እና​ስ​ነ​ሣ​ለን የሚ​ሉ​ትን፥ ከል​ባ​ቸ​ውም አን​ቅ​ተው ሐሰት የሚ​ና​ገ​ሩ​ትን ሰዎች ምል​ክት የሚ​ለ​ውጥ ማን ነው? ጥበ​በ​ኞ​ቹ​ንም ወደ ኋላ ይመ​ል​ሳል፤ ምክ​ራ​ቸ​ው​ንም ስን​ፍና ያደ​ር​ጋል።


እነ​ር​ሱም፥ “ሕግ ከካ​ህን፥ ምክ​ርም ከጠ​ቢብ፥ ቃልም ከነ​ቢይ አይ​ጠ​ፋ​ምና ኑ፤ በኤ​ር​ም​ያስ ላይ ምክ​ርን እን​ም​ከር። ኑ፤ በም​ላስ እን​ም​ታው፤ ቃሉ​ንም ሁሉ አና​ዳ​ምጥ” አሉ።


በቀ​ስታ ተክዝ፤ ነገር ግን የሙ​ታ​ንን ልቅሶ አታ​ል​ቅስ፤ መጠ​ም​ጠ​ሚ​ያ​ህን በራ​ስህ ላይ አድ​ርግ፤ ጫማ​ህ​ንም በእ​ግ​ርህ አጥ​ልቅ፤ ከን​ፈ​ሮ​ች​ህ​ንም አት​ሸ​ፍን፤ የዕ​ዝን እን​ጀ​ራ​ንም አት​ብላ።”


እኔም እን​ዳ​ደ​ረ​ግሁ እና​ንተ ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ፤ በአ​ን​ደ​በ​ታ​ቸው አት​ጽ​ና​ኑም፤ የዕ​ዝን እን​ጀ​ራ​ንም አት​በ​ሉም።


“የለ​ምጽ ደዌ ያለ​በት ሰው ልብሱ የተ​ቀ​ደደ ይሁን፤ ራሱም የተ​ገ​ለጠ ይሁን፤ ከን​ፈ​ሩ​ንም ይሸ​ፍን፤ ርኩስ ይባ​ላል።


“እነሆ በም​ድር ላይ ራብን የም​ሰ​ድ​ድ​በት ዘመን ይመ​ጣል፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እር​ሱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ከመ​ስ​ማት እንጂ እን​ጀ​ራን ከመ​ራ​ብና ውኃን ከመ​ጠ​ማት አይ​ደ​ለም።


የዚያን ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ይጮኻሉ፥ እርሱም አይሰማቸውም፥ ሥራቸውንም ክፉ አድርገዋልና በዚያን ጊዜ ፊቱን ከእነርሱ ይሰውራል።


አሕዛብ አይተው በጕልበታቸው ሁሉ ያፍራሉ፥ እጃቸውን በአፋቸው ላይ ያኖራሉ፥ ጆሮአቸውም ትደነቍራለች፥ እንደ እባብም መሬት ይልሳሉ፥


በዚያም ቀን ነቢያቱ ሁሉ ትንቢትን ሲናገሩ እያንዳንዱ ስለ ራእዩ ያፍራል፣ ያታልሉም ዘንድ የማቅ ልብስ አይለብሱም።


ሳኦ​ልም፥ “ልው​ረ​ድና ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ልከ​ተ​ልን? በእ​ስ​ራ​ኤ​ልስ እጅ አሳ​ል​ፈህ ትሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለ​ህን?” ብሎ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠየ​ቀው። በዚያ ቀን ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አል​መ​ለ​ሰ​ለ​ትም።


ሳሙ​ኤ​ልም ሳኦ​ልን፥ “ለምን አወ​ክ​ኸኝ? ለም​ንስ አስ​ነ​ሣ​ኸኝ?” አለው። ሳኦ​ልም መልሶ፥ “ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ይወ​ጉ​ኛ​ልና እጅግ ተጨ​ን​ቄ​አ​ለሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእኔ ርቆ​አል፤ በነ​ቢ​ያት ወይም በሕ​ልም አላ​ሚ​ዎች አል​መ​ለ​ሰ​ል​ኝም፤ ስለ​ዚ​ህም የማ​ደ​ር​ገ​ውን ታስ​ታ​ው​ቀኝ ዘንድ ጠራ​ሁህ” አለው።


ሳኦ​ልም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ጠየቀ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሕ​ልም አላ​ሚ​ዎች፥ ወይም በነ​ጋ​ሪ​ዎች፥ ወይም በነ​ቢ​ያት አል​መ​ለ​ሰ​ለ​ትም።


ቀድሞ ነቢ​ዩን ባለ ራእይ ይሉት ነበ​ርና አስ​ቀ​ድሞ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ሰው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለመ​ጠ​የቅ ሲሄድ፦ ኑ፤ ወደ ባለ ራእይ እን​ሂድ ይል ነበር።”


跟着我们:

广告


广告