Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ማቴዎስ 4:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ናዝሬትንም ትቶ በዛብሎንና በንፍታሌም አገር በባሕር አጠገብ ወደ አለችው ወደ ቅፍርናሆም መጥቶ ኖረ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 የናዝሬትንም ከተማ ትቶ፣ በዛብሎንና በንፍታሌም አካባቢ በባሕሩ አጠገብ በምትገኘው በቅፍርናሆም ከተማ ሄዶ መኖር ጀመረ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ናዝሬትንም ትቶ በዛብሎንና በንፍታሌም ክልል ወደ አለችው በባሕር አጠገብ ወደምትገኝ ወደ ቅፍርናሆም መጥቶ ኖረ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 የናዝሬትንም ከተማ ትቶ፥ በዛብሎንና በንፍታሌም አውራጃ በገሊላ ባሕር አጠገብ ወደምትገኘው ወደ ቅፍርናሆም ከተማ መጥቶ ኖረ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ናዝሬትንም ትቶ በዛብሎንና በንፍታሌም አገር በባሕር አጠገብ ወደ አለችው ወደ ቅፍርናሆም መጥቶ ኖረ።

参见章节 复制




ማቴዎስ 4:13
17 交叉引用  

አንቺም ቅፍርናሆም፥ እስከ ሰማይ ከፍ አልሽን? ወደ ሲኦል ትወርጃለሽ፤ በአንቺ የተደረገው ተአምራት በሰዶም ተደርጎ ቢሆን፥ እስከ ዛሬ በኖረች ነበርና።


ወደ ቅፍርናሆምም በመጡ ጊዜ ግብር የሚቀበሉ ሰዎች ወደ ጴጥሮስ ቀረቡና “መምህራችሁ ሁለቱን ዲናር አይገብርምን?” አሉት።


በነቢዩም በኢሳይያስ እንዲህ የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሆነ፤


ምድርና የንፍታሌም ምድር፥ የባሕር መንገድ፥ በዮርዳኖስ ማዶ፥ የአሕዛብ ገሊላ፤


በታንኳም ገብቶ ተሻገረና ወደ ገዛ ከተማው መጣ።


ወደ ቅፍርናሆምም ገቡ፤ ወዲያውም በሰንበት ወደ ምኵራብ ገብቶ አስተማረ።


ከጥቂት ቀን በኋላ ወደ ቅፍርናሆም ደግሞ ገብቶ በቤት እንደ ሆነ ተሰማ።


አን​ቺም ቅፍ​ር​ና​ሆም እስከ ሰማይ ድረስ ከፍ ከፍ ብትዪ እስከ ሲኦል ትወ​ር​ጃ​ለሽ።


እር​ሱም፥ “በውኑ ባለ መድ​ኀ​ኒት ራስ​ህን አድን፤ በቅ​ፍ​ር​ና​ሆም ያደ​ረ​ግ​ኸ​ው​ንና የሰ​ማ​ነ​ውን ሁሉ በዚ​ህም በሀ​ገ​ርህ ደግሞ አድ​ርግ ብላ​ችሁ ይህ​ችን ምሳሌ ትመ​ስ​ሉ​ብ​ኛ​ላ​ችሁ” አላ​ቸው።


ከዚ​ህም በኋላ እር​ሱና እናቱ፥ ወን​ድ​ሞ​ቹና ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ወደ ቅፍ​ር​ና​ሆም ወረዱ፤ በዚ​ያም ብዙ ያይ​ደለ ጥቂት ቀን ተቀ​መጡ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ውኃ​ውን የወ​ይን ጠጅ ወደ አደ​ረ​ገ​በት የገ​ሊላ ክፍል ወደ​ም​ት​ሆን ወደ ቃና ዳግ​መኛ ሄደ። በቅ​ፍ​ር​ና​ሆም ልጁ የታ​መ​መ​በት የን​ጉሥ ወገን የሆነ አንድ ሰው ነበረ፤


ወደ ታን​ኳም ወጡ፤ ወደ ባሕር ማዶ ወደ ቅፍ​ር​ና​ሆ​ምም ሄዱ፤ እነ​ሆም፥ ፈጽሞ ጨለማ ሆነ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ወደ እነ​ርሱ ገና አል​መ​ጣም ነበር።


እነ​ዚያ ሰዎ​ችም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ፥ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም በዚያ እን​ዳ​ል​ነ​በሩ ባዩ ጊዜ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ይፈ​ል​ጉት ዘንድ በእ​ነ​ዚያ ታን​ኳ​ዎች ገብ​ተው ወደ ቅፍ​ር​ና​ሆም መጡ።


በቅ​ፍ​ር​ና​ሆ​ምም በም​ኵ​ራብ ሲያ​ስ​ተ​ም​ራ​ቸው ይህን ተና​ገረ፤


跟着我们:

广告


广告