Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ማቴዎስ 21:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ወደ ኢየሩሳሌምም በገባ ጊዜ መላው ከተማ “ይህ ማን ነው?” ብሎ ተናወጠ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ኢየሩሳሌም በገባ ጊዜም ከተማዋ በመላ፣ “ይህ ማነው?” በማለት ታወከች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ወደ ኢየሩሳሌም በገባ ጊዜ “ይህ ማን ነው?” ብሎ መላው ከተማ ተናወጠ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም በገባ ጊዜ የከተማው ሰዎች በሙሉ “ይህ ማን ነው?” በማለት ታወኩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ወደ ኢየሩሳሌምም በገባ ጊዜ መላው ከተማ፦ ይህ ማን ነው? ብሎ ተናወጠ።

参见章节 复制




ማቴዎስ 21:10
14 交叉引用  

መዓ​ዛዋ እንደ ከር​ቤና እንደ ዕጣን የሆ​ነው፥ ከልዩ የሽቱ ቅመም ሁሉ የሆ​ነው፥ ይህች ከም​ድረ በዳ እንደ ጢስ ዐምድ የወ​ጣ​ችው ማን ናት?


ከኤ​ዶ​ም​ያስ፥ ከባ​ሶራ የሚ​መጣ፥ ልብ​ሱም የቀላ፥ የሚ​መካ ኀይ​ለኛ፥ አለ​ባ​በ​ሱም ያማረ፥ ይህ ማን ነው? ስለ ጽድቅ የም​ከ​ራ​ከር፥ ስለ ማዳ​ንም የም​ፈ​ርድ እኔ ነኝ።


ንጉሡ ሄሮድስም ሰምቶ ደነገጠ፤ ኢየሩሳሌምም ሁሉ ከእርሱ ጋር፤


ሕዝቡም “ይህ ከገሊላ ናዝሬት የመጣ ነቢዩ ኢየሱስ ነው፤” አሉ።


የሚቀድሙትም ሕዝብ የሚከተሉትም “ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ! በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው! ሆሣዕና በአርያም!” እያሉ ይጮኹ ነበር።


“ይህን በማን ሥል​ጣን ታደ​ር​ጋ​ለህ? ይህ​ንስ እን​ድ​ታ​ደ​ርግ ማን ፈቀ​ደ​ልህ? እስኪ ንገ​ረን” አሉት።


ጻፎ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም፥ “የሚ​ሳ​ደብ ይህ ማን ነው? ከአ​ንዱ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀር ኀጢ​አ​ትን ማስ​ተ​ስ​ረይ ማን ይች​ላል?” ብለው ያስቡ ጀመር።


በማ​ዕዱ የተ​ቀ​መ​ጡ​ትም እርስ በር​ሳ​ቸው፥ “ኀጢ​አ​ትን የሚ​ያ​ስ​ተ​ሰ​ርይ ይህ ማነው?” ይሉ ጀመር።


ሄሮ​ድ​ስም፥ “እኔ የዮ​ሐ​ን​ስን ራስ አስ​ቈ​ረ​ጥሁ፤ እን​ግ​ዲህ ስለ እርሱ ሲወራ የም​ሰ​ማው ይህ ማነው?” አለ፤ ሊያ​የ​ውም ይሻ ነበር።


አይ​ሁ​ድም መል​ሰው፥ “ይህን የም​ታ​ደ​ርግ ምን ምል​ክት ታሳ​ያ​ለህ?” አሉት።


ሳው​ልም፥ “አቤቱ፥ አንተ ማነህ?” አለው፤ እር​ሱም፥ “አንተ የም​ታ​ሳ​ድ​ደኝ የና​ዝ​ሬቱ ኢየ​ሱስ ነኝ፤ በሾለ ብረት ላይ ብት​ቆም ለአ​ንተ ይብ​ስ​ሃል” አለው።


ሁለቱም እስከ ቤተ ልሔም ድረስ ሄዱ። ወደ ቤተ ልሔምም በደረሱ ጊዜ የከተማይቱ ሰዎች ሁሉ ስለ እነርሱ፦ ይህች ኑኃሚን ናትን? እያሉ ተንጫጩ።


ሳሙ​ኤ​ልም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ረ​ውን አደ​ረገ፤ ወደ ቤተ ልሔ​ምም መጣ። የከ​ተ​ማ​ውም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች በተ​ገ​ና​ኙት ጊዜ ደነ​ገጡ፥ “ነቢይ! የመ​ጣ​ኸው ለሰ​ላም ነውን?” አሉት።


跟着我们:

广告


广告