Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ማቴዎስ 16:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያንም ቀርበው ሲፈትኑት ከሰማይ ምልክት እንዲያሳያቸው ለመኑት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን ወደ ኢየሱስ ቀርበው ሊፈትኑት ከሰማይ ምልክት እንዲያሳያቸው ጠየቁት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን ሊፈትኑት መጡና ከሰማይ ምልክት እንዲያሳያቸው ጠየቁት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን ወደ ኢየሱስ መጡ፤ ሊፈትኑትም ፈልገው “ከሰማይ ተአምር አሳየን” ሲሉ ጠየቁት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያንም ቀርበው ሲፈትኑት ከሰማይ ምልክት እንዲያሳያቸው ለመኑት።

参见章节 复制




ማቴዎስ 16:1
33 交叉引用  

ፈሪሳውያን ግን ወጥተው እንዴት አድርገው እንዲያጠፉት ተማከሩበት።


በዚያን ጊዜ ጻፎችና ፈሪሳውያን ከኢየሩሳሌም ወደ ኢየሱስ ቀረቡና


ኢየሱስም “ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን እርሾ ተጠንቀቁና ተጠበቁ፤” አላቸው።


ፈሪሳውያንም ወደ እርሱ ቀረቡና ሲፈትኑት “ሰው በሆነው ምክንያት ሁሉ ሚስቱን ሊፈታ ተፈቅዶለታልን?” አሉት።


ስለዚህ ፈሪሳውያን ሄዱና እንዴት አድርገው በነገር እንዲያጠምዱት ተማከሩ።


ኢየሱስም ክፋታቸውን አውቆ “እናንተ ግብዞች፥ ስለ ምን ትፈትኑኛላችሁ?


በዚያን ቀን “ትንሣኤ ሙታን የለም፤” የሚሉ ሰዱቃውያን ወደ እርሱ ቀረቡ፤


“ጻፎችና ፈሪሳውያን በሙሴ ወንበር ተቀምጠዋል።


በማግሥቱም ከመዘጋጀት በኋላ በሚሆነው ቀን፥ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን ወደ ጲላጦስ ተሰበሰቡና


እላችኋለሁና ጽድቃችሁ ከጻፎችና ከፈሪሳውያን ጽድቅ ካልበለጠ፥ ወደ መንግሥተ ሰማያት ከቶ አትገቡም።


ፈሪሳውያንም አይተው ደቀ መዛሙርቱን “መምህራችሁ ከቀራጮችና ከኀጢአተኞች ጋር አብሮ ስለ ምን ይበላል?” አሉአቸው።


ፈሪሳውያንም ቀርበው “ሰው ሚስቱን ሊፈታ ተፈቅዶለታልን?” ብለው ሊፈትኑት ጠየቁት።


እርሱ ግን ግብዝነታቸውን አውቆ “ለምን ትፈትኑኛላችሁ? አየው ዘንድ አንድ ዲናር አምጡልኝ፤” አላቸው።


ትንሣኤ ሙታን የለም የሚሉ ሰዱቃውያን ወደ እርሱ መጥተው ጠየቁት እንዲህም አሉት


ከዚህ በኋላ አንድ ሕግ ዐዋቂ ሊፈ​ት​ነው ተነ​ሣና፥ “መም​ህር ሆይ፥ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን እወ​ርስ ዘንድ ምን ላድ​ርግ?” አለው።


ሌሎ​ችም ሊፈ​ት​ኑት ከእ​ርሱ ዘንድ ከሰ​ማይ ምል​ክ​ትን ይፈ​ልጉ ነበር።


ተን​ኰ​ላ​ቸ​ው​ንም ዐውቆ፥ “ለምን ትፈ​ት​ኑ​ኛ​ላ​ችሁ? ገን​ዘ​ቡን አሳ​ዩኝ” አላ​ቸው።


“ሙታን አይ​ነ​ሡም” ከሚሉ ከሰ​ዱ​ቃ​ው​ያ​ንም አን​ዳ​ንድ ሰዎች ወደ እርሱ መጡ።


በእ​ር​ሱም ላይ ምክ​ን​ያት ሊያ​ገኙ ሲፈ​ት​ኑት ይህን አሉ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ጐን​በስ ብሎ በጣቱ በም​ድር ላይ ጻፈ።


ሕዝ​ቡ​ንም ሲያ​ስ​ተ​ምሩ ሊቃነ ካህ​ና​ትና የቤተ መቅ​ደስ ሹም፥ ሰዱ​ቃ​ው​ያ​ንም መጡ።


ሊቀ ካህ​ና​ቱና አብ​ረ​ውት የነ​በ​ሩት የሰ​ዱ​ቃ​ው​ያን ወገ​ኖ​ችም ቀን​ተው በእ​ነ​ርሱ ላይ ተነሡ።


አይ​ሁድ ምል​ክ​ትን ይጠ​ይ​ቃሉ፤ የጽ​ርዕ ሰዎ​ችም ጥበ​ብን ይሻሉ።


跟着我们:

广告


广告