Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ማቴዎስ 15:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 ስለዚህም ሕዝቡ ድዳዎች ሲናገሩ፥ ጉንድሾችም ሲድኑ፥ አንካሶችም ሲሄዱ፥ ዕውሮችም ሲያዩ አይተው ተደነቁ፤ የእስራኤልንም አምላክ አከበሩ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 ሕዝቡም ዲዳው ሲናገር፣ ሽባው ደኅና ሲሆን፣ ዐንካሳው ቀጥ ብሎ ሲሄድ፣ ዐይነ ስውሩም ሲያይ ተመልክተው ተደነቁ፤ የእስራኤልንም አምላክ አመሰገኑ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ሕዝቡም ዲዳዎች ሲናገሩ፥ ሽባዎች ሲፈወሱ፥ አንካሶች ሲራመዱ፥ ዕውሮችም ሲያዩ አይተው ተደነቁ፤ የእስራኤልንም አምላክ አከበሩ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 ስለዚህ ሕዝቡ ድዳዎች ሲናገሩ፥ ሽባዎች ሲድኑ፥ አንካሳዎች በደኅና ሲራመዱ፥ ዕውሮች ሲያዩ በተመለከቱ ጊዜ ተደንቀው የእስራኤልን አምላክ አመሰገኑ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 ስለዚህም ሕዝቡ ዲዳዎች ሲናገሩ፥ ጉንድሾችም ሲድኑ፥ አንካሶችም ሲሄዱ፥ ዕውሮችም ሲያዩ አይተው ተደነቁ፤ የእስራኤልንም አምላክ አከበሩ።

参见章节 复制




ማቴዎስ 15:31
23 交叉引用  

አለ​ውም፥ “ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ስምህ እስ​ራ​ኤል ይባል እንጂ ያዕ​ቆብ አይ​ባል፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና ከሰው ጋር ታግ​ለህ በር​ት​ተ​ሃ​ልና።”


በዚ​ያም መሠ​ው​ያ​ዉን አቆመ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም አም​ላክ ጠራ።


አቤቱ፥ ከን​ፈ​ሮ​ችን ክፈት፥ አፌም ምስ​ጋ​ና​ህን ያወ​ራል።


የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የቆ​መ​በ​ትን ቦታ አዩ፤ ከእ​ግ​ሩም በታች እንደ ሰማይ መልክ የሚ​ያ​በራ፥ እንደ ብሩህ ሰን​ፔር ድን​ጋይ የሚ​መ​ስል ወለል ነበረ።


ብዙ ሕዝብም አንካሶችን፥ ዕውሮችንም፥ ድዳዎችንም፥ ጉንድሾችንም፥ ሌሎችንም ብዙ ይዘው ወደ እርሱ ቀረቡ በኢየሱስም እግር አጠገብ አስቀመጡአቸው፤ ፈወሳቸውም፤


እጅህ ወይም እግርህ ብታሰናክልህ፥ ቈርጠህ ከአንተ ጣላት፤ ሁለት እጅ ወይም ሁለት እግር ኖሮህ ወደ ዘላለም እሳት ከምትጣል ይልቅ አንካሳ ወይም ጕንድሽ ሆነህ ወደ ሕይወት መግባት ይሻልሀል።


በመቅደስም ዕውሮችና አንካሶች ወደ እርሱ ቀረቡና ፈወሳቸው።


ኢየሱስም ሰምቶ ተደነቀና ለተከተሉት እንዲህ አለ “እውነት እላችኋለሁ፤ በእስራኤል እንኳ እንዲህ ያለ ትልቅ እምነት አላገኘሁም።


እነርሱም ሲወጡ እነሆ ጋኔን ያደረበትን ድዳ ሰው ወደ እርሱ አመጡ።


ጋኔኑንም ካወጣው በኋላ ድዳው ተናገረ። ሕዝቡም “እንዲህ ያለ በእስራኤል ዘንድ ከቶ አልታየም፤” እያሉ ተደነቁ።


ሕዝቡም አይተው ተደነቁ፤ ለሰውም እንዲህ ያለ ሥልጣን የሰጠ እግዚአብሔርን አከበሩ።


ተነሥቶም ወዲያው አልጋውን ተሸክሞ በሁሉ ፊት ወጣ፤ ስለዚህም ሰዎች ሁሉ ተገረሙና “እንዲህ ያለ ከቶ አላየንም፤” ብለው እግዚአብሔርን አከበሩ።


ያለ መጠንም ተገረሙና “ሁሉን ደኅና አድርጎአል፤ ደንቆሮችም እንዲሰሙ ዲዳዎችም እንዲናገሩ ያደርጋል፤” አሉ።


እጅህ ብታሰናክልህ ቍረጣት፤ ሁለት እጅ ኖሮህ ትላቸው ወደማይሞትበት እሳቱም ወደማይጠፋበት ወደ ገሃነም ወደማይጠፋ እሳት ከመሄድ ጕንድሽ ሆነህ ወደ ሕይወት መግባት ይሻላል።


ነገር ግን በበ​ዓል ምሳ በም​ታ​ደ​ር​ግ​በት ጊዜ ድሆ​ች​ንና ጦም አዳ​ሪ​ዎ​ችን፥ ዕው​ሮ​ችን፥ እጅና እግ​ርም የሌ​ላ​ቸ​ውን ጥራ።


አገ​ል​ጋ​ዩም ተመ​ልሶ ለጌ​ታው ይህ​ንኑ ነገ​ረው፤ ያን​ጊ​ዜም ባለ​ቤቱ ተቈጣ፤ አገ​ል​ጋ​ዩ​ንም፦ ፈጥ​ነህ ወደ አደ​ባ​ባ​ይና ወደ ከተ​ማው ጐዳና ሂድ፤ ድሆ​ች​ንና ጦም አዳ​ሪ​ዎ​ችን፥ ዕው​ሮ​ች​ንና አን​ካ​ሶ​ችን ወደ​ዚህ አም​ጣ​ልኝ አለው።


በዚ​ያን ጊዜም አየ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አመ​ሰ​ገነ፤ ተከ​ተ​ለ​ውም፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ አይ​ተው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገ​ኑት።


ሁሉም ፈሩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አመ​ሰ​ገኑ፤ እን​ዲ​ህም አሉ፥ “ታላቅ ነቢይ ተነ​ሣ​ልን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝ​ቡን ጐብ​ኝ​ቶ​አ​ልና።”


ዕውር የነ​በ​ረ​ው​ንም ሰው ዳግ​መኛ ጠር​ተው፥ “ሂድ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ጋና አቅ​ርብ፤ ይህ ሰው ኀጢ​ኣ​ተኛ እንደ ሆነ እኛ እና​ው​ቃ​ለን” አሉት።


跟着我们:

广告


广告