Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ማቴዎስ 14:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ወዲያውም ኢየሱስ ተናገራቸውና “አይዞአችሁ፤ እኔ ነኝ፤ አትፍሩ፤” አላቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ኢየሱስም ወዲያውኑ፣ “አይዟችሁ፤ እኔ ነኝ አትፍሩ” አላቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ወዲያው ኢየሱስ ተናገራቸው፥ “አይዞአችሁ፥ እኔ ነኝ፤ አትፍሩ፤” አላቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ኢየሱስም ወዲያውኑ “አይዞአችሁ! እኔ ነኝ፤ አትፍሩ!” አላቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ወዲያውም ኢየሱስ ተናገራቸውና፦ አይዞአችሁ፥ እኔ ነኝ፤ አትፍሩ አላቸው።

参见章节 复制




ማቴዎስ 14:27
21 交叉引用  

እኔ ከአ​ንተ ጋር ነኝና አት​ፍራ፤ እኔ አም​ላ​ክህ ነኝና አት​ደ​ን​ግጥ፤ አበ​ረ​ታ​ሃ​ለሁ፤ እረ​ዳ​ህ​ማ​ለሁ፤ በጽ​ድ​ቄም ቀኝ ደግፌ እይ​ዝ​ሃ​ለሁ።


ያዕ​ቆብ ሆይ፥ አት​ፍራ፤ በቍ​ጥር ጥቂት የነ​በ​ርህ እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ እኔ እረ​ዳ​ሃ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ የሚ​ቤ​ዥ​ህም የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ ነው።


ይህን የሠ​ራና ያደ​ረገ፥ ትው​ል​ድ​ንም ከጥ​ንት የጠራ ማን ነው? እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊተ​ኛ​ውና ኋለ​ኛው እኔ ነኝ።


እኔ ነኝ፤ የማ​ጽ​ና​ናሽ እኔ ነኝ፤ አንቺ እን​ግ​ዲህ ዕወቂ፤ ማንን ፈራሽ? የሚ​ሞ​ተ​ውን ሰው እንደ ሣርም የሚ​ጠ​ወ​ል​ገ​ውን የሰው ልጅ ነውን?


ጴጥሮስም መልሶ “ጌታ ሆይ! አንተስ ከሆንህ በውሃው ላይ ወደ አንተ እንድመጣ እዘዘኝ፤” አለው።


ኢየሱስም ቀርቦ ዳሰሳቸውና “ተነሡ፤ አትፍሩም፤” አላቸው።


በዚያን ጊዜ ኢየሱስ “አትፍሩ፤ ሄዳችሁ ወደ ገሊላ እንዲሄዱ ለወንድሞቼ ተናገሩ፤ በዚያም ያዩኛል፤” አላቸው።


መልአኩም መልሶ ሴቶቹን አላቸው “እናንተስ አትፍሩ የተሰቀለውን ኢየሱስን እንድትሹ አውቃለሁና፤


እነሆም፥ በአልጋ የተኛ ሽባ ወደ እርሱ አመጡ። ኢየሱስም እምነታቸውን አይቶ ሽባውን “አንተ ልጅ! አይዞህ፤ ኀጢአትህ ተሰረየችልህ፤” አለው።


ሁሉ አይተውታልና ታወኩም። ወዲያውም ተናገራቸውና “አይዞአችሁ፤ እኔ ነኝ፤ አትፍሩ፤” አላቸው።


መል​አ​ኩም እን​ዲህ አለው፥ “ዘካ​ር​ያስ ሆይ፥ አት​ፍራ፤ ጸሎ​ትህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ተሰ​ም​ቶ​አ​ልና፤ ሚስ​ትህ ኤል​ሣ​ቤ​ጥም ትፀ​ን​ሳ​ለች፤ ወንድ ልጅ​ንም ትወ​ል​ድ​ል​ሃ​ለች፤ ስሙ​ንም ዮሐ​ንስ ትለ​ዋ​ለህ።


መል​አ​ኩም እን​ዲህ አላት፥ “ማር​ያም ሆይ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ባለ​ሟ​ል​ነ​ትን አግ​ኝ​ተ​ሻ​ልና አት​ፍሪ።


“አንተ ታናሽ መንጋ፥ አት​ፍራ፤ አባ​ታ​ችሁ መን​ግ​ሥ​ቱን ሊሰ​ጣ​ችሁ ወዶ​አ​ልና።


መል​አ​ኩም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እነሆ፥ ለእ​ና​ን​ተና ለሕ​ዝቡ ሁሉ ደስታ የሚ​ሆን ታላቅ የም​ሥ​ራች እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለ​ሁና አት​ፍሩ።


እን​ዲ​ሁም የስ​ም​ዖን ባል​ን​ጀ​ራ​ዎች የነ​በሩ የዘ​ብ​ዴ​ዎስ ልጆች ያዕ​ቆ​ብና ዮሐ​ንስ ተደ​ነቁ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ስም​ዖ​ንን፥ “አት​ፍራ፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲ​ህስ ሰውን ታጠ​ም​ዳ​ለህ” አለው።


በእ​ኔም ሰላ​ምን እን​ድ​ታ​ገኙ ይህን ነገ​ር​ኋ​ችሁ፤ በዓ​ለም ግን መከ​ራን ትቀ​በ​ላ​ላ​ችሁ፤ ነገር ግን ጽኑ፤ እኔ ዓለ​ሙን ድል ነሥ​ቼ​ዋ​ለ​ሁና።”


እር​ሱም፥ “እኔ ነኝ፤ አት​ፍሩ” አላ​ቸው።


በሁ​ለ​ተ​ኛ​ዪ​ቱም ሌሊት ጌታ​ችን ለጳ​ው​ሎስ ተገ​ልጦ፥ “ጽና፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ምስ​ክር እንደ ሆን​ኸኝ እን​ዲሁ በሮም ምስ​ክር ትሆ​ነ​ኛ​ለህ” አለው።


跟着我们:

广告


广告