Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ማርቆስ 15:43 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

43 የከበረ አማካሪ የሆነ የአርማትያስ ዮሴፍ መጣ፤ እርሱም ደግሞ የእግዚአብሔርን መንግሥት ይጠባበቅ ነበር፤ ደፍሮም ወደ ጲላጦስ ገባና የኢየሱስን ሥጋ ለመነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

43 የተከበረ የሸንጎ አባልና የእግዚአብሔርን መንግሥት ይጠባበቅ የነበረው የአርማትያሱ ዮሴፍ በድፍረት ወደ ጲላጦስ ሄዶ የኢየሱስን ሥጋ ለመነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

43 የተከበረ የሸንጎ አባልና የእግዚአብሔርን መንግሥት ይጠባበቅ የነበረው የአርማትያሱ ዮሴፍ በድፍረት ወደ ጲላጦስ ሄዶ የኢየሱስን ሥጋ ለመነው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

43 በዚያኑ ጊዜ የአይሁድ ሸንጎ አባል የነበረ ዮሴፍ የሚባል፥ የተከበረ የአርማትያስ ሰው መጣ። እርሱም የእግዚአብሔርን መንግሥት በተስፋ የሚጠባበቅ ሰው ነበር። በድፍረት ወደ ጲላጦስ ፊት ቀረበና የኢየሱስ አስከሬን እንዲሰጠው ለመነ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

43 እርሱም ደግሞ የእግዚአብሔርን መንግሥት ይጠባበቅ ነበር፤ ደፍሮም ወደ ጲላጦስ ገባና የኢየሱስን ሥጋ ለመነው።

参见章节 复制




ማርቆስ 15:43
16 交叉引用  

ነገር ግን ብዙዎቹ ፊተኞች ኋለኞች፥ ኋለኞችም ፊተኞች ይሆናሉ።


እንዲሁ ኋለኞች ፊተኞች፥ ፊተኞችም ኋለኞች ይሆናሉ፤ የተጠሩ ብዙዎች፥ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸውና።’ ”


በመሸም ጊዜ ዮሴፍ የተባለው ባለ ጠጋ ሰው ከአርማትያስ መጣ፤ እርሱም ደግሞ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ነበረ፤


ጴጥሮስም እስከ ሊቀ ካህናቱ ግቢ ውስጥ በሩቁ ተከተለው፤ ከሎሌዎችም ጋር ተቀምጦ እሳት ይሞቅ ነበር።


ጲላጦስም “አሁኑን እንዴት ሞተ?” ብሎ ተደነቀ፤ የመቶ አለቃውንም ጠርቶ “ከሞተ ቆይቶአልን?” ብሎ ጠየቀው፤


በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ስሙ ስም​ዖን የሚ​ባል አንድ ሰው ነበር፤ እር​ሱም ጻድ​ቅና ደግ ሰው ነበር፤ እር​ሱም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ደስ​ታ​ቸ​ውን ያይ ዘንድ ተስፋ ያደ​ርግ ነበር፤ መን​ፈስ ቅዱ​ስም ያደ​ረ​በት ነበር።


ያን​ጊ​ዜም ተነ​ሥታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገ​ነች፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ድኅ​ነት ተስፋ ለሚ​ያ​ደ​ርጉ ሁሉ ስለ እርሱ ተና​ገ​ረች።


እነሆ፥ በጎና ጻድቅ ሰው፥ የሸ​ንጎ አማ​ካ​ሪም የሆነ ዮሴፍ የሚ​ባል ሰው መጣ።


እር​ሱም በአ​ይ​ሁድ በም​ክ​ራ​ቸ​ውና በሥ​ራ​ቸው አል​ተ​ባ​በ​ረም ነበር፤ ሀገ​ሩም የይ​ሁዳ ዕጣ የሚ​ሆን አር​ማ​ት​ያስ ነበር፤ እር​ሱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት ተስፋ ያደ​ርግ ነበር።


ከዚ​ህም በኋላ አይ​ሁ​ድን ስለ​ፈራ በስ​ውር የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ደቀ መዝ​ሙር የነ​በ​ረው የአ​ር​ማ​ት​ያስ ሰው ዮሴፍ የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱ​ስን ሥጋ ይወ​ስድ ዘንድ ጲላ​ጦ​ስን ለመ​ነው፤ ጲላ​ጦ​ስም ፈቀ​ደ​ለት። እር​ሱም ሄዶ የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱ​ስን ሥጋ ወሰደ።


አይ​ሁድ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈሩ የከ​በሩ ሴቶ​ች​ንና የከ​ተ​ማ​ውን ሽማ​ግ​ሌ​ዎች አነ​ሳ​ሡ​አ​ቸው፤ በጳ​ው​ሎ​ስና በበ​ር​ና​ባስ ላይም ስደ​ትን አስ​ነሡ፤ ከሀ​ገ​ራ​ቸ​ውም አባ​ረ​ሩ​አ​ቸው።


ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ያመኑ ብዙ​ዎች ነበሩ፤ ከአ​ረ​ማ​ው​ያን ወገን የሆኑ ብዙ ደጋግ ሴቶ​ችም ነበሩ፤ ወን​ዶ​ችም ብዙ​ዎች ነበሩ።


ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ንም ብዙ​ዎቹ በእ​ስ​ራቴ ምክ​ን​ያት በጌታ ታመኑ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል ያለ ፍር​ሀት ጨክ​ነው ያስ​ተ​ምሩ ዘንድ እጅግ ተደ​ፋ​ፈሩ።


跟着我们:

广告


广告