Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ማርቆስ 14:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 የፋሲካን በግ በሚያርዱበት በቂጣ በዓል መጀመሪያ ቀን ደቀ መዛሙርቱ “ፋሲካን ትበላ ዘንድ ወዴት ሄደን ልናሰናዳ ትወዳለህ?” አሉት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 የፋሲካ በግ በሚታረድበት በቂጣ በዓል የመጀመሪያው ቀን፣ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሱስ ቀርበው፣ “የፋሲካ እራት የት እንድናዘጋጅልህ ትፈልጋለህ?” አሉት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 የፋሲካ በግ በሚታረድበት በቂጣ በዓል የመጀመሪያው ቀን፥ ደቀመዛሙርቱ ወደ ኢየሱስ ቀርበው፥ “የፋሲካ እራት የት እንድናዘጋጅልህ ትፈልጋለህ?” አሉት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 የፋሲካውን በግ በሚያርዱበት በቂጣ በዓል መጀመሪያ ቀን፥ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሱስ ቀርበው፦ “የፋሲካን ራት ለመብላት ወዴት ሄደን እንድናዘጋጅልህ ትፈልጋለህ?” ሲሉ ጠየቁት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ፋሲካን በሚያርዱበት በቂጣ በዓል መጀመሪያ ቀን ደቀ መዛሙርቱ፦ ፋሲካን ትበላ ዘንድ ወዴት ሄደን ልናሰናዳ ትወዳለህ? አሉት።

参见章节 复制




ማርቆስ 14:12
16 交叉引用  

ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ወር በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛው ቀን ሠርክ ጀም​ራ​ችሁ እስ​ከ​ዚሁ ወር ሃያ አን​ደኛ ቀን ሠርክ ድረስ ቂጣ ትበ​ላ​ላ​ችሁ።


በዚ​ህም ወር እስከ ዐሥራ አራ​ተኛ ቀን ድረስ ጠብ​ቁት፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ ሲመሽ ይረ​ዱት።


በእ​ሳ​ትም የተ​ጠ​በ​ሰ​ውን ሥጋ​ውን በዚ​ያች ሌሊት ይብሉ፤ ቂጣ​ውን እን​ጀ​ራም ከመ​ራራ ቅጠል ጋር ይብ​ሉት።


ሙሴም ሕዝ​ቡን አለ፥ “ከባ​ር​ነት ቤት ከግ​ብፅ የወ​ጣ​ች​ሁ​ባ​ትን ይህ​ችን ቀን ዐስቡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከዚህ ቦታ በበ​ረ​ታች እጅ አው​ጥ​ቶ​አ​ች​ኋ​ልና። ስለ​ዚህ የቦካ እን​ጀራ አት​ብሉ።


ኢየሱስም መልሶ “አሁንስ ፍቀድልኝ፤ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና” አለው። ያን ጊዜ ፈቀደለት።


ከሁለት ቀን በኋላ ፋሲካና የቂጣ በዓል ነበረ። የካህናት አለቆችም ጻፎችም እንዴት አድርገው በተንኰል እንደሚይዙትና እንደሚገድሉት ይፈልጉ ነበር።


ሲሰሙም ደስ አላቸው፤ ብርም ይሰጡት ዘንድ ተስፋ ሰጡት። በሚመች ጊዜም እንዴት አድርጎ አሳልፎ እንዲሰጠው ይፈልግ ነበር።


ከደቀ መዛሙርቱም ሁለት ላከ፤ እንዲህም አላቸው “ወደ ከተማ ሂዱ፤ ማድጋ ውኀ የተሸከመ ሰውም ይገናኛችኋል፤ተከተሉት።


ነገር ግን ቀጠ​ሮው በደ​ረሰ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጁን ላከ፤ ከሴ​ትም ተወ​ለደ፤ የኦ​ሪ​ት​ንም ሕግ ፈጸመ።


አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰ​ጠህ ከተ​ሞች በማ​ን​ኛ​ዪ​ቱም ፋሲ​ካን ትሠዋ ዘንድ አይ​ገ​ባ​ህም።


跟着我们:

广告


广告