Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ማርቆስ 11:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ለጸሎትም በቆማችሁ ጊዜ፥ በሰማያት ያለው አባታችሁ ደግሞ ኀጢአታችሁን ይቅር እንዲላችሁ፥ በማንም ላይ አንዳች ቢኖርባችሁ ይቅር በሉት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 እንዲሁም ለጸሎት በምትቆሙበት ጊዜ፣ የሰማዩ አባታችሁ በደላችሁን ይቅር እንዲልላችሁ፣ እናንተም በሰው ላይ ያላችሁን ሁሉ ይቅር በሉ። [

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 እንዲሁም ለጸሎት በምትቆሙበት ጊዜ፥ የሰማዩ አባታችሁ ኀጢአታችሁን ይቅር እንዲልላችሁ፥ እናንተም በሰው ላይ ያላችሁን ሁሉ ይቅር በሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 በሰማይ ያለው አባታችሁ ኃጢአታችሁን ይቅር እንዲልላችሁ እናንተም ለጸሎት በምትቆሙበት ጊዜ ሰው በአንዳች ነገር አስቀይሞአችሁ ከሆነ ይቅርታ አድርጉለት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ለጸሎትም በቆማችሁ ጊዜ፥ በሰማያት ያለው አባታችሁ ደግሞ ኃጢአታችሁን ይቅር እንዲላችሁ፥ በማንም ላይ አንዳች ቢኖርባችሁ ይቅር በሉት።

参见章节 复制




ማርቆስ 11:25
13 交叉引用  

እርሱም ታላቁን ካህን ኢያሱን በእግዚአብሔር መልአክ ፊት ቆሞ አሳየኝ፥ ሰይጣንም ይከስሰው ዘንድ በስተ ቀኙ ቆሞ ነበር።


እንግዲህ መባህን በመሠዊያው ላይ ብታቀርብ፥ በዚያም ወንድምህ አንዳች በአንተ ላይ እንዳለው ብታስብ፥


እኛም ደግሞ የበደሉንን ይቅር እንደምንል በደላችንን ይቅር በለን፤


“ስትጸልዩም እንደ ግብዞች አትሁኑ፤ ለሰው ይታዩ ዘንድ በምኩራብና በመንገድ ማዕዘን ቆመው መጸለይን ይወዳሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፤ ዋጋቸውን ተቀብለዋል።


ፈሪ​ሳ​ዊ​ውም ቆመና እን​ዲህ ብሎ ጸለየ፦ ‘አቤቱ እንደ ሌሎች ሰዎች፥ እንደ ቀማ​ኞ​ችና እንደ ዐመ​ፀ​ኞች፥ እንደ አመ​ን​ዝ​ሮ​ችም፥ ወይም እን​ደ​ዚህ ቀራጭ ያላ​ደ​ረ​ግ​ኸኝ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።


ቀራጩ ግን ራቅ ብሎ ቆመ፤ ዐይ​ኖ​ቹ​ንም ወደ ላይ ወደ ሰማይ ሊያ​ነሣ አል​ወ​ደ​ደም፤ ደረ​ቱ​ንም እየ​መታ፦ ‘አቤቱ፥ እኔን ኀጢ​ኣ​ተ​ኛ​ውን ይቅር በለኝ’ አለ።


አት​ፍ​ረዱ፥ አይ​ፈ​ረ​ድ​ባ​ች​ሁ​ምም፤ አት​በ​ድሉ፥ አይ​በ​ድ​ሉ​አ​ች​ሁ​ምም፤ ይቅር በሉ፥ ይቅ​ርም ይሉ​አ​ች​ኋል።


እርስ በር​ሳ​ች​ሁም ቸሮ​ችና ርኅ​ሩ​ኆች ሁኑ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በክ​ር​ስ​ቶስ ይቅር እን​ዳ​ላ​ችሁ ይቅር ተባ​ባሉ።


ባል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ች​ሁን ታገ​ሡ​አ​ቸው፤ እርስ በር​ሳ​ችሁ ይቅር ተባ​ባሉ፤ ባል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ች​ሁን የነ​ቀ​ፋ​ች​ሁ​በ​ትን ሥራ ተዉ፤ ክር​ስ​ቶስ ይቅር እን​ዳ​ላ​ችሁ እና​ን​ተም እን​ዲሁ አድ​ርጉ።


ምሕረትን ለማያደርግ ምሕረት የሌለበት ፍርድ ይሆናልና፤ ምሕረትም በፍርድ ላይ ይመካል።


እነዚህ በምድር ጌታ ፊት የሚቆሙ ሁለቱ ወይራዎችና ሁለቱ መቅረዞች ናቸው።


跟着我们:

广告


广告