Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሉቃስ 9:39 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

39 እነሆ፥ ጋኔን ሊነ​ጥ​ቀኝ ነው፤ ድን​ገ​ትም ያስ​ጮ​ኸ​ዋል፤ ጥሎም ያፈ​ራ​ግ​ጠ​ዋል፤ አረ​ፋም ያስ​ደ​ፍ​ቀ​ዋል፤ ቀጥ​ቅጦ በጭ​ንቅ ይተ​ወ​ዋል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

39 መንፈስ ሲይዘው በድንገት ይጮኻል፤ ዐረፋ እያስደፈቀው ያንፈራግጠዋል፤ ጕዳትም ካደረሰበት በኋላ በስንት መከራ ይተወዋል፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

39 እነሆም፥ ርኩስ መንፈስ ይይዘዋል፤ ድንገትም ይጮኻል፤ አረፋም እያስደፈቀው ያንፈራግጠዋል፤ አድቅቆ በጭንቅ ይለቀዋል፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

39 እነሆ! ርኩስ መንፈስ በድንገት ይዞ ያስጮኸዋል፤ በመሬት ላይ ጥሎ ዐረፋ እያስደፈቀ ያንፈራግጠዋል፤ ሰውነቱንም እያቈሰለ በአሳር ይለቀዋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

39 እነሆም፥ ጋኔን ይይዘዋል፥ ድንገትም ይጮኻል አረፋም እያስደፈቀው ያንፈራግጠዋል፥ እየቀጠቀጠም በጭንቅ ይለቀዋል፤

参见章节 复制




ሉቃስ 9:39
11 交叉引用  

በያዘውም ስፍራ ሁሉ ይጥለዋል፤ አረፋም ይደፍቃል፤ ጥርሱንም ያፋጫል፤ ይደርቃልም፤ እንዲያወጡለትም ለደቀ መዛሙርትህ ነገርኋቸው፤ አልቻሉምም” አለው።


ወደ እርሱም አመጡት። እርሱንም ባየ ጊዜ ያ መንፈስ ወዲያው አንፈራገጠው፤ ወደ ምድርም ወድቆ አረፋ እየደፈቀ ተንፈራፈረ።


ጮኾም እጅግም አንፈራግጦት ወጣ፤ ብዙዎችም “ሞተ” እስኪሉ ድረስ እንደ ሙት ሆነ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ዝም በልና ከእ​ርሱ ውጣ” ብሎ ገሠ​ጸው፤ ጋኔ​ኑም በም​ኵ​ራቡ መካ​ከል ጣለ​ውና ከእ​ርሱ ወጣ፤ ነገር ግን ምንም አል​ጐ​ዳ​ውም።


ክፉ​ውን ጋኔን ከዚያ ሰው ላይ እን​ዲ​ወጣ ያዝ​ዘው ነበ​ርና፤ ዘወ​ት​ርም አእ​ም​ሮ​ዉን ያሳ​ጣው ነበ​ርና፤ ብላ​ቴ​ኖ​ችም በእ​ግር ብረት አስ​ረው ይጠ​ብ​ቁት ነበር፤ እግር ብረ​ቱ​ንም ይሰ​ብር ነበር፤ ጋኔ​ኑም በም​ድረ በዳ ያዞ​ረው ነበር።


አንድ ሰውም በሕ​ዝቡ መካ​ከል ጮኾ እን​ዲህ አለው፥ “መም​ህር ሆይ፥ እርሱ ለእኔ አንድ ነውና ልጄን ታይ​ልኝ ዘንድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ።


እን​ዲ​ያ​ወ​ጡ​ትም ደቀ መዛ​ሙ​ር​ት​ህን ለመ​ን​ሁ​አ​ቸው፤ ነገር ግን ማው​ጣት ተሳ​ና​ቸው።”


እና​ን​ተስ ከአ​ባ​ታ​ችሁ ከሰ​ይ​ጣን ናችሁ፤ የአ​ባ​ታ​ች​ሁ​ንም ፈቃድ ልታ​ደ​ርጉ ትወ​ዳ​ላ​ችሁ፤ እርሱ ከጥ​ንት ጀምሮ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ በእ​ው​ነ​ትም አይ​ቆ​ምም፤ በእ​ርሱ ዘንድ እው​ነት የለ​ምና፤ ሐሰ​ት​ንም በሚ​ና​ገ​ር​በት ጊዜ ከራሱ አን​ቅቶ ይና​ገ​ራል፤ ሐሰ​ተኛ ነውና፤ የሐ​ሰ​ትም አባት ነውና።


በመጠን ኑሩ፤ ንቁም፤ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና፤


በእነርሱም ላይ ንጉሥ አላቸው፤ እርሱም የጥልቅ መልአክ ነው፤ ስሙም በዕብራይስጥ አባዶን በግሪክም አጶልዮን ይባላል።


跟着我们:

广告


广告