Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሉቃስ 7:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ሄደ፤ ወደ ቤቱም በቀ​ረበ ጊዜ፥ የመቶ አለ​ቃዉ ወዳ​ጆ​ቹን እን​ዲህ ብሎ ላከ፥ “አቤቱ፥ አት​ድ​ከም፤ ከቤቴ ጣራ በታች ልት​ገባ አይ​ገ​ባ​ኝ​ምና።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ኢየሱስም ከእነርሱ ጋራ ሄደ። እርሱም ወደ ቤቱ በተቃረበ ጊዜ፣ የመቶ አለቃው ወዳጆቹን ልኮ እንዲህ አለው፤ “ጌታ ሆይ፤ ከቤቴ ጣራ በታች ልትገባ የሚገባኝ ሰው አይደለሁምና አትድከም፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ሄደ። ወደ ቤቱም በቀረበ ጊዜ መቶ አለቃው ወዳጆቹን ወደ እርሱ ልኮ እንዲህ አለው፦ “ጌታ ሆይ! ከቤቴ ጣራ በታች ልትገባ አይገባኝምና ራስህን አታድክም፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ስለዚህ ኢየሱስ ከእነርሱ ጋር አብሮ ሄደ፤ ወደ ቤቱም በቀረበ ጊዜ የመቶ አለቃው ወዳጆቹን እንዲህ ሲል ወደ ኢየሱስ ላከ፦ “ጌታ ሆይ፥ አንተ ወደ ቤቴ ትገባ ዘንድ ያልተገባሁ ነኝና ወደ ቤቴ ለመምጣት አትድከም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ሄደ። አሁንም ወደ ቤቱ በቀረበ ጊዜ የመቶው አለቃ ወዳጆቹን ወደ እርሱ ላከ፤ አለውም፦ ጌታ ሆይ በቤቴ ጣራ በታች ልትገባ አይገባኝምና አትድከም፤

参见章节 复制




ሉቃስ 7:6
15 交叉引用  

ለባ​ሪ​ያህ በአ​ደ​ረ​ግ​ኸው በም​ሕ​ረ​ት​ህና በእ​ው​ነ​ት​ህም ሁሉ በጎ​ውን አድ​ር​ግ​ልኝ፤ በት​ሬን ብቻ ይዤ ይህን ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ግሬ ነበ​ርና፥ አሁን ግን የሁ​ለት ክፍል ሠራ​ዊት ሆንሁ።


እንዲሁም የሰው ልጅ ሊያገለግል ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም።”


እኔስ “ለንስሐ በውሃ አጠምቃችኋለሁ፤ ጫማውን እሸከም ዘንድ የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይልቅ ይበረታል፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስ በእሳትም ያጠምቃችኋል፤


ከእርሱም ጋር ሄደ። ብዙ ሕዝብም ተከተሉት አጋፉትም።


ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስም ይህን አይቶ ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ እግር በታች ሰገ​ደና፥ “እኔ ኀጢ​አ​ተኛ ሰው ነኝና አቤቱ ከእኔ ፈቀቅ በል፤” አለው።


ወደ ጌታ​ችን ወደ ኢየ​ሱ​ስም መጥ​ተው ማለ​ዱት፤ እን​ዲ​ህም አሉት፥ “ፈጥ​ነህ ውረድ፤ ይህን ልታ​ደ​ር​ግ​ለት ይገ​ባ​ዋ​ልና።


እርሱ ወገ​ና​ች​ንን ይወ​ዳ​ልና፤ ምኵ​ራ​ባ​ች​ን​ንም ሠር​ቶ​ል​ና​ልና።”


እኔም ወደ አንተ ልመጣ አይ​ገ​ባ​ኝም፤ ነገር ግን በቃ​ልህ እዘዝ፤ ብላ​ቴ​ና​ዬም ይድ​ናል።


ይህ​ንም ሲና​ገር አንድ ሰው ከም​ኵ​ራቡ ሹም ቤት መጥቶ፥ “ልጅ​ህስ ሞታ​ለች እን​ግ​ዲህ መም​ህ​ሩን አታ​ድ​ክ​መው” አለው።


ስለ ናዝ​ሬቱ ስለ ኢየ​ሱስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ን​ፈስ ቅዱስ በኀ​ይ​ልም እንደ ቀባው፥ እየ​ዞ​ረም መል​ካም እንደ አደ​ረገ፥ ሰይ​ጣን ያሸ​ነ​ፋ​ቸ​ው​ንም እንደ ፈወሰ ታው​ቃ​ላ​ችሁ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ርሱ ጋር ነበ​ርና።


በጌታ ፊት ራሳችሁን አዋርዱ፤ ከፍ ከፍም ያደርጋችኋል።


ነገር ግን ጸጋን አብልጦ ይሰጣል፤ ስለዚህ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል፤” ይላል።


跟着我们:

广告


广告