Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሉቃስ 7:47 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

47 ስለ​ዚ​ህም እል​ሃ​ለሁ፤ ብዙ ኀጢ​ኣቷ ተሰ​ር​ዮ​ላ​ታል፤ በብዙ ወድ​ዳ​ለ​ችና፤ ጥቂት የሚ​ወ​ድድ ጥቂት ይሰ​ረ​ይ​ለ​ታል፤ ብዙ የሚ​ወ​ድ​ድም ብዙ ይሰ​ረ​ይ​ለ​ታል።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

47 ስለዚህ እልሃለሁ፤ በብዙ ወድዳለችና ብዙው ኀጢአቷ ተሰርዮላታል፤ በትንሹ የተሰረየለት ግን የሚወድደው በትንሹ ነው።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

47 ስለዚህም እጅግ ወዳለችና ብዙ ኃጢአትዋ ተሰርዮላታል እልሃለሁ፤ ጥቂት ግን የሚሰረይለት ጥቂት ይወዳል።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

47 ስለዚህ ብዙ ስለ ወደደች ብዙ ኃጢአትዋ ይቅር ተብሎላታል እልሃለሁ፤ ኃጢአቱ በጥቂት ይቅር የሚባልለት ግን የሚወደውም በጥቂቱ ነው።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

47 ስለዚህ እልሃለሁ፥ እጅግ ወዳለችና ብዙ ያለው ኃጢአትዋ ተሰርዮላታል፤ ጥቂት ግን የሚሰረይለት ጥቂት ይወዳል።

参见章节 复制




ሉቃስ 7:47
25 交叉引用  

“ኑና እን​ዋ​ቀስ” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ኀጢ​አ​ታ​ችሁ እንደ አለላ ቢሆን እንደ በረዶ አነ​ጻ​ዋ​ለሁ፤ እንደ ደምም ቢቀላ እንደ ባዘቶ አጠ​ራ​ዋ​ለሁ።


ክፉ ሰው መን​ገ​ዱን፥ በደ​ለ​ኛም ዐሳ​ቡን ይተው፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይመ​ለስ፤ እር​ሱም ይም​ረ​ዋል፤ እርሱ ብዙ በደ​ላ​ች​ሁን ይተ​ው​ላ​ች​ኋ​ልና።


ታስቢ ዘንድ፥ ታፍ​ሪም ዘንድ፥ ደግ​ሞም ስላ​ደ​ረ​ግ​ሽው ነገር ሁሉ ይቅር ባል​ሁሽ ጊዜ፥ስለ ኀፍ​ረ​ትሽ አፍ​ሽን ትከ​ፍቺ ዘንድ አይ​ቻ​ል​ሽም፤” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ተመልሶ ይምረናል፥ ክፋታችንንም ይጠቀጥቃል፥ ኃጢአታችንንም በባሕሩ ጥልቅ ይጥለዋል።


ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤ ከእኔ ይልቅም ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም።


የጠ​ራው ፈሪ​ሳ​ዊም ባየ ጊዜ በልቡ ዐሰበ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ይህስ ነቢይ ቢሆን ኖሮ ይህቺ የም​ት​ዳ​ስ​ሰው ሴት ማን እንደ ሆነች፥ እን​ዴ​ትስ እንደ ነበ​ረች ባላ​ወ​ቀም ነበ​ርን? ኀጢ​አ​ተኛ ናትና።”


አንተ ራሴን እንኳ ዘይት አል​ቀ​ባ​ኸ​ኝም፤ እር​ስዋ ግን እግ​ሬን ሽቱ ቀባ​ችኝ።


ሴቲ​ቱ​ንም፥ “ኀጢ​ኣ​ትሽ ተሰ​ረ​የ​ልሽ” አላት።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እር​ሱን ለእ​ስ​ራ​ኤል ንስ​ሓን፥ የኀ​ጢ​አ​ት​ንም ስር​የት ይሰጥ ዘንድ ራስም አዳ​ኝም አደ​ረ​ገው፤ በቀ​ኙም አስ​ቀ​መ​ጠው።


ኦሪ​ትስ ኀጢ​አ​ትን ታበ​ዛት ዘንድ መጣች፤ ኀጢ​አ​ትም ከበ​ዛች ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ በዛች።


የክ​ር​ስ​ቶስ ፍቅር በዚህ አሳብ እን​ድ​ን​ጸና ያስ​ገ​ድ​ደ​ናል፤ ሁሉ ፈጽ​መው ስለ ሞቱ አንዱ ስለ ሁሉ ቤዛ ሆኖ ሞቶ​አ​ልና።


በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ዘንድ በፍ​ቅር የም​ት​ሠራ እም​ነት እንጂ መገ​ዘር አይ​ጠ​ቅ​ም​ምና፤ አለ​መ​ገ​ዘ​ርም ግዳጅ አይ​ፈ​ጽ​ም​ምና።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ባለ መጥ​ፋት ከሚ​ወ​ዱት ሁሉ ጋር ጸጋ ይሁን። አሜን። በሮሜ ተጽፋ በቲ​ኪ​ቆስ እጅ ወደ ኤፌ​ሶን ሰዎች የተ​ላ​ከች መል​እ​ክት ተፈ​ጸ​መች። ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ጋና ይሁን። አሜን።


ስለ​ዚ​ህም በአ​እ​ም​ሮና በልብ ጥበብ ሁሉ ፍቅ​ራ​ችሁ እን​ዲ​በዛ፥ እን​ዲ​ጨ​ም​ርም እጸ​ል​ያ​ለሁ፤


የጌታችንም ጸጋ በክርስቶስ ኢየሱስ ካሉ ከእምነትና ከፍቅር ጋር አብልጦ በዛ።


ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።


ልጆቼ ሆይ፥ በሥራና በእውነት እንጂ በቃልና በአንደበት አንዋደድ።


እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ እንወደዋለን።


ትእዛዛቱን ልንጠብቅ የእግዚአብሔር ፍቅር ይህ ነውና፤ ትእዛዛቱም ከባዶች አይደሉም።


跟着我们:

广告


广告