ሉቃስ 6:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፥ “እጠይቃችኋለሁ፤ በሰንበት ሊደረግ የሚገባው ምንድነው? መልካም መሥራት ነውን? ወይስ ክፉ መሥራት? ነፍስን ማዳን ነውን? ወይስ መግደል?” 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም9 ኢየሱስም፣ “እስኪ አንድ ነገር ልጠይቃችሁ፤ በሰንበት ቀን የተፈቀደው በጎ ማድረግ ነው ወይስ ክፉ ማድረግ? ነፍስ ማዳን ነው ወይስ ማጥፋት?” አላቸው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “እስቲ ልጠይቃችሁ፤ በሰንበት ቀን የተፈቀደው በጎ ማድረግ ነውን ወይንስ ክፉ? ነፍስ ማዳን ነውን ወይንስ ማጥፋት?” 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 በዚህ ጊዜ ኢየሱስ “እስቲ ልጠይቃችሁ፤ ለመሆኑ በሰንበት ቀን የተፈቀደው መልካም ማድረግ ነውን? ወይስ ክፉ? ነፍስን ማዳን ነውን ወይስ ማጥፋት?” አላቸው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 ኢየሱስም፦ እጠይቃችኋለሁ፤ በሰንበት በጎ ማድረግ ተፈቅዶአልን ወይስ ክፉ? ነፍስ ማዳንን ወይስ መግደል? አላቸው። 参见章节 |