Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሉቃስ 6:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 አሁ​ንም ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ውደዱ፤ መል​ካ​ምም አድ​ር​ጉ​ላ​ቸው፤ እን​ዲ​መ​ል​ሱ​ላ​ችሁ ተስፋ ሳታ​ደ​ርጉ አበ​ድሩ፤ ዋጋ​ች​ሁም ብዙ ይሆ​ናል፤ የል​ዑ​ልም ልጆች ትሆ​ና​ላ​ችሁ፤ እርሱ ለበ​ጎ​ዎ​ችና ለክ​ፉ​ዎች ቸር ነውና።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 ነገር ግን ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ መልካም አድርጉ፤ መልሳችሁ ለመቀበል ተስፋ ሳታደርጉም አበድሩ፤ በዚህም ወሮታችሁ ታላቅ ይሆናል፤ የልዑልም ልጆች ትሆናላችሁ፤ እርሱ ለማያመሰግኑና ለክፉዎች ቸር ነውና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 ነገር ግን ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ መልካምም አድርጉ፤ ይመለስልናልም ብላችሁ ምንም ተስፋ ሳታደርጉ አበድሩ፤ ዋጋችሁም ታላቅ ይሆናል፤ የልዑልም ልጆች ትሆናላችሁ፤ እርሱ ለማያመሰግኑና ለክፉዎች ቸር ነውና።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 እናንተ ግን ጠላቶቻችሁን ውደዱ! መልካም ነገርም አድርጉላቸው፤ ‘ብድራችን ይመለስልናል’ ብላችሁ ተስፋ ሳታደርጉ አበድሩ፤ ይህን ብታደርጉ ዋጋችሁ ትልቅ ይሆናል፤ የልዑል እግዚአብሔር ልጆችም ትሆናላችሁ፤ እርሱ ለውለታ ቢሶችና ለክፉዎች እንኳ ሳይቀር ቸር ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 ነገር ግን ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ መልካም አድርጉ፤ ምንም ተስፋ ሳታደርጉም አበድሩ፥ ዋጋችሁም ታላቅ ይሆናል፥ የልዑልም ልጆች ትሆናላችሁ፥ እርሱ ለማያመሰግኑ ለክፉዎችም ቸር ነውና።

参见章节 复制




ሉቃስ 6:35
21 交叉引用  

እንደ አም​ላ​ካ​ችን እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማን ነው? በል​ዕ​ልና የሚ​ኖር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስደ​ተ​ኞ​ችን ይጠ​ብ​ቃ​ቸ​ዋል፤ ድሃ አደ​ጎ​ች​ንና ባል​ቴ​ቶ​ችን ይቀ​በ​ላ​ቸ​ዋል፤ የኃ​ጥ​ኣ​ን​ንም መን​ገድ ያጠ​ፋል።


ሕግ​ህን እን​ዳ​ይ​ረሱ አት​ግ​ደ​ላ​ቸው፤ አቤቱ፥ አም​ላ​ኬና ረዳቴ፥ በኀ​ይ​ልህ በት​ና​ቸው፥ አዋ​ር​ዳ​ቸ​ውም።


ለድሃ ቸርነትን የሚያደርግ ለእግዚአብሔር ያበድራል፥ እንደ ስጦታውም መልሶ ይከፍለዋል።


ለድሃ የሚራራ እርሱ ይበላል እንጀራውን ለድሃ ሰጥቶአልና። ለሰጠው ሀብታምም የሚከፍል አይደለምና። መማለጃን የሰጠ ሰው ድል መንሣትንና ሞገስን ያገኛል፥ ነገር ግን የተቀበለውን ነፍስ ያጠፋል።


የሚያስተራርቁ ብፁዓን ናቸው፤የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና።


በታላቅ ድምፅም እየጮኸ “የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሆይ! ከአንተ ጋር ምን አለኝ? እንዳታሠቃየኝ በእግዚአብሔር አምልሃለሁ፤” አለ፤


እር​ሱም ታላቅ ነው፤ የል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅም ይባ​ላል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም የአ​ባ​ቱን የዳ​ዊ​ትን ዙፋን ይሰ​ጠ​ዋል።


ሰማ​ያዊ አባ​ታ​ችሁ የሚ​ራራ እንደ ሆነ እና​ን​ተም የም​ት​ራሩ ሁኑ።


እርስ በር​ሳ​ች​ሁም ብቷ​ደዱ፥ የእኔ ደቀ መዛ​ሙ​ርት እንደ ሆና​ችሁ በዚህ ሁሉ ያው​ቋ​ች​ኋል።”


ብዙ ፍሬ ብታ​ፈሩ፥ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቴም ብት​ሆኑ በዚህ አባቴ ይከ​በ​ራል።


ከዚ​ህም ሁሉ ጋር መል​ካም ሥራን እየ​ሠራ ከሰ​ማይ ዝና​ምን፥ ፍሬ የሚ​ሆ​ን​በ​ት​ንም ወራት ሲሰ​ጠን፥ ልባ​ች​ን​ንም በመ​ብ​ልና በደ​ስታ ሲሞ​ላው ራሱን ያለ ምስ​ክር አል​ተ​ወም።”


የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ቸር​ነ​ቱን ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ በእ​ርሱ ድህ​ነት እና​ንተ ባለ​ጸ​ጎች ትሆኑ ዘንድ እርሱ ባለ​ጸጋ ሲሆን፥ ስለ እና​ንተ ራሱን ድሃ አደ​ረገ።


ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉና፤ ገንዘብን የሚወዱ፥ ትምክህተኞች፥ ትዕቢተኞች፥ ተሳዳቢዎች፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥ የማያመሰግኑ፥ ቅድስና የሌላቸው፥


跟着我们:

广告


广告