Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሉቃስ 6:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 የሚ​ረ​ግ​ሙ​አ​ች​ሁን መር​ቁ​አ​ቸው፤ ለሚ​በ​ድ​ሉ​አ​ች​ሁም ጸል​ዩ​ላ​ቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 የሚረግሟችሁን መርቁ፤ ለሚበድሏችሁም ጸልዩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 የሚረግሙአችሁንም መርቁ፤ ስለሚበድሉአችሁም ጸልዩ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 የሚረግሙአችሁን መርቁ፤ ለሚበድሉአችሁም ጸልዩላቸው፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ስለሚበድሉአችሁም ጸልዩ።

参见章节 复制




ሉቃስ 6:28
13 交叉引用  

ንጉ​ሡም ኢዮ​ር​ብ​ዓም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሰው፥ “አሁን የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፊት ለምን፤ እጄም ወደ እኔ ትመ​ለስ ዘንድ ስለ እኔ ጸልይ” አለው፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለመነ፤ የን​ጉ​ሡም እጅ ወደ እርሱ ተመ​ለ​ሰች። እንደ ቀድ​ሞም ሆነች።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን በቀ​ልን አድ​ር​ገ​ዋ​ልና፥ በቀ​ላ​ቸ​ው​ንም አጽ​ን​ተ​ዋ​ልና፥ እስ​ራ​ኤ​ልም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይጠፉ ዘንድ ነፍ​ሳ​ቸው ደስ ይላ​ታ​ልና፤


ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ያሳ​ድ​ዱ​አ​ትና ይበ​ዘ​ብ​ዙ​አት ዘንድ በል​ባ​ቸው ሁሉ ደስ​ታና በነ​ፍ​ሳ​ቸው ንቀት ምድ​ሬን ርስት አድ​ር​ገው ለራ​ሳ​ቸው በሰጡ በቀ​ሩት አሕ​ዛ​ብና በኤ​ዶ​ም​ያስ ሁሉ ላይ በቅ​ን​አቴ እሳት ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፤


እኔ ግን እላችኋለሁ፤ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፤ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፤ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፤ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “አባት ሆይ፥ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን ኣያ​ው​ቁ​ምና ይቅር በላ​ቸው” አለ፤ በል​ብ​ሱም ላይ ዕጣ ተጣ​ጣ​ሉና ተካ​ፈሉ።


“ለም​ት​ሰ​ሙኝ ለእ​ና​ንተ ግን እን​ዲህ እላ​ች​ኋ​ለሁ፦ ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ውደዱ፤ ለሚ​ጠ​ሉ​አ​ች​ሁም መል​ካም አድ​ርጉ።


አሁ​ንም ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ውደዱ፤ መል​ካ​ምም አድ​ር​ጉ​ላ​ቸው፤ እን​ዲ​መ​ል​ሱ​ላ​ችሁ ተስፋ ሳታ​ደ​ርጉ አበ​ድሩ፤ ዋጋ​ች​ሁም ብዙ ይሆ​ናል፤ የል​ዑ​ልም ልጆች ትሆ​ና​ላ​ችሁ፤ እርሱ ለበ​ጎ​ዎ​ችና ለክ​ፉ​ዎች ቸር ነውና።


አሕ​ዛ​ብና አይ​ሁድ ግን ከአ​ለ​ቆ​ቻ​ቸው ጋር ሊያ​ን​ገ​ላ​ት​ዋ​ቸ​ውና በድ​ን​ጋይ ሊደ​በ​ድ​ቧ​ቸው ተነሡ።


በጕ​ል​በ​ቱም ተን​በ​ር​ክኮ፥ “አቤቱ፥ ይህን ኀጢ​አት አት​ቍ​ጠ​ር​ባ​ቸው” ብሎ በታ​ላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህ​ንም ብሎ ሞተ፤ ሳው​ልም በእ​ስ​ጢ​ፋ​ኖስ ሞት ተባ​ባሪ ነበር።


የሚ​ያ​ሳ​ድ​ዱ​አ​ች​ሁን መርቁ፤ መርቁ እንጂ አት​ር​ገሙ።


በእ​ጃ​ችን ሥራ እያ​ገ​ለ​ገ​ልን እን​ደ​ክ​ማ​ለን፤ ይረ​ግ​ሙ​ናል፤ እኛ ግን እን​መ​ር​ቃ​ቸ​ዋ​ለን፤ ያሳ​ድ​ዱ​ናል፤ እኛ ግን እን​ጸ​ል​ይ​ላ​ቸ​ዋ​ለን፤ እን​ታ​ገ​ሣ​ቸ​ዋ​ለ​ንም።


ከአንድ አፍ በረከትና መርገም ይወጣሉ። ወንድሞቼ ሆይ! ይህ እንዲህ ሊሆን አይገባም።


ክፉን በክፉ ፈንታ ወይም ስድብን በስድብ ፈንታ አትመልሱ፤ በዚህ ፈንታ ባርኩ እንጂ፤ በረከትን ልትወርሱ ለዚህ ተጠርታችኋልና።


跟着我们:

广告


广告